Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 4:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ወደ ቤት​ሽም ገብ​ተሽ ከአ​ን​ቺና ከል​ጆ​ችሽ በኋላ በሩን ዝጊ፤ ወደ እነ​ዚ​ህም ማድ​ጋ​ዎች ሁሉ ዘይ​ቱን ገል​ብጪ፤ የሞ​ላ​ው​ንም ፈቀቅ አድ​ርጊ” አላት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ገብተሽም መዝጊያውን በአንቺና በልጆችሽ ላይ የኋሊት ዝጊው፤ ዘይቱንም በማድጋዎቹ ሁሉ ጨምሪ፤ እያንዳንዱ ማድጋ ሲሞላም ወደ አንድ በኩል አኑሪው።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከዚህም በኋላ አንቺና ልጆችሽ ወደ ቤት ገብታችሁ መዝጊያውን ዝጉ፤ የማሰሮውንም ዘይት ወደ ማድጋዎቹ ማንቆርቆር ጀምሩ፤ እያንዳንዱ ማድጋ በሚሞላበት ጊዜ ለብቻው በማግለል አኑሩት።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከዚህም በኋላ አንቺና ልጆችሽ ወደ ቤት ገብታችሁ መዝጊያውን ዝጉ፤ የማሰሮውንም ዘይት ወደ ማድጋዎቹ ማንቈርቈር ጀምሩ፤ እያንዳንዱ ማድጋ በሚሞላበት ጊዜ ለብቻው በማግለል አኑሩት።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ገብተሽም ከአንቺና ከልጆችሽ በኋላ በሩን ዝጊ፤ ወደ እነዚህም ማድጋዎች ሁሉ ዘይቱን ገልብጪ፤ የሞላውንም ፈቀቅ አድርጊ፤” አለ።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 4:4
13 Cross References  

አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ፤ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።


በከ​ሃ​ሊ​ነቱ እንደ ረዳን መጠን፥ የም​ና​ስ​በ​ው​ንና የም​ን​ለ​ም​ነ​ውን ሁሉ ትሠሩ ዘንድ፥ ታበ​ዙም ዘንድ ሊያ​ጸ​ና​ችሁ ለሚ​ችል፥


ጴጥ​ሮ​ስም ሁሉን ካስ​ወጣ በኋላ ተን​በ​ር​ክኮ ጸለየ፤ ወደ በድ​ን​ዋም መለስ ብሎ፥ “ጣቢታ ሆይ፥ ተነሽ” አላት፤ እር​ስ​ዋም ዐይ​ኖ​ች​ዋን ገለ​ጠች፤ ያን​ጊ​ዜም ጴጥ​ሮ​ስን አየ​ችው፤ ቀና ብላም ተቀ​መ​ጠች።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ያን እን​ጀራ ይዞ አመ​ሰ​ገነ፤ ቈር​ሶም ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሰጣ​ቸው፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ለተ​ቀ​መ​ጡት ሰዎች ሰጡ​አ​ቸው፤ ከዓ​ሣ​ውም እን​ዲሁ የፈ​ለ​ጉ​ትን ያህል ሰጡ​አ​ቸው።


በጣምም ሳቁበት። እርሱ ግን ሁሉን አስወጥቶ የብላቴናይቱን አባትና እናት ከእርሱ ጋር የነበሩትንም ይዞ ብላቴናይቱ ወዳለችበት ገባ።


ሕዝቤ ሆይ፥ ና፤ ወደ ቤት​ህም ግባ፤ ደጅ​ህን በኋ​ላህ ዝጋ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቍጣ እስ​ኪ​ያ​ልፍ ድረስ ጥቂት ጊዜ ተሸ​ሸግ።


እር​ሱም፥ “ሂጂና ከጎ​ረ​ቤ​ቶ​ችሽ ሁሉ ከውጭ ባዶ ማድ​ጋ​ዎ​ችን ተዋሺ፤ አታ​ሳ​ን​ሻ​ቸ​ውም።


እን​ዲ​ሁም ከእ​ርሱ ሄዳ፥ በሩን ከእ​ር​ስ​ዋና ከል​ጆ​ችዋ በኋላ ዘጋች፤ እነ​ር​ሱም ማድ​ጋ​ዎ​ቹን ወደ እር​ስዋ ያቀ​ር​ቡ​ላት ነበር፤ እር​ስ​ዋም ትገ​ለ​ብጥ ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements