Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 3:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ አደ​ረገ፤ ነገር ግን እንደ አባ​ቱና እንደ እናቱ አል​ነ​በ​ረም፤ አባ​ቱም ያሠ​ራ​ውን የበ​ዓ​ልን ምስል አጠፋ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እርሱም በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ክፉ ድርጊት ፈጸመ፤ ክፉ ድርጊቱ ግን አባትና እናቱ እንደ ፈጸሙት ዐይነት አልነበረም፤ አባቱ ያሠራውንም የበኣልን ሐውልት አስወገደ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እርሱም ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔርን አሳዘነ፤ ይሁን እንጂ እርሱ የአባቱንና የእናቱን የኤልዛቤልን ያኽል መጥፎ ሰው አልነበረም፤ ባዓል ተብሎ የሚጠራውን ባዕድ አምላክ ለማምለክ አባቱ አሠርቶት የነበረውን ምስል አስወገደ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እርሱም ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔርን አሳዘነ፤ ይሁን እንጂ እርሱ የአባቱንና የእናቱን የኤልዛቤልን ያኽል መጥፎ ሰው አልነበረም፤ ባዓል ተብሎ የሚጠራውን ባዕድ አምላክ ለማምለክ አባቱ አሠርቶት የነበረውን ምስል አስወገደ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ አደረገ፤ ነገር ግን አባቱ ያሠራውን የበኣልን ሐውልት አርቆአልና እንደ አባቱና እንደ እናቱ አልነበረም።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 3:2
14 Cross References  

ኢዩም ሕዝ​ቡን ሁሉ ሰብ​ስቦ፥ “አክ​አብ በዓ​ልን በጥ​ቂቱ አመ​ለ​ከው፤ ኢዩ ግን በብዙ ያመ​ል​ከ​ዋል።


ሌሎች ሠራ​ዊ​ትን እና​መ​ጣ​ል​ሃ​ለን፤ አን​ተም ቀድሞ በሞ​ቱ​ብህ ሠራ​ዊት ምትክ ሹም፤ ፈረ​ሱን በፈ​ረስ ፋንታ፥ ሰረ​ገ​ላ​ውን በሰ​ረ​ገላ ፋንታ ለውጥ፤ በሜ​ዳ​ውም እን​ዋ​ጋ​ቸ​ዋ​ለን፤ ድልም እና​ደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለን።” እር​ሱም ምክ​ራ​ቸ​ውን ሰማ፤ እን​ዲ​ሁም አደ​ረገ።


ለአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸው አት​ስ​ገድ፤ አታ​ም​ል​ካ​ቸ​ውም፤ እንደ ሥራ​ቸ​ውም አት​ሥራ፤ ነገር ግን ፈጽ​መህ አፍ​ር​ሳ​ቸው፤ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሰባ​ብ​ራ​ቸው።


አባቱ ምና​ሴም እን​ዳ​ደ​ረገ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ሠራ።


ልጁ​ንም በእ​ሳት ሠዋ፤ ሞራ ገላ​ጭም ሆነ፤ አስ​ማ​ትም አደ​ረገ፤ መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ች​ንም ሰበ​ሰበ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት እጅግ ክፉ ነገር አደ​ረገ፤ ኣስ​ቈ​ጣ​ውም።


ኢዩም ገብቶ በላ፤ ጠጣም፥ ከዝ​ያም በኋላ፥ “ሂዱ፥ ይህ​ችን የተ​ረ​ገ​መች እዩ​አት፤ የን​ጉሥ ልጅ ናትና ቅበ​ሩ​አት” አለ።


ኢዮ​ራ​ምም ኢዩን ባየ ጊዜ “ኢዩ ሆይ፥ ሰላም ነውን?” አለ። እር​ሱም፥ “የእ​ና​ትህ የኤ​ል​ዛ​ቤል ግል​ሙ​ት​ና​ዋና መተቷ ሲበዛ ምን ሰላም አለ?” ብሎ መለሰ።


ሁሉም እያ​ን​ዳ​ንዱ በፊቱ የነ​በ​ረ​ውን ሰው ገደለ፤ ደጋ​ግ​መ​ውም ገደሉ። ከዚ​ህም በኋላ ሶር​ያ​ው​ያን ሸሹ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው፤ የሶ​ርያ ንጉሥ ወልደ አዴ​ርም በፈ​ጣን ፈረስ አመ​ለጠ።


ስላ​ደ​ረ​ገ​ውም ኀጢ​አት፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ስላ​ሳ​ተ​በት ኀጢ​አት፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አድ​ር​ጎ​አ​ልና፥ በና​ባጥ ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምም መን​ገድ ሄዶ​አ​ልና ሞተ።


ለም​ርኮ ሳስ​ተህ ለምን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ማ​ህም? ለም​ንስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረ​ግህ?”


Follow us:

Advertisements


Advertisements