2 ነገሥት 4:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)41 ኤልሳዕም፥ “ዶቄት አምጣና በምንቸቱ ውስጥ ጨምረው” አለው፥ ኤልሳዕም ግያዝን፥ “ለሕዝቡ መልስላቸው ይብሉ” አለው። ከዚህም በኋላ በምንቸቱ ውስጥ ክፉ ነገር አልተገኘም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም41 ኤልሳዕም፣ “እስኪ ዱቄት አምጡልኝ” አለ። ያንም በምንቸቱ ውስጥ ጨምሮ፣ “እንዲመገቡት ለሰዎቹ አቅርቡላቸው” አለ። በምንቸቱም ውስጥ ጕዳት የሚያስከትል ነገር አልተገኘም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)41 ኤልሳዕም ዱቄት እንዲሰጡት ጠይቆ በድስቱ ውስጥ ጨመረውና “ወጡን እያወጣህ ጨምርላቸው” ሲል አዘዘ፤ በዚህም ጊዜ በወጡ ውስጥ ምንም ዓይነት መራራነት አልነበረም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም41 ኤልሳዕም ዱቄት እንዲሰጡት ጠይቆ በድስቱ ውስጥ ጨመረውና “ወጡን እያወጣህ ጨምርላቸው” ሲል አዘዘ፤ በዚህም ጊዜ በወጡ ውስጥ ምንም ዐይነት መራራነት አልነበረም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)41 እርሱም “ዱቄት አምጡልኝ፤” አለ፤ በምንቸቱም ውስጥ ጥሎ “ይበሉ ዘንድ ለሕዝቡ ቅዱ፤” አለ። በምንቸቱም ውስጥ ክፉ ነገር አልተገኘም። See the chapter |