Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 24:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ከፊቱ አው​ጥቶ እስ​ኪ​ጥ​ላ​ቸው ድረስ ይህ ነገር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በይ​ሁዳ ላይ ሆኖ​አ​ልና፤ ሴዴ​ቅ​ያ​ስም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 እንግዲህ ይህ ሁሉ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ሊደርስ የቻለው ከእግዚአብሔር ቍጣ የተነሣ ነበር፤ በመጨረሻም ከፊቱ አስወገዳቸው። በዚህ ጊዜ ሴዴቅያስ በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 እግዚአብሔር በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሕዝብ ላይ ተቆጥቶ ከፊቱ አስወገዳቸው፤ ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እግዚአብሔር በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሕዝብ ላይ ተቈጥቶ ከፊቱ አስወገዳቸው፤ ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ከፊቱ አውጥቶ እስኪጥላቸው ድረስ ይህ ነገር በእግዚአብሔር ቍጣ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ሆኖአልና፤ ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 24:20
21 Cross References  

ደግ​ሞም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም አም​ሎት በነ​በ​ረው በን​ጉሡ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ላይ ዐመፀ፤ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ይ​መ​ለስ አን​ገ​ቱን አደ​ነ​ደነ፤ ልቡ​ንም አጠ​ነ​ከረ።


እን​ግ​ዲህ ጥበ​በኛ ማን ነው? ጸሓ​ፊስ ማን ነው? ይህን ዓለ​ምስ የሚ​መ​ረ​ም​ረው ማን ነው? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዚ​ህን ዓለም ጥበብ ስን​ፍና አላ​ደ​ረ​ገ​ው​ምን?


በእ​ጃ​ችሁ ሥራ ሁሉ ታስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ ትታ​ች​ሁ​ኛ​ልና፥ ለሌ​ሎች አማ​ል​ክ​ትም ዐጥ​ና​ች​ኋ​ልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነ​ድ​ዳል፥ አይ​ጠ​ፋ​ምም።


ስለ​ዚህ በዚህ የሕግ መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፈ​ውን መር​ገም ሁሉ ያመ​ጣ​ባት ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በዚ​ህች ምድር ነደደ፤


የሐ​ሴ​ቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳ​ል​ፈን ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደም፤ እንደ ዛሬው ሁሉ በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ይሰ​ጠው ዘንድ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈ​ሱን አደ​ን​ድ​ኖ​ታ​ልና፥ ልቡ​ንም አጽ​ን​ቶ​ታ​ልና።


ቃየ​ልም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወጣ፤ በኤ​ዶም አን​ጻር ባለ​ችው ኖድ በም​ት​ባ​ለው ምድ​ርም ኖረ።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​በላ እሳት፥ ቀና​ተ​ኛም አም​ላክ ነውና።


ነገር ግን ምናሴ ስላ​ስ​ቈ​ጣው ነገር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በይ​ሁዳ ላይ ከነ​ደ​ደው ከታ​ላቁ ቍጣው ትኵ​ሳት አል​ተ​መ​ለ​ሰም።


እር​ሱም ሆነ፥ አገ​ል​ጋ​ዮቹ፥ የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ በነ​ቢዩ በኤ​ር​ም​ያስ እጅ የተ​ና​ገ​ረ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ሙም።


ከፊ​ቱም አው​ጥቶ እስ​ኪ​ጥ​ላ​ቸው ድረስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በይ​ሁዳ ላይ ሆኖ​አ​ልና፤ ሴዴ​ቅ​ያ​ስም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።


በእ​ር​ሱም ዘመን የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ወጣ፤ ኢዮ​አ​ቄ​ምም ሦስት ዓመት ተገ​ዛ​ለት፤ ከዚ​ያም በኋላ ዘወር አለና ዐመ​ፀ​በት።


ምና​ሴም ስላ​ደ​ረ​ገው ኀጢ​አት ሁሉ ከፊቱ ያር​ቀው ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በይ​ሁዳ ላይ ሆነ፤


“የሰው ልጅ ሆይ፥ ለአ​ስ​ቈ​ጡኝ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ይህ ትር​ጓሜ ምን እንደ ሆነ አታ​ው​ቁ​ምን? በላ​ቸው። እን​ዲ​ህም ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ እነሆ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጣ፤ ንጉ​ሥ​ዋ​ንና መኳ​ን​ን​ቶ​ች​ዋ​ንም ማረከ፤ ወደ ሀገ​ሩም ወደ ባቢ​ሎን ወሰ​ዳ​ቸው።


ከተ​መ​ረ​ጡት ጫፎ​ች​ዋም በትር እሳት ወጣች፤ ፍሬ​ዋ​ንም በላች፤ የነ​ገ​ሥ​ታ​ትም በትር ይሆን ዘንድ የበ​ረታ በትር የለ​ባ​ትም።” ይህ ሙሾ ነው፤ ለል​ቅ​ሶም ይሆ​ናል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements