Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 4:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 አን​ዱም ቅጠላ ቅጠል ያመጣ ዘንድ ወደ ሜዳ ወጣ፤ በም​ድረ በዳ​ውም የወ​ይን ቦታ አገኘ፤ ከዚ​ያም የም​ድር ቅጠላ ቅጠል ሰብ​ሰበ፤ ልብ​ሱ​ንም ሞላ፤ መት​ሮም በወጡ ምን​ቸት ውስጥ ጨመ​ረው፤ አበ​ሰ​ለ​ውም፤ ምን እንደ ሆነ ግን አላ​ወ​ቁም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 ከእነርሱም አንዱ ቅጠላ ቅጠል ለማምጣት ወደ ሜዳ ወጥቶ፤ ዱር በቀል ሐረግ አገኘ፤ ከሐረጉም ላይ የቅል ፍሬ ለቅሞ በልብሱ ሙሉ ይዞ ተመለሰና ቈራርጦ በወጡ ምንቸት ውስጥ ጨመረው፤ ምን እንደ ሆነ ግን ማንም አላወቀም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 ከነቢያቱም አንዱ ጎመን የሚመስል ቅጠላ ቅጠል ለመልቀም ወደ ሜዳ ሔደ፤ እርሱም በዱር ውስጥ የበቀለ የቅል ሐረግ አገኘ፤ መሸከም የሚችለውን ያኽል በርከት ያለ ቅል ቆርጦ አመጣ፤ የዚያንም ምንነት ሳያውቅ ከትፎ ወጡ ውስጥ ጨመረው፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 ከነቢያቱም አንዱ ጎመን የሚመስል ቅጠላ ቅጠል ለመልቀም ወደ ሜዳ ሔደ፤ እርሱም በዱር ውስጥ የበቀለ የቅል ሐረግ አገኘ፤ መሸከም የሚችለውን ያኽል በርከት ያለ ቅል ቈርጦ አመጣ፤ የዚያንም ምንነት ሳያውቅ ከትፎ ወጡ ውስጥ ጨመረው፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 አንዱም ቅጠላቅጠል ያመጣ ዘንድ ወደ ሜዳ ወጣ፤ የምድረ በዳውንም ሐረግ አገኘ፤ ከዚያም የበረሃ ቅል ሰበሰበ፤ ልብሱንም ሞልቶ ተመለሰ፤ መትሮም በወጡ ምንቸት ውስጥ ጨመረው፤ ምን እንደ ሆነ ግን አላወቁም።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 4:39
9 Cross References  

አስ​ተ​ውሉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ጸጋ የሚ​ያ​ቃ​ልል አይ​ኑር፤ ሕማ​ምን የም​ታ​መጣ፥ ብዙ​ዎ​ች​ንም የም​ታ​ስ​ታ​ቸ​ውና የም​ታ​ረ​ክ​ሳ​ቸው መራራ ሥር የም​ት​ገ​ኝ​በ​ትም አይ​ኑር።


እርሱ ግን መልሶ “የሰማዩ አባቴ ያልተከለው ተክል ሁሉ ይነቀላል።


እኔ የተ​መ​ረ​ጠች ወይን፥ ፍጹ​ምም እው​ነ​ተኛ ዘር አድ​ርጌ ተክ​ዬሽ ነበር፤ አንቺ ግን ተለ​ው​ጠሽ እን​ዴት መራራ የእ​ን​ግዳ ወይን ግንድ ሆንሽ?


ለወ​ይኔ ያላ​ደ​ረ​ግ​ሁ​ለት፥ ከዚህ ሌላ አደ​ር​ግ​ለት ዘንድ የሚ​ገ​ባኝ ምን​ድን ነው? ወይ​ንን ያፈ​ራል ብዬ ጠበ​ቅ​ሁት፤ ነገር ግን እሾ​ህን አፈራ።


ለያ​ዕ​ቆ​ብም የም​ስር ንፍሮ ቀቀ​ለ​ች​ለት፤ ዔሳ​ውም ደክሞ ከበ​ረሃ ገባ፤


የቤ​ቱ​ንም ውስጥ በተ​ጐ​በ​ጐ​በና በፈ​ነዳ አበባ፥ በተ​ቀ​ረጸ ዝግባ ለበ​ጠው፤ ሁሉም ዝግባ ነበረ፤ ድን​ጋ​ዩም አል​ታ​የም ነበር።


ኤል​ሳ​ዕም ዳግ​መኛ ወደ ጌል​ጌላ ተመ​ለሰ፤ በም​ድ​ርም ላይ ራብ ነበረ፤ የነ​ቢ​ያ​ትም ልጆች በፊቱ ተቀ​ም​ጠው ነበር፤ ኤል​ሳ​ዕም ሎሌ​ውን፥ “ታላ​ቁን ምን​ቸት ጣድ፤ ለነ​ቢ​ያ​ትም ልጆች ቅጠላ ቅጠል አብ​ስ​ል​ላ​ቸው” አለው።


ከዚ​ህም በኋላ ሰዎቹ ይበሉ ዘንድ አቀ​ረ​በ​ላ​ቸው፤ የበ​ሰ​ለ​ው​ንም ቅጠል በሚ​በ​ሉ​በት ጊዜ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ሆይ፥ በም​ን​ቸቱ ውስጥ መርዝ አለ” ብለው ጮኹ፤ ይበ​ሉም ዘንድ አል​ቻ​ሉም።


ነፍስ ዕውቀት የሌለባት ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ እግሩንም የሚያፈጥን ከመንገድ ይስታል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements