Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 3:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ወደ ይሁ​ዳም ንጉሥ ወደ ኢዮ​ሣ​ፍጥ፥ “የሞ​ዓብ ንጉሥ ከዳኝ፤ ከእኔ ጋር በሞ​ዓብ ላይ ለሰ​ልፍ ትሄ​ዳ​ለ​ህን?” ብሎ፤ ላከ። እር​ሱም፥ “እወ​ጣ​ለሁ፤ እኔ እንደ አንተ፥ አን​ተም እንደ እኔ፥ ሕዝ​ቤም እንደ ሕዝ​ብህ፥ ፈረ​ሶ​ቼም እንደ ፈረ​ሶ​ችህ ናቸው” አለ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ለይሁዳ ንጉሥ ለኢዮሣፍጥ፣ “የሞዓብ ንጉሥ ስለ ዐመፀብኝ ዐብረኸኝ ትዘምታለህን?” ሲል መልእክት ላከበት። እርሱም፣ “አዎን ዐብሬህ እዘምታለሁ፤ እኔ እንደ አንተው ነኝ፤ ሕዝቤ እንደ ሕዝብህ፤ ፈረሶቼም እንደ ፈረሶችህ ናቸው” በማለት መለሰለት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ኢዮሣፍጥም “የሞዓብ ንጉሥ በእኔ ላይ አምፆብኛል፤ በእርሱ ላይ በማደርገው ጦርነት ከእኔ ጋር ትተባበራለህን?” የሚል መልእክት ላከ። ንጉሥ ኢዮሣፍጥም “አዎ እተባበርሃለሁ፤ እኔን እንደ አንተ፥ ሠራዊቴን እንደ ሠራዊትህ፥ ፈረሶቼን እንደ ፈረሶችህ መቁጠር ትችላለህ” ሲል ከመለሰ በኋላ፥

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ኢዮሣፍጥም “የሞአብ ንጉሥ በእኔ ላይ አምፆብኛል፤ በእርሱ ላይ በማደርገው ጦርነት ከእኔ ጋር ትተባበራለህን?” የሚል መልእክት ላከ። ንጉሥ ኢዮሣፍጥም “አዎ እተባበርሃለሁ፤ እኔን እንደ አንተ፥ ሠራዊቴን እንደ ሠራዊትህ፥ ፈረሶቼን እንደ ፈረሶችህ መቊጠር ትችላለህ” ሲል ከመለሰ በኋላ፥

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ወደ ይሁዳም ንጉሥ ወደ ኢዮሣፍጥ “የሞዓብ ንጉሥ ዐምዖብኛልና ከእኔ ጋር በሞዓብ ላይ ለሰልፍ ትሄዳለህን?” ብሎ ላከ። እርሱም “እወጣለሁ፤ እኔ እንደ አንተ፥ ሕዝቤም እንደ ሕዝብህ፥ ፈረሶቼም እንደ ፈረሶችህ ናቸው፤” አለ።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 3:7
12 Cross References  

የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉ​ሥም ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ እን​ዋጋ ዘንድ ከእኔ ጋር ትዘ​ም​ታ​ለ​ህን?” አለው። ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ለእ​ስ​ራ​እል ንጉሥ፥ “እኔ እንደ አንተ፥ ሕዝ​ቤም እንደ ሕዝ​ብህ፥ ፈረ​ሶቼም እንደ ፈረ​ሶ​ችህ ናቸው” አለው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ አክ​ዓብ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “ከእኔ ጋር ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ትሄ​ዳ​ለ​ህን?” አለው። እር​ሱም፥ “እኔ እንደ አንተ ነኝ፤ ሕዝ​ቤም ለሰ​ልፍ እንደ ሕዝ​ብህ ናቸው፤” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


ነቢዩ የአ​ናኒ ልጅ ኢዩ ሊገ​ና​ኘው ወጣ፤ ንጉ​ሡ​ንም ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ታግ​ዛ​ለ​ህን? ወይስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ጠ​ላ​ውን ትወ​ድ​ዳ​ለ​ህን? ስለ​ዚ​ህም ነገር ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ቍጣ መጥ​ቶ​ብ​ሃል።


በዚ​ያም ጊዜ ንጉሡ ኢዮ​ራም ከሰ​ማ​ርያ ወጥቶ እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ቈጠ​ራ​ቸው።


ደግ​ሞም፥ “በየ​ት​ኛው መን​ገድ እን​ሄ​ዳ​ለን?” አለ፤ እር​ሱም፥ “በኤ​ዶ​ም​ያስ ምድረ በዳ መን​ገድ” አለው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉ​ሥና የይ​ሁዳ ንጉሥ፥ የኤ​ዶ​ም​ያ​ስም ንጉሥ ሄዱ፤ የሰ​ባ​ትም ቀን መን​ገድ ዞሩ፤ ለሠ​ራ​ዊ​ቱና ለሚ​ጫኑ እን​ስ​ሶች ውኃ አጡ።


ኤል​ሳ​ዕም ሞተ፤ ቀበ​ሩ​ትም። ከሞ​ዓ​ብም አደጋ ጣዮች በየ​ዓ​መቱ መጀ​መ​ሪያ ወደ ሀገሩ ይገቡ ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements