2 ነገሥት 2:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 ውኃው ወዳለበትም ምንጭ ወጥቶ ጨው ጣለበትና፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህን ውኃ ፈውሼዋለሁ፤ ከዚህም በኋላ የሚሞት፥ የሚመክንም አይኖርም” አለ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም21 ከዚያም ወደ ውሃው ምንጭ ሄዶ ጨው ጣለበትና “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ይህን ውሃ ፈውሼዋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ለሞት ምክንያት አይሆንም፤ ምድሪቱንም ፍሬ እንዳትሰጥ አያደርጋትም’ አለ።” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 እርሱም ወደ ምንጩ ሄዶ ጨውን በውሃው ውስጥ በመጨመር፥ “እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው ‘እኔ ይህን ውሃ በመፈወስ ንጹሕ እንዲሆን አደርጋለሁ፤ ከዚህም በኋላ ዳግመኛ የሞትና የምርት አልባነት ምክንያት አይሆንም’” ሲል ተናገረ፤ See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 እርሱም ወደ ምንጩ ሄዶ ጨውን በውሃው ውስጥ በመጨመር፥ “እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው ‘እኔ ይህን ውሃ በመፈወስ ንጹሕ እንዲሆን አደርጋለሁ፤ ከዚህም በኋላ ዳግመኛ የሞትና የምርት አልባነት ምክንያት አይሆንም’ ” ሲል ተናገረ፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 ውሃውም ወዳለበት ምንጭ ወጥቶ ጨው ጣለበትና “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘ይህን ውሃ ፈውሼዋለሁ፤ ከዚህም በኋላ ሞትና ጭንገፋ አይሆንበትም፤’” አለ። See the chapter |