Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 4:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 ሴት​ዮ​ዋም ገብታ በእ​ግሩ አጠ​ገብ ወደ​ቀች በም​ድ​ርም ላይ ሰገ​ደች፤ ልጅ​ዋ​ንም አን​ሥታ ወጣች።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 እርሷም ገብታ በእግሩ ላይ ወደቀች፤ በምድርም ላይ ተደፋች፤ ልጇንም ይዛ ወጣች።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 እርሷም ወደ መሬት ለጥ ብላ በኤልሳዕ ጫማ ላይ በመውደቅ እጅ ነሣች፤ ከዚያም በኋላ ልጇን ይዛ ሄደች።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 እርስዋም ወደ መሬት ለጥ ብላ በኤልሳዕ ጫማ ላይ በመውደቅ እጅ ነሣች፤ ከዚያም በኋላ ልጅዋን ይዛ ሄደች።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 ገብታም በእግሩ አጠገብ ወደቀች፤ በምድርም ላይ ተደፋች፤ ልጅዋንም አንሥታ ወጣች።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 4:37
6 Cross References  

ሴቶ​ችም እንደ ትን​ሣኤ ቀን ተነ​ሥ​ተ​ው​ላ​ቸው ሙታ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ተቀ​በሉ፤ ተፈ​ር​ዶ​ባ​ቸው የሞ​ቱም አሉ፤ የም​ት​በ​ል​ጠ​ውን ሕይ​ወት ያገኙ ዘንድ ሊድኑ አል​ወ​ደ​ዱ​ምና።


ወደ ተራ​ራ​ውም ወደ ኤል​ሳዕ ደርሳ እግ​ሮ​ቹን ጨበ​ጠች፤ ግያ​ዝም ሊያ​ር​ቃት መጣ፤ ኤል​ሳ​ዕም፥ “ነፍ​ስዋ አዝ​ና​ለ​ችና ተዋት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያን ከእኔ ሰው​ሮ​ታል፤ አል​ነ​ገ​ረ​ኝ​ምም” አለ።


በኢ​ያ​ሪ​ኮም የነ​በ​ሩት የነ​ቢ​ያት ልጆች ኤል​ሳዕ ወደ እነ​ርሱ ሲመጣ ባዩት ጊዜ፥ “የኤ​ል​ያስ መን​ፈስ በኤ​ል​ሳዕ ላይ ዐር​ፎ​አል” አሉ። ሊገ​ና​ኙ​ትም መጥ​ተው በፊቱ በም​ድር ላይ ሰገ​ዱ​ለት።


ሴቲ​ቱም ኤል​ያ​ስን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው እንደ ሆንህ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል በአ​ፍህ እው​ነት እንደ ሆነ አሁን ዐወ​ቅሁ” አለ​ችው።


ግያ​ዝ​ንም ጠርቶ፥ “ይህ​ችን ሱማ​ና​ዊት ጥራ” አለው። ጠራ​ትም፤ ወደ እር​ሱም በገ​ባች ጊዜ፥ “ልጅ​ሽን አን​ሥ​ተሽ ውሰጂ” አላት።


ዮሴ​ፍም ከጕ​ል​በቱ ፈቀቅ አደ​ረ​ጋ​ቸው፤ ወደ ምድ​ርም በግ​ን​ባሩ ሰገደ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements