Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 6:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ወደ​ዚ​ያም ፈረ​ሶ​ች​ንና ሰረ​ገ​ሎ​ችን ብዙም ጭፍራ ላከ፤ በሌ​ሊ​ትም መጥ​ተው ከተ​ማ​ዪ​ቱን ከበ​ቡ​አት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ስለዚህ ፈረሶችና ሠረገሎች እንዲሁም ብዙ ሰራዊት ወደዚያ ላከ። እነርሱም በሌሊት ደርሰው ከተማዪቱን ከበቡ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ንጉሡ በፈረሶችና በሠረገሎች የተጠናከረ ሠራዊት ወደዚያ ላከ፤ እነርሱም በሌሊት ደርሰው ከተማይቱን ከበቡ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ንጉሡ በፈረሶችና በሠረገሎች የተጠናከረ ሠራዊት ወደዚያ ላከ፤ እነርሱም በሌሊት ደርሰው ከተማይቱን ከበቡ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ወደዚያም ፈረሶችንና ሠረገሎችን እጅግም ጭፍራ ሰደደ፤ በሌሊትም መጥተው ከተማይቱን ከበቡ።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 6:14
10 Cross References  

በዚያን ሰዓት ኢየሱስ ለሕዝቡ “ወንበዴን እንደምትይዙ ሰይፍና ጐመድ ይዛችሁ ልትይዙኝ ወጣችሁን? በመቅደስ ዕለት ዕለት እያስተማርሁ ከእናንተ ጋር ስቀመጥ ሳለሁ አልያዛችሁኝም።


ይህንም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ይሁዳ መጣ፤ ከእርሱም ጋር ብዙ ሕዝብ ሰይፍና ጐመድ ይዘው ከካህናት አለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሎች ዘንድ መጡ።


የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ተር​ታ​ን​ንና ራፌ​ስን ራፋ​ስ​ቂ​ስ​ንም ከብዙ ሠራ​ዊት ጋር ከለ​ኪሶ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ላካ​ቸው። ወጥ​ተ​ውም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ደረሱ፤ በአ​ጣ​ቢ​ውም እርሻ መን​ገድ ባለ​ችው በላ​ዪ​ኛ​ዪቱ ኩሬ መስኖ አጠ​ገብ ቆሙ።


ሳኦ​ልም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ከማ​ሳ​ደድ ከተ​መ​ለሰ በኋላ፥ “እነሆ! ዳዊት በዓ​ይን ጋዲ ምድረ በዳ አለ” ብለው ነገ​ሩት።


ሳኦ​ልና ሰዎ​ቹም በተ​ራ​ራው በአ​ንድ ወገን ሄዱ፤ ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም በተ​ራ​ራው በሌ​ላው ወገን ሄዱ። ዳዊ​ትም ከሳ​ኦል ፊት ያመ​ልጥ ዘንድ ተሰ​ውሮ ነበር። ሳኦ​ልና ሰዎቹ ዳዊ​ት​ንና ሰዎ​ቹን ለመ​ያዝ ከብ​በ​ዋ​ቸው ነበ​ርና።


“ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ጭፍ​ሮች ከብ​በ​ዋት ባያ​ችሁ ጊዜ ጥፋቷ እንደ ደረሰ ዕወቁ።


እር​ሱም፥ “ልኬ አስ​ይ​ዘው ዘንድ ሄዳ​ችሁ ወዴት እንደ ሆነ ዕወቁ፤” አለ። እነ​ር​ሱም፥ “እነሆ፥ በዶ​ታ​ይን አለ” ብለው ነገ​ሩት።


የኤ​ል​ሳ​ዕም ሎሌ ማለዳ ነቃ፤ ተነ​ሥ​ቶም በወጣ ጊዜ፥ እነሆ፥ በከ​ተ​ማ​ዪቱ ዙሪያ ጭፍ​ሮች ከተ​ማ​ዋን ከብ​በ​ዋት አየ። ፈረ​ሶ​ችና ሰረ​ገ​ሎ​ችም ነበሩ። ሎሌ​ውም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ወዮ! ምን እና​ድ​ርግ?” አለው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements