Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 5:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ፦ ደብ​ዳ​ቤ​ውን አደ​ረሰ። ደብ​ዳ​ቤ​ውም እን​ዲህ ይላል፥ “ደብ​ዳ​ቤው ካንተ ዘንድ በደ​ረሰ ጊዜ ባለ​ሟ​ሌን ንዕ​ማ​ንን ወደ አንተ ልኬ​ዋ​ለ​ሁና ከለ​ምጹ ፈው​ሰው።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ለእስራኤልም ንጉሥ የያዘው ደብዳቤ፣ “ከቈዳ በሽታ እንድትፈውሰው ይህን ደብዳቤ አስይዤ አገልጋዬን ንዕማንን ወደ አንተ ልኬዋለሁ” የሚል ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ይዞት የሄደውም መልእክት “ይህ ደብዳቤ የእኔ ሠራዊት አዛዥ ስለ ሆነው ስለ ንዕማን ጉዳይ የሚገልጥ ነው፤ ከቆዳ በሽታ በማንጻት እንድትፈውሰው እፈልጋለሁ” የሚል ነበር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ይዞት የሄደውም መልእክት “ይህ ደብዳቤ የእኔ ሠራዊት አዛዥ ስለ ሆነው ስለ ንዕማን ጉዳይ የሚገልጥ ነው፤ ከቈዳ በሽታ በማንጻት እንድትፈውሰው እፈልጋለሁ” የሚል ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ለእስራኤልም ንጉሥ “ይህች ደብዳቤ ወደ አንተ ስትደርስ ባሪያዬን ንዕማንን ከለምጹ ትፈውሰው ዘንድ እንደ ሰደድሁልህ እወቅ፤” የሚል ደብዳቤ ወሰደ።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 5:6
3 Cross References  

የሶ​ር​ያም ንጉሥ ንዕ​ማ​ንን፥ “ሂድ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ደብ​ዳቤ እል​ካ​ለሁ” አለው። እር​ሱም ሄደ፤ ዐሥ​ርም መክ​ሊት ብር፥ ስድ​ስት ሺህም ወቄት ወርቅ፥ ዐሥ​ርም መለ​ወጫ ልብስ በእጁ ወሰደ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ደብ​ዳ​ቤ​ውን ባነ​በበ ጊዜ ልብ​ሱን ቀድዶ፥ “ሰውን ከለ​ምጹ እፈ​ውስ ዘንድ ይህ ሰው ወደ እኔ መስ​ደዱ እኔ በውኑ ለመ​ግ​ደ​ልና ለማ​ዳን የም​ችል አም​ላክ ነኝን? ተመ​ል​ከቱ፥ የጠብ ምክ​ን​ያት እን​ደ​ሚ​ፈ​ል​ግ​ብኝ ተመ​ል​ከቱ” አለ።


እን​ዲ​ህም አለ፥ “ይህ ደብ​ዳቤ አሁን በደ​ረ​ሳ​ችሁ ጊዜ የጌ​ታ​ችሁ ልጆች ሰረ​ገ​ሎ​ቹና ፈረ​ሶ​ቹም፥ የተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞ​ቹም፥ የጦር መሣ​ሪ​ያ​ዎ​ቹም በእ​ና​ንተ ዘንድ አሉ፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements