Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 23:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም በድ​ኑን በሰ​ረ​ገ​ላው አድ​ር​ገው ከመ​ጊዶ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አመ​ጡት፤ በመ​ቃ​ብ​ሩም ቀበ​ሩት። የሀ​ገ​ሩም ሰዎች የኢ​ዮ​ስ​ያ​ስን ልጅ ዮአ​ክ​ስን ወሰ​ዱት። ቀብ​ተ​ውም በአ​ባቱ ፋንታ አነ​ገ​ሡት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 የኢዮስያስም አገልጋዮች ከመጊዶ ሬሳውን በሠረገላ ወደ ኢየሩሳሌም አምጥተው በገዛ መቃብሩ ቀበሩት። የአገሩም ሰዎች የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአካዝን ወስደው ቀቡት፤ በአባቱም ምትክ አነገሡት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ባለሟሎቹ የሆኑ ባለሥልጣኖችም ሬሳውን በሠረገላ ወደ ኢየሩሳሌም አምጥተው እዚያ በነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ። የይሁዳም ሰዎችም የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአካዝን መረጡ፤ ቀብተውም አነገሡት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ባለሟሎቹ የሆኑ ባለሥልጣኖችም ሬሳውን በሠረገላ ወደ ኢየሩሳሌም አምጥተው እዚያ በነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ። የይሁዳም ሰዎችም የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአካዝን መረጡ፤ ቀብተውም አነገሡት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ከሞተም በኋላ ባሪያዎቹ በሠረገላው አድርገው ከመጊዶ ወደ ኢየሩሳሌም አመጡት፤ በመቃብሩም ቀበሩት። የአገሩም ሰዎች የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአካዝን ወሰዱት፤ ቀብተውም በአባቱ ፋንታ አነገሡት።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 23:30
11 Cross References  

ብላ​ቴ​ኖ​ቹም በሰ​ረ​ገ​ላው ጭነው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወሰ​ዱት፥ በዳ​ዊ​ትም ከተማ በመ​ቃ​ብሩ ቀበ​ሩት።


ብላ​ቴ​ኖ​ቹም ከሰ​ረ​ገ​ላው አው​ር​ደው ለእ​ርሱ በነ​በ​ረው በሁ​ለ​ተ​ኛው ሰረ​ገላ ውስጥ አስ​ቀ​መ​ጡት፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አመ​ጡት፤ እር​ሱም በዚያ ሞተ፤ በአ​ባ​ቶ​ቹም መቃ​ብር ተቀ​በረ፤ ይሁ​ዳና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሁሉ ለኢ​ዮ​ስ​ያስ አለ​ቀሱ።


የሀ​ገሩ ሕዝብ ግን በን​ጉሡ በአ​ሞጽ ላይ ያሴ​ሩ​ትን ሁሉ ገደሉ፤ የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ ልጁን ኢዮ​ስ​ያ​ስን በእ​ርሱ ፋንታ አነ​ገ​ሡት።


የይ​ሁ​ዳም ሕዝብ ሁሉ የዐ​ሥራ ስድ​ስት ዓመት ልጅ የነ​በ​ረ​ውን ዓዛ​ር​ያ​ስን ወስ​ደው በአ​ባቱ በአ​ሜ​ስ​ያስ ፋንታ አነ​ገ​ሡት።


ነገሩ እን​ደ​ዚህ አይ​ደ​ለም፤ ወደ አባ​ቶ​ችህ እሰ​በ​ስ​ብ​ሃ​ለሁ፥ በሰ​ላ​ምም ወደ መቃ​ብ​ርህ ትሰ​በ​ሰ​ባ​ለህ፤ በዚ​ህም ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ የማ​መ​ጣ​ውን ክፉ ነገር ዐይ​ኖ​ችህ አያ​ዩም።” ይህ​ንም ለን​ጉሡ ነገ​ሩት።


ከዚ​ህም ሁሉ በኋላ፥ ኢዮ​ስ​ያ​ስም ቤተ መቅ​ደ​ሱን ካሰ​ናዳ በኋላ፥ የግ​ብጽ ንጉሥ ፈር​ዖን ኒካዑ በኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ አጠ​ገብ የአ​ሦ​ርን ንጉሥ ይዋጋ ዘንድ ወጣ፤ ኢዮ​ስ​ያ​ስም ሊጋ​ጠ​መው ወጣ።


በአ​ባቱ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ፋንታ ስለ ነገ​ሠው፥ ከዚ​ህም ስፍራ ስለ ወጣ​ውና ስለ​ማ​ይ​መ​ለ​ሰው ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮ​ስ​ያስ ልጅ፥ ስለ ሳሌም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦


“አን​ተም ለእ​ስ​ራ​ኤል አለቃ ይህን ሙሾ አሙ​ሽ​ለት፤


ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አይ​መ​ለ​ስ​ምና፥ የተ​ወ​ለ​ደ​ባ​ት​ንም ሀገር አያ​ይ​ምና ለሚ​ወጣ እጅግ አል​ቅሱ እንጂ ለሞተ አታ​ል​ቅሱ፤ አት​ዘ​ኑ​ለ​ትም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements