Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 23:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ካህ​ና​ቱ​ንም ሁሉ ከይ​ሁዳ ከተ​ሞች አወ​ጣ​ቸው፤ ከጌ​ባ​ልም ጀምሮ እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ ካህ​ናት ያጥ​ኑ​በት የነ​በ​ረ​ውን የኮ​ረ​ብታ መስ​ገጃ ሁሉ ርኩስ አደ​ረ​ገው። በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም በር በግራ በኩል በነ​በ​ረው በከ​ተ​ማ​ዪቱ ሹም በኢ​ያሱ በር መግ​ቢያ አጠ​ገብ የነ​በ​ሩ​ትን የበ​ሮ​ቹን መስ​ገ​ጃ​ዎች አፈ​ረሰ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ኢዮስያስ የቤተ ጣዖት ካህናትን ሁሉ ከይሁዳ ከተማ ወደ ኢየሩሳሌም አወጣቸው፤ ከጌባዕ ጀምሮ እስከ ቤርሳቤህ ድረስ፣ ካህናቱ ዕጣን ያጥኑባቸው የነበሩትን የኰረብታ ማምለኪያ ስፍራዎችን አረከሰ። ከከተማዪቱ በር በስተግራ በኩል፣ በከተማዪቱ ገዥ በኢያሱ በር መግቢያ አጠገብ የነበሩትን የበሮቹን ማምለኪያ ስፍራዎች አፈረሰ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በይሁዳ ከተሞችና በመላ ሀገሪቱ ከገባዕ እስከ ቤርሳቤህ የነበሩትን ካህናት ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣ፤ መሥዋዕት ያቀርቡባቸው የነበሩትን መሠዊያዎች ሁሉ ርኩስ መሆናቸውን ዐወጀ፤ እንዲሁም የከተማይቱ ገዢ ኢያሱ ወደ ከተማይቱ ሲገቡ ከዋናው ቅጽር በር በስተ ግራ በኩል ባሠራው ቅጽር በር አጠገብ የሚገኙትን መስገጃዎች አፈራረሰ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በይሁዳ ከተሞችና በመላ ሀገሪቱ ከገባዕ እስከ ቤርሳቤህ የነበሩትን ካህናት ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣ፤ መሥዋዕት ያቀርቡባቸው የነበሩትን መሠዊያዎች ሁሉ ርኩስ መሆናቸውን ዐወጀ፤ እንዲሁም የከተማይቱ ገዢ ኢያሱ ወደ ከተማይቱ ሲገቡ ከዋናው ቅጽር በር በስተ ግራ በኩል ባሠራው ቅጽር በር አጠገብ የሚገኙትን መስገጃዎች አፈራረሰ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ካህናቱንም ሁሉ ከይሁዳ ከተሞች አወጣቸው፤ ከጌባም ጀምሮ እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ካህናት ያጥኑበት የነበረውን የኮረብታ መስገጃ ሁሉ ርኩስ አደረገው። በከተማይቱም በር በግራ በኩል በነበረው በከተማይቱ ሹም በኢያሱ በር መግቢያ አጠገብ የነበሩትን የበሮቹን መስገጃዎች አፈረሰ።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 23:8
13 Cross References  

ንጉ​ሡም አሳ በይ​ሁዳ ሁሉ ላይ አዋጅ ነገረ፤ ማንም ነጻ አል​ነ​በ​ረም፥ ንጉሡ ባኦ​ስም የሠ​ራ​በ​ትን የራ​ማን ድን​ጋ​ይና እን​ጨት ወሰደ፤ የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ አሳ የብ​ን​ያ​ም​ንና የመ​ሴ​ፋን ኮረ​ብታ ሠራ​በት።


ከብ​ን​ያ​ምም ነገድ ገባ​ዖ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ጋቲ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤


ምድር ሁሉ ከጌባ ጀምሮ በኢየሩሳሌምም ደቡብ በኩል እስካለችው እስከ ሬሞን ድረስ ተለውጣ እንደ ዓረባ ትሆናለች፣ እርስዋም ከፍ ከፍ ትላለች፥ ከብንያምም በር ጀምሮ እስከ ፊተኛው በር ስፍራ እስከ ማዕዘኑ በር ድረስ፥ ከሐናንኤልም ግንብ ጀምሮ እስከ ንጉሡ መጥመቂያ ድረስ በስፍራዋ ትኖራለች።


በቆላ ያል​ፋል፤ ወደ አን​ጋ​ይም በደ​ረሰ ጊዜ ሬማ​ትና የሳ​ኦል ከተማ ገባ​ዖን ይፈ​ራሉ፤


ከብ​ን​ያ​ምም ነገድ ጌባ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ጋሌ​ማ​ት​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን፥ ዓና​ቶ​ት​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን ሰጡ። ከተ​ሞ​ቻ​ቸው ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ።


ኤል​ያ​ስም ፈርቶ ተነሣ፤ ነፍ​ሱ​ንም ሊያ​ድን ሄደ፤ በይ​ሁ​ዳም ወዳ​ለው ወደ ቤር​ሳ​ቤህ መጥቶ ብላ​ቴ​ና​ውን በዚያ ተወ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ወጡ፤ ማኅ​በ​ሩም ከዳን እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ፥ ከገ​ለ​ዓ​ድም ሰዎች ጋር፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መሴፋ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰ​በ​ሰቡ።


ከዚ​ያም ወደ ዐዘ​ቅተ መሐላ ሄደ።


ስለ​ዚ​ህም ያን ጕድ​ጓድ ዐዘ​ቅተ መሐላ ብሎ ጠራው፤ በዚያ እርስ በር​ሳ​ቸው ተማ​ም​ለ​ዋ​ልና።


አብ​ር​ሃ​ምም ማልዶ ተነሣ፤ እን​ጀ​ራ​ንም ወሰደ፤ የውኃ አቍ​ማ​ዳ​ንም ለአ​ጋር በት​ከ​ሻዋ አሸ​ከ​ማት፤ ሕፃ​ኑ​ንም ሰጥቶ አስ​ወ​ጣት፤ እር​ስ​ዋም ሄደች፤ በዐ​ዘ​ቅተ መሐ​ላም በኩል ባለው ምድረ በዳ ተቅ​በ​ዘ​በ​ዘች።


ከእኔ ዘንድ የራቁ፥ እስ​ራ​ኤ​ልም በሳቱ ጊዜ ጣዖ​ታ​ቸ​ውን ተከ​ት​ለው ከእኔ ዘንድ የሳቱ ሌዋ​ው​ያን ሳይ​ቀር ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ይሸ​ከ​ማሉ።


ቃራፋ፥ ቄፍራ፥ ሞኒ፥ ጋባህ፤ ዐሥራ ሁለቱ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።


ነገር ግን ጌል​ገላ ፈጽሞ ትማ​ረ​ካ​ለ​ችና፥ ቤቴ​ልም እን​ዳ​ል​ነ​በ​ረች ትሆ​ና​ለ​ችና ቤቴ​ልን አት​ፈ​ልጉ፤ ወደ ጌል​ገ​ላም አት​ሂዱ፤ ወደ ቤር​ሳ​ቤ​ህም አት​ለፉ።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements