Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 19:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 አቤቱ፥ በእ​ው​ነት የአ​ሦር ነገ​ሥት አሕ​ዛ​ብን አጥ​ፍ​ተ​ዋል፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “እግዚአብሔር ሆይ፤ የአሦር ነገሥታት እውነትም እነዚህን አሕዛብንና ምድራቸውን አጥፍተዋል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እግዚአብሔር ሆይ፥ የአሦር ነገሥታት ብዙ ሕዝቦችና ምድራቸውን መደምሰሳቸው እርግጥ ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እግዚአብሔር ሆይ፥ የአሦር ነገሥታት ብዙ ሕዝቦችና ምድራቸውን መደምሰሳቸው እርግጥ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 አቤቱ፥ በእውነት የአሦር ነገሥታት አሕዛብንና ምድራቸውን አፍርሰዋል፤

See the chapter Copy




2 ነገሥት 19:17
19 Cross References  

በል​ባ​ቸው የደ​በ​ቁ​ትም ይገ​ለ​ጣል፤ ከዚህ በኋላ ያ የማ​ያ​ም​ነው ተመ​ልሶ ይጸ​ጸ​ታል፤ በግ​ን​ባ​ሩም ወድቆ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰ​ግ​ዳል፥ በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር እን​ዳ​ለም ይና​ገ​ራል።


በቀ​ባ​ኸው በቅ​ዱስ ልጅህ ላይ ሄሮ​ድ​ስና ጰን​ጤ​ና​ዊው ጲላ​ጦስ ከወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸ​ውና ከእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ጋር በእ​ው​ነት በዚች ሀገር ላይ ዶለቱ።


አን​ዲት ሰዓት ያህ​ልም ቈይቶ አንድ ሌላ ሰው፥ “ይህም በእ​ው​ነት ከእ​ርሱ ጋር ነበረ፤ ሰው​የ​ውም የገ​ሊላ ሰው ነው” ብሎ አስ​ጨ​ነ​ቀው።


ነገር ግን ይህን ቃል ሁሉ በጆ​ሮ​አ​ችሁ እና​ገር ዘንድ በእ​ው​ነቱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ እና​ንተ ልኮ​ኛ​ልና ብት​ገ​ድ​ሉኝ ንጹሕ ደምን በራ​ሳ​ች​ሁና በዚች ከተማ፥ በሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትም ላይ እን​ድ​ታ​መጡ በር​ግጥ ዕወቁ።”


ይህ በሠ​ራ​ዊት ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጆሮ ተሰ​ም​ቶ​አ​ልና፦ ቤቶች ቢሠሩ ባድማ ይሆ​ናሉ፤ ታላ​ላ​ቅና የሚ​ያ​ምሩ ቤቶ​ችም የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸው አይ​ኖ​ርም።


“በእ​ው​ነት እን​ዲህ እንደ ሆነ ዐወ​ቅሁ፤ ሰውስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ጻድቅ መሆን እን​ዴት ይች​ላል?


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ የአ​ሦ​ርን ንጉሥ የፋ​ሎ​ክን መን​ፈስ፥ የአ​ሦ​ር​ንም ንጉሥ የቴ​ል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶ​ርን መን​ፈስ አስ​ነሣ፤ የሮ​ቤ​ል​ንና የጋ​ድን ልጆች የም​ና​ሴ​ንም ነገድ እኩ​ሌታ አፈ​ለሰ፥ እስከ ዛሬም ወዳ​ሉ​በት ወደ አላ​ሔና ወደ ኦቦር፥ ወደ ሃራ​ንና ወደ ጎዛን ወንዝ አመ​ጣ​ቸው።


የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ከባ​ቢ​ሎ​ንና ከኩታ፥ ከአ​ዋና ከሐ​ማት፥ ከሴ​ፌ​ር​ዋ​ይም ሰዎ​ችን አመጣ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ፋንታ በሰ​ማ​ርያ ከተ​ሞች አኖ​ራ​ቸው፤ ሰማ​ር​ያ​ንም ወረ​ሱ​አት፤ በከ​ተ​ሞ​ች​ዋም ተቀ​መጡ።


በሆ​ሴ​ዕም በዘ​ጠ​ነ​ኛው ዓመት የአ​ሦር ንጉሥ ሰማ​ር​ያን ያዘ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ወደ አሶር አፈ​ለሰ፤ በአ​ላ​ሔና በአ​ቦር፤ በጎ​ዛ​ንም ወንዝ፤ በሜ​ዶ​ንም ከተ​ሞች አኖ​ራ​ቸው።


የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ሰማው፤ የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ወደ ደማ​ስቆ ወጣ፤ ያዛ​ትም፤ ሕዝ​ብ​ዋ​ንም ወደ ቂር አፈ​ለ​ሳ​ቸው፤ ረአ​ሶ​ን​ንም ገደ​ለው።


በታንኳይቱም የነበሩት “በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤” ብለው ሰገዱለት።


አቤቱ፥ ጆሮ​ህን አዘ​ን​ብ​ልና ስማ፥ አቤቱ፥ ዐይ​ን​ህን ክፈ​ትና እይ፤ በሕ​ያው አም​ላክ ላይ ይገ​ዳ​ደር ዘንድ የላ​ከ​ውን የሰ​ና​ክ​ሬ​ምን ቃል ስማ።


አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ላይ ጥለ​ዋል፤ የእ​ን​ጨ​ትና የድ​ን​ጋይ የሰው እጅ ሥራ ነበሩ እንጂ አማ​ል​ክት አል​ነ​በ​ሩ​ምና፤ ስለ​ዚህ አጥ​ፍ​ተ​ዋ​ቸ​ዋል።


በአ​ም​ላ​ኩም በሲ​ድ​ራክ ቤት ሲሰ​ግድ ልጆቹ አድ​ራ​ሜ​ሌ​ክና ሶር​ሶር በሰ​ይፍ ገደ​ሉት፤ ወደ አራ​ራ​ትም ሀገር ኰበ​ለሉ። ልጁም አስ​ራ​ዶን በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።


የአ​ክ​ዓ​ብን ቤት ሁሉ ታጠ​ፋ​ለህ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ አጥር ተጠ​ግቶ እስ​ከ​ሚ​ሸን የቀ​ረ​በ​ውን ሁሉና ከእ​ነ​ርሱ የቀ​ረ​ውን ሁሉ ታጠ​ፋ​ለህ።


በውኑ የአ​ሕ​ዛብ አማ​ል​ክት አገ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ከአ​ሦር ንጉሥ እጅ አድ​ነ​ዋ​ቸ​ዋ​ልን?


Follow us:

Advertisements


Advertisements