Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 4:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ሴት​ዮ​ዋም ለባ​ልዋ፥ “ይህ በእኛ ዘንድ ሁል​ጊዜ የሚ​ያ​ል​ፈው ቅዱስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው እንደ ሆነ አው​ቃ​ለሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ሴቲቱም ባልዋን እንዲህ አለችው፤ “ይህ አዘውትሮ በደጃችን የሚያልፍ ሰው፣ ቅዱስ የእግዚአብሔር ሰው መሆኑን ዐውቃለሁ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እርሷም ባሏን እንዲህ አለችው፤ “ብዙ ጊዜ ወደ ቤታችን የሚመጣው ይህ ሰው የተቀደሰ የእግዚአብሔር ሰው ስለ መሆኑ እርግጠኛ ነኝ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እርስዋም ባልዋን እንዲህ አለችው፤ “ብዙ ጊዜ ወደ ቤታችን የሚመጣው ይህ ሰው የተቀደሰ የእግዚአብሔር ሰው ስለ መሆኑ እርግጠኛ ነኝ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ለባልዋም “ይህ በእኛ ዘንድ ሁልጊዜ የሚያልፈው ቅዱስ የእግዚአብሔር ሰው እንደ ሆነ አውቃለሁ።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 4:9
14 Cross References  

ሴቲ​ቱም ኤል​ያ​ስን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው እንደ ሆንህ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል በአ​ፍህ እው​ነት እንደ ሆነ አሁን ዐወ​ቅሁ” አለ​ችው።


መጥ​ታም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ነገ​ረ​ችው፤ እር​ሱም፥ “ሄደሽ ዘይ​ቱን ሽጭ ዕዳ​ሽ​ንም ክፈዪ፤ በተ​ረ​ፈ​ውም ዘይት የአ​ን​ቺ​ንና የል​ጆ​ች​ሽን ሰው​ነት አድኚ” አላት።


ነገር ግን እንግዳ ተቀባይ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚወድ፥ ጠንቃቃ፥ ጻድቅ፥ ቅዱስ፥ ራሱን የሚገዛ ይሁን፤


በእናንተ በምታምኑ ዘንድ እንዴት ባለ ቅድስናና ጽድቅ ነቀፋም በሌለበት ኑሮ እንደ ሄድን፥ እናንተና እግዚአብሔር ምስክሮች ናችሁ፤


መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።


እር​ስ​ዋም ኤል​ያ​ስን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ሆይ፥ እኔ ከአ​ንተ ጋር ምን አለኝ? አን​ተስ ከእኔ ጋር ምን አለህ? ኀጢ​አ​ቴ​ንስ ታሳ​ስብ ዘንድ፥ ልጄ​ንስ ትገ​ድል ዘንድ ወደ እኔ መጥ​ተ​ሃ​ልን?” አለ​ችው።


እንዲሁም እናንተ ሚስቶች ሆይ! ከባሎቻችሁ አንዳንዱ ለትምህርት የማይታዘዙ ቢኖሩ፥ በፍርሃት ያለውን ንጹሑን ኑሮአችሁን እየተመለከቱ ያለ ትምህርት በሚስቶቻቸው ኑሮ እንዲገኙ ተገዙላቸው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ሙሴ ሳይ​ሞት የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች የባ​ረ​ከ​ባት በረ​ከት ይህች ናት።


ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፤ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።


አንተ ግን የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ከዚህ ሽሽ፤ ጽድቅንና እግዚአብሔርን መምሰል እምነትንም ፍቅርንም መጽናትንም የዋህነትንም ተከታተል።


እነ​ሆም፥ አንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ከይ​ሁዳ ወደ ቤቴል መጣ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም መሥ​ዋ​ዕት ይሠዋ ዘንድ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ ቆሞ ነበር።


አንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ግን ወደ እርሱ መጥቶ፥ “ንጉሥ ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልና ከኤ​ፍ​ሬም ልጆች ሁሉ ጋር አይ​ደ​ለ​ምና የእ​ስ​ራ​ኤል ጭፍራ ከአ​ንተ ጋር አይ​ውጣ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements