Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 22:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የይ​ሁዳ ንጉሥ እን​ዳ​ነ​በ​በው እን​ደ​ዚህ መጽ​ሐፍ ቃል ሁሉ በዚህ ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ ክፉ ነገር አመ​ጣ​ለሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የይሁዳ ንጉሥ ባነበበው መጽሐፍ የተጻፈውን ክፉ ነገር ሁሉ በዚህ ስፍራና በነዋሪዎቹ ላይ አመጣለሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 “እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ የይሁዳ ንጉሥ ባነበበው መጽሐፍ ውስጥ በተጻፈው መሠረት በዚህች ቦታና በሕዝብዋ ላይ ክፉ ነገርን አመጣለሁ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 “እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ የይሁዳ ንጉሥ ባነበበው መጽሐፍ ውስጥ በተጻፈው መሠረት በዚህች ቦታና በሕዝብዋ ላይ ክፉ ነገርን አመጣለሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘እነሆ፥ የይሁዳ ንጉሥ እንዳነበበው እንደ መጽሐፉ ቃል ሁሉ በዚህ ስፍራና በሚኖሩበት ላይ ክፉ ነገር አመጣለሁ።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 22:16
18 Cross References  

አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረው መል​ካም ነገር ሁሉ እንደ ደረ​ሰ​ላ​ችሁ፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ጣ​ችሁ ከዚ​ህች ከመ​ል​ካ​ሚቱ ምድር እና​ን​ተን እስ​ኪ​ያ​ጠ​ፋ​ችሁ ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲሁ ክፉን ነገር ሁሉ ያመ​ጣ​ባ​ች​ኋል።


እነሆ፥ በቤ​ትህ ያለው ሁሉ፥ አባ​ቶ​ች​ህም እስከ ዛሬ ያከ​ማ​ቹት ሁሉ ወደ ባቢ​ሎን የሚ​ፈ​ል​ስ​በት ወራት ይመ​ጣል፤ ምንም አይ​ቀ​ርም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ጣ​ችሁ ከዚ​ህች ከመ​ል​ካ​ሚቱ ምድር እስ​ክ​ት​ጠፉ ድረስ መው​ደ​ቂ​ያና ወጥ​መድ፥ በእ​ግ​ራ​ች​ሁም ችን​ካር፥ በዐ​ይ​ና​ች​ሁም እሾህ ይሆ​ኑ​ባ​ች​ኋል እንጂ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ እነ​ዚ​ህን አሕ​ዛብ ከፊ​ታ​ችሁ እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው ራሳ​ችሁ ዕወቁ።


ስለ​ዚህ በዚህ የሕግ መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፈ​ውን መር​ገም ሁሉ ያመ​ጣ​ባት ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በዚ​ህች ምድር ነደደ፤


እር​ስ​ዋም አለ​ቻ​ቸው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ወደ እኔ ለላ​ካ​ችሁ ሰው እን​ዲህ ብላ​ችሁ ንገ​ሩት፦


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ሊያ​መ​ል​ጡት የማ​ይ​ች​ሉ​ትን ክፉ ነገር በዚህ ሕዝብ ላይ አመ​ጣ​ለሁ፤ ወደ እኔም ይጮ​ኻሉ፤ እኔ ግን አል​ሰ​ማ​ቸ​ውም።


ሳሙ​ኤ​ልም አደገ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ነበረ፤ ከቃ​ሉም አን​ዳች በም​ድር ላይ አይ​ወ​ድ​ቅም ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን አደጋ ጣዮች፥ የሶ​ር​ያ​ው​ያ​ን​ንም አደጋ ጣዮች፥ የሞ​ዓ​ባ​ው​ያ​ን​ንም አደጋ ጣዮች፥ የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች አደጋ ጣዮች ሰደ​ደ​በት፤ በባ​ሪ​ያ​ዎቹ በነ​ቢ​ያት ቃል እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ያጠ​ፉት ዘንድ በይ​ሁዳ ላይ ሰደ​ዳ​ቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements