2 ነገሥት 8:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)29 ንጉሡም ኢዮራም ከሶርያ ንጉሥ ከአዛሄል ጋር በተዋጋ ጊዜ ሶርያውያን በሬማት ያቈሰሉትን ቍስል ይታከም ዘንድ ወደ ኢይዝራኤል ተመለሰ። የአክዓብም ልጅ ኢዮራም ታምሞ ነበርና የኢዮራም ልጅ አካዝያስ ሊያየው ወደ ኢይዝራኤል ወረደ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም29 ስለዚህ ንጉሥ ኢዮራም፣ ከአዛሄል ጋራ ራማት ላይ ባደረገው ጦርነት ሶርያውያን ካቈሰሉት ቍስል ለመዳን ወደ ኢይዝራኤል ተመለሰ። ከዚያም የአክዓብ ልጅ ኢዮራም ስለ ታመመ፣ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራሆም ልጅ አካዝያስ ሊጠይቀው ወደ ኢይዝራኤል ወረደ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)29 ኢዮራምም ከንጉሥ አዛሄል ጋር ሆኖ በሬማት በተደረገው ጦርነት የደረሰበትን ቁስል ለመፈወስ ወደ ኢይዝራኤል ከተማ ተመለሰ። የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በደረሰበት ጉዳት እርሱን ለመጠየቅ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ ሊጠይቀው ወደ ኢይዝራኤል ከተማ ሄደ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም29 ኢዮራምም ከንጉሥ ኣዛሄል ጋር ሆኖ በሬማት በተደረገው ጦርነት የደረሰበትን ቊስል ለመፈወስ ወደ ኢይዝራኤል ከተማ ተመለሰ። የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በደረሰበት ጒዳት እርሱን ለመጠየቅ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ ሊጠይቀው ወደ ኢይዝራኤል ከተማ ሄደ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)29 ንጉሡም ኢዮራም ከሶርያ ንጉሥ ከአዛሄል ጋር በተዋጋ ጊዜ ሶርያውያን በሬማት ያቈሰሉትን ቈስል ይታከም ዘንድ ወደ ኢይዝራኤል ተመለሰ። የአክዓብም ልጅ ኢዮራም ታምሞ ነበርና የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ ሊያየው ወደ ኢይዝራኤል ወረደ። See the chapter |