Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 20:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ነቢ​ዩም ኢሳ​ይ​ያስ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ፤ ጥላ​ውም ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ተመ​ለሰ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ከዚያም ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፤ እግዚአብሔርም አካዝ በሠራው ደረጃ ላይ የወረደውን ጥላ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላው እንዲመለስ አደረገ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ኢሳይያስም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም ንጉሥ አካዝ ባሠራው ደረጃ ላይ ያረፈው ጥላ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደረገ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ኢሳይያስም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም ንጉሥ አካዝ ባሠራው ደረጃ ላይ ያረፈው ጥላ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደረገ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ነቢዩ ኢሳይያስም ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፤ ጥላውንም በአካዝ የጥላ ስፍራ ሰዓት ላይ በወረደበት መንገድ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ መለሰው።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 20:11
9 Cross References  

እነሆ፥ በአ​ባ​ትህ የጥላ ስፍረ ሰዓት ላይ ከፀ​ሐይ ጋራ የወ​ረ​ደ​ውን በደ​ረ​ጃ​ዎች ያለ​ውን ጥላ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እን​ዲ​መ​ለስ አደ​ር​ጋ​ለሁ።” ፀሐ​ይም በጥላ ስፍረ ሰዓት ላይ የወ​ረ​ደ​በት ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ተመ​ለሰ።


በዚ​ያም ወራት ሕዝ​ቅ​ያስ እስከ ሞት ድረስ ታመመ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸለየ፤ እር​ሱም ሰማው፤ ምል​ክ​ትም ሰጠው።


ጴጥ​ሮ​ስም ሁሉን ካስ​ወጣ በኋላ ተን​በ​ር​ክኮ ጸለየ፤ ወደ በድ​ን​ዋም መለስ ብሎ፥ “ጣቢታ ሆይ፥ ተነሽ” አላት፤ እር​ስ​ዋም ዐይ​ኖ​ች​ዋን ገለ​ጠች፤ ያን​ጊ​ዜም ጴጥ​ሮ​ስን አየ​ችው፤ ቀና ብላም ተቀ​መ​ጠች።


ነገር ግን የባ​ቢ​ሎን መሳ​ፍ​ንት መል​እ​ክ​ተ​ኞች በሀ​ገሩ ላይ ስለ ተደ​ረ​ገው ተአ​ም​ራት ይጠ​ይ​ቁት ዘንድ ወደ እርሱ በተ​ላኩ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ት​ነ​ውና በልቡ ያለ​ውን ሁሉ ያውቅ ዘንድ ተወው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ለምን ትጮ​ኽ​ብ​ኛ​ለህ? ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን እን​ዲ​ነዱ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ንገር።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ኢሳ​ይ​ያ​ስን፥ “ጥላው ዐሥር ደረጃ ቢጨ​ምር ቀላል ነገር ነው፤ እን​ዲህ አይ​ሁን፤ ነገር ግን ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ይመ​ለሰ” አለው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements