Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 21:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 “የይ​ሁዳ ንጉሥ ምናሴ ከእ​ርሱ በፊት የነ​በሩ አሞ​ራ​ው​ያን ከሠ​ሩት ሁሉ ይልቅ ይህን ክፉ ርኵ​ሰት አድ​ር​ጎ​አ​ልና፥ ይሁ​ዳ​ንም ደግሞ በጣ​ዖ​ታቱ አስ​ቶ​አ​ልና፥

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 “የይሁዳ ንጉሥ ምናሴ ይህን ሁሉ አስጸያፊ ኀጢአት ሠርቷል፤ ከርሱ በፊት ከነበሩት አሞራውያን ይልቅ ክፉ ድርጊት ፈጽሟል፤ ይሁዳንም በጣዖታቱ አስቷል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 “የይሁዳ ንጉሥ ምናሴ ይህን ሁሉ አሳፋሪ ነገር አደረገ፤ ይኸውም ቀድሞ ከነዓናውያን ይፈጽሙት ከነበረው ሁሉ የከፋ ነው፤ በሠራቸውም ጣዖቶች የይሁዳን ሕዝብ ወደ ኃጢአት መራ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 “የይሁዳ ንጉሥ ምናሴ ይህን ሁሉ አሳፋሪ ነገር አደረገ፤ ይኸውም ቀድሞ ከነዓናውያን ይፈጽሙት ከነበረው ሁሉ የከፋ ነው፤ በሠራቸውም ጣዖቶች የይሁዳን ሕዝብ ወደ ኃጢአት መራ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 “የይሁዳ ንጉሥ ምናሴ ይህን ርኵሰት አድርጎአልና፥ ከፊቱም የነበሩ አሞራውያን ከሠሩት ሁሉ ይልቅ ክፉ ሥራ ሠርቶአልና፥ ይሁዳንም ደግሞ በጣዖታቱ አስቶአልና

See the chapter Copy




2 ነገሥት 21:11
21 Cross References  

ከዚ​ህም በኋላ በዓ​መቱ ወልደ አዴር ሶር​ያ​ው​ያ​ንን ቈጠ​ራ​ቸው፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጋር ይዋጋ ዘንድ ወደ አፌቅ ወጣ።


ነገር ግን አል​ሰ​ሙም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ካጠ​ፋ​ቸው ከአ​ሕ​ዛብ ይልቅ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይ​ኖች ፊት ክፉ ይሠሩ ዘንድ ምናሴ አሳ​ታ​ቸው።


የይ​ሁዳ ንጉሥ የሕ​ዝ​ቅ​ያስ ልጅ ምናሴ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ስለ አደ​ረ​ገው ሁሉ በም​ድር መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ መካ​ከል ለመ​ከራ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።


አንቺ ባል​ዋ​ንና ልጆ​ች​ዋን የጠ​ላች የእ​ና​ትሽ ልጅ ነሽ፤ አን​ቺም ባሎ​ቻ​ቸ​ው​ንና ልጆ​ቻ​ቸ​ውን የጠሉ የእ​ኅ​ቶ​ችሽ እኅት ነሽ፤ እና​ታ​ችሁ ኬጢ​ያ​ዊት ነበ​ረች፤ አባ​ታ​ች​ሁም አሞ​ራዊ ነበረ።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ዲህ ይላል፦ ዘር​ሽና ትው​ል​ድሽ ከከ​ነ​ዓን ምድር ነው፤ አባ​ትሽ አሞ​ራዊ ነበረ፤ እና​ት​ሽም ኬጢ​ያ​ዊት ነበ​ረች።


አባ​ቱም በሄ​ደ​በት መን​ገድ ሁሉ ሄደ፤ አባ​ቱም ያመ​ለ​ካ​ቸ​ውን ጣዖ​ታት አመ​ለከ፥ ሰገ​ደ​ላ​ቸ​ውም።


ደግ​ሞም ምናሴ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይ​ኖች ፊት ክፉ ይሠራ ዘንድ ይሁ​ዳን ካሳ​ተ​በት ኀጢ​አት ሌላ ከዳር እስከ ዳር ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን እስ​ኪ​ሞ​ላት ድረስ እጅግ ብዙ ንጹሕ ደምን አፈ​ሰሰ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት እን​ዳ​ራ​ቃ​ቸው እንደ አሕ​ዛብ ርኵ​ሰት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነገ​ርን አደ​ረገ።


ስላ​ደ​ረ​ገ​ውም ኀጢ​አት፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ስላ​ሳ​ተ​በት ኀጢ​አት፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አድ​ር​ጎ​አ​ልና፥ በና​ባጥ ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምም መን​ገድ ሄዶ​አ​ልና ሞተ።


ይኸ​ውም ኢዮ​ር​ብ​ዓም ስለ ሠራው ኀጢ​አት፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ስላ​ሳ​ተ​በት፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስላ​ስ​ቈ​ጣ​በት ማስ​ቈ​ጣት ነው።


ስለ በደ​ለ​ውና እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ስላ​ሳ​ተ​በት ስለ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት እስ​ራ​ኤ​ልን ይጥ​ላል።”


በአ​ራ​ተ​ኛው ትው​ልድ ግን ወደ​ዚህ ይመ​ለ​ሳሉ፤ እስከ ዛሬ ድረስ የአ​ሞ​ራ​ው​ያን ኀጢ​አት አል​ተ​ፈ​ጸ​መ​ምና።”


ነገር ግን በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት መን​ገድ ሄደ፤ ደግ​ሞም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት እን​ዳ​ሳ​ደ​ዳ​ቸው እንደ አሕ​ዛብ ርኵ​ሰት ልጁን በእ​ሳት ሠዋው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በባ​ሪ​ያ​ዎቹ በነ​ቢ​ያት ቃል እን​ዲህ ሲል ተና​ገረ፦


አባቱ ምና​ሴም እን​ዳ​ደ​ረገ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ሠራ።


ደግ​ሞም ካህኑ ኬል​ቅ​ያስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ባገ​ኘው መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፈ​ውን የሕ​ጉን ቃል ያጸና ዘንድ፥ መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ቹ​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ቹን ተራ​ፊ​ም​ንና ጣዖ​ታ​ት​ንም በይ​ሁዳ ሀገ​ርና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የተ​ገ​ኘ​ውን ርኵ​ሰት ሁሉ ኢዮ​ስ​ያስ አስ​ወ​ገደ።


ድሀ​ው​ንና ችግ​ረ​ኛ​ውን ቢያ​ስ​ጨ​ንቅ፥ ቢቀ​ማም፥ መያ​ዣ​ው​ንም ባይ​መ​ልስ፥ ዐይ​ኖ​ቹ​ንም ወደ ጣዖ​ታት ቢያ​ነሣ፥ ርኩ​ስ​ንም ነገር ቢያ​ደ​ርግ፥


ኤያ​ቡ​ሴ​ዎ​ንን፥ አሞ​ሬ​ዎ​ንን፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ንን፥


እር​ስ​ዋም ከአ​ሕ​ዛብ ይልቅ ፍር​ዴን በኀ​ጢ​አት ለወ​ጠች፤ በዙ​ሪ​ያ​ዋም ከአሉ ሀገ​ሮች ሁሉ ይልቅ ትእ​ዛ​ዜን ተላ​ለ​ፈች፤ ፍር​ዴን ጥለ​ዋ​ልና፥ በት​እ​ዛ​ዜም አል​ሄ​ዱ​ምና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements