Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 9:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ፈረ​ሰ​ኛ​ውም ሊቀ​በ​ላ​ቸው ሄዶ፥ “ንጉሡ እን​ዲህ ይላል፦ ሰላም ነውን?” አላ​ቸው። ኢዩም፥ “አንተ ከሰ​ላም ጋር ምን አለህ? ወደ ኋላዬ ተመ​ል​ሰህ ተከ​ተ​ለኝ” አለ። ሰላ​ዩም፥ “መል​እ​ክ​ተ​ኛው ደረ​ሰ​ባ​ቸው፥ ነገር ግን አል​ተ​መ​ለ​ሰም” ብሎ ነገ​ረው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ፈረሰኛውም ኢዩን ለመገናኘት ጋልቦ ሄደና፣ “ንጉሡ፣ ‘የመጣችሁት በሰላም ነውን?’ ብሏል” አለው። ኢዩም፣ “ስለ ሰላም መጨነቅ የአንተ ጕዳይ አይደለም! ይልቅስ ወደ ኋላ ዕለፍና ተከተለኝ” አለው። ጠባቂውም፣ “መልእክተኛው ከእነርሱ ዘንድ ደርሷል፤ ነገር ግን ተመልሶ አልመጣም” ብሎ አሳወቀ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 መልእክተኛውም ጋልቦ ሄዶ ኢዩን “ንጉሡ አመጣጥህ በወዳጅነት እንደሆነ ማወቅ ይፈልጋል” ሲል ጠየቀው። ኢዩም “አንተ ከሰላም ጋር ምን ግንኙነት አለህ? ይልቅስ ወደ ኋላ አልፈህ ተከተለኝ!” ሲል መለሰለት። በከተማይቱም መጠበቂያ ግንብ ላይ የነበረው ዘብ “መልእክተኛው በመምጣት ላይ ወዳለው ጭፍራ ደርሶአል፤ ነገር ግን ተመልሶ አልመጣም” ሲል አስረዳ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 መልእክተኛውም ጋልቦ ሄዶ ኢዩን “ንጉሡ አመጣጥህ በወዳጅነት እንደ ሆነ ማወቅ ይፈልጋል” ሲል ጠየቀው። ኢዩም “አንተ ከሰላም ጋር ምን ግንኙነት አለህ? ይልቅስ ወደ ኋላ አልፈህ ተከተለኝ!” ሲል መለሰለት። በከተማይቱም መጠበቂያ ግንብ ላይ የነበረው ዘብ “መልእክተኛው በመምጣት ላይ ወዳለው ጭፍራ ደርሶአል፤ ነገር ግን ተመልሶ አልመጣም” ሲል አስረዳ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ፈረሰኛውም ሊገናኘው ሄዶ “ንጉሡ እንዲህ ይላል ‘ሰላም ነውን?’” አለ። ኢዩም “አንተ ከሰላም ጋር ምን አለህ? ወደ ኋላዬ አልፈህ ተከተለኝ፤” አለ። ሰላዩም “መልእክተኛው ደረሰባቸው፤ ነገር ግን አልተመለሰም፤” ብሎ ነገረው።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 9:18
8 Cross References  

ኢዮ​ራ​ምም ኢዩን ባየ ጊዜ “ኢዩ ሆይ፥ ሰላም ነውን?” አለ። እር​ሱም፥ “የእ​ና​ትህ የኤ​ል​ዛ​ቤል ግል​ሙ​ት​ና​ዋና መተቷ ሲበዛ ምን ሰላም አለ?” ብሎ መለሰ።


ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ፈረ​ሰኛ ሰደደ፤ ወደ እነ​ር​ሱም ደርሶ ንጉሡ እን​ዲህ ይላል፥ “ሰላም ነውን?” አላ​ቸው። ኢዩም፥ “አንተ ከሰ​ላም ጋር ምን አለህ? ወደ ኋላዬ ተመ​ል​ሰህ ተከ​ተ​ለኝ” አለ።


የሰ​ላ​ምን መን​ገድ አያ​ው​ቋ​ትም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰላ​ሜን፥ ቸር​ነ​ቴ​ንና ምሕ​ረ​ቴን፥ ከዚህ ሕዝብ አስ​ወ​ግ​ጄ​አ​ለ​ሁና ልቅሶ ወዳ​ለ​በት ቤት አት​ግባ፤ ታለ​ቅ​ስና ታዝ​ንም ዘንድ አት​ሂድ።


የሰ​ላ​ምን መን​ገድ አያ​ው​ቁም፤ በመ​ን​ገ​ዳ​ቸ​ውም ፍርድ የለም፤ የሚ​ሄ​ዱ​በ​ትም መን​ገድ ጠማማ ነው፤ ሰላ​ም​ንም አያ​ው​ቁም።


እን​ግ​ዲህ ኃጥ​ኣን ደስታ አያ​ደ​ር​ጉም፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሰላ​ይም ያያ​ቸው ዘንድ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ግንብ ላይ ቆመ፤ ሲመ​ጡም የእ​ነ​ኢ​ዩን አቧራ አየ። “እነ​ሆም፥ አቧራ አያ​ለሁ” አለ። ኢዮ​ራ​ምም፥ “ይገ​ና​ኛ​ቸው ዘንድ አንድ ፈረ​ሰኛ ይሂድ፤ እር​ሱም፦ ሰላም ነውን? ይበ​ላ​ቸው” አለ።


ኢዩም ወደ ከተማ በገባ ጊዜ፥ “ጌታ​ውን የገ​ደለ ዘምሪ ሰላም ነውን?” አለ​ችው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements