Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 6:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 እር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካል​ረ​ዳሽ እኔ እን​ዴት እረ​ዳ​ሻ​ለሁ? ከአ​ው​ድ​ማው ወይስ ከመ​ጭ​መ​ቂ​ያው ነውን?” አለ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ንጉሡም፣ “እግዚአብሔር ካልረዳሽ እኔ እንዴት ልረዳሽ እችላለሁ? ከዐውድማው ነው ወይስ ከወይን መጥመቂያው የምረዳሽ?” ሲል መለሰላት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ንጉሡም “እግዚአብሔር ሊረዳሽ ካልፈቀደ እኔ ምን ዓይነት እርዳታ ልሰጥሽ እችላለሁ? ከአውድማው ወይስ ከወይን መጭመቂያው? ምን ያለኝ ይመስልሻል?

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ንጉሡም “እግዚአብሔር ሊረዳሽ ካልፈቀደ እኔ ምን ዐይነት ርዳታ ልሰጥሽ እችላለሁ? ከአውድማው ወይስ ከወይን መጭመቂያው? ምን ያለኝ ይመስልሻል?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 እርሱም “እግዚአብሔር ያልረዳሽን እኔ እንዴት እረዳሻለሁ? ከአውድማው ወይስ ከመጥመቂያው ነውን?” አለ።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 6:27
11 Cross References  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በሰው የሚ​ታ​መን የሥጋ ክን​ዱ​ንም በእ​ርሱ የሚ​ያ​ስ​ደ​ግፍ፥ ልቡም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ርቅ ሰው ርጉም ነው።


ልባ​ቸው የቈ​ሰ​ለ​ውን ይፈ​ው​ሳል፥ ቍስ​ላ​ቸ​ው​ንም ያደ​ር​ቅ​ላ​ቸ​ዋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ሩት ሁሉ፥ በመ​ን​ገ​ዶ​ቹም የሚ​ሄዱ ብፁ​ዓን ናቸው።


ነፍሴ በኋ​ላህ ተከ​ታ​ተ​ለች፥ እኔ​ንም ቀኝህ ተቀ​በ​ለ​ችኝ።


በኋላ ዘመን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በተ​ራ​ሮች ራስ ላይ ይታ​ያል፤ ከኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ አሕ​ዛ​ቡም ሁሉ ወደ እርሱ ይመ​ጣሉ።


በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወዳ​ለ​ችው ወደ አጣድ አው​ድማ ደረሱ፤ እጅግ ታላቅ በሆነ በጽኑ ልቅ​ሶም አለ​ቀ​ሱ​ለት፤ ለአ​ባ​ቱም ሰባት ቀን ልቅሶ አደ​ረ​ገ​ለት።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በቅ​ጥር ላይ ሲመ​ላ​ለስ አን​ዲት ሴት፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ርዳኝ” ብላ ወደ እርሱ ጮኸች።


ንጉ​ሡም፥ “ምን ሆነ​ሻል?” አላት፤ እር​ስ​ዋም፥ “ይህች ሴት፦ ዛሬ እን​ድ​ን​በ​ላው ልጅ​ሽን አምጪ፤ ነገም ልጄን እን​በ​ላ​ለን አለ​ችኝ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements