Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 18:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 አሁን በውኑ ያለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ይህን ስፍራ እና​ጠፋ ዘንድ ወጥ​ተ​ና​ልን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ወደ​ዚች ሀገር ወጥ​ታ​ችሁ አጥ​ፉ​አት አለን።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 በተጨማሪም አደጋ ጥዬ ይህችን ስፍራ ለማጥቃትና ለማጥፋት የመጣሁት፣ ያለ እግዚአብሔር ይመስልሃል? በዚህች አገር ላይ ዘምቼ እንዳጠፋት የነገረኝ ራሱ እግዚአብሔር ነው።’ ”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 እኔ በአንተ አገር ላይ አደጋ የጣልኩባትና የደመሰስኳት ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ይመስልሃልን? እግዚአብሔር ራሱ በዚህች አገር ላይ አደጋ እንድጥልባትና እንድደመስሳት አዞኛል።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 እኔ በአንተ አገር ላይ አደጋ የጣልኩባትና የደመሰስኳት ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ይመስልሃልን? እግዚአብሔር ራሱ በዚህች አገር ላይ አደጋ እንድጥልባትና እንድደመስሳት አዞኛል።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 አሁን በውኑ ያለ እግዚአብሔር ትእዛዝ ይህን ስፍራ አጠፋ ዘንድ ወጥቻለሁን? እግዚአብሔር ‘ወደዚች አገር ወጥተህ አጥፋት፤’ አለኝ።”

See the chapter Copy




2 ነገሥት 18:25
10 Cross References  

ኢሳ​ይ​ያ​ስም አላ​ቸው፥ “ለጌ​ታ​ችሁ እን​ዲህ በሉት፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የአ​ሦር ንጉሥ ብላ​ቴ​ኖች ስለ ተሳ​ደ​ቡት፥ ስለ ሰማ​ኸው ቃል አት​ፍራ።


ወይስ በከ​ተማ ውስጥ መለ​ከት ሲነፋ ሕዝቡ አይ​ደ​ነ​ግ​ጡ​ምን? ወይስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያላ​ዘ​ዘው ክፉ ነገር በከ​ተማ ላይ ይመ​ጣ​ልን?


እር​ሱም፥ “የይ​ሁዳ ንጉሥ ሆይ፥ ከአ​ንተ ጋር ምን አለኝ? በም​ዋ​ጋ​በት በሌላ ቤት ላይ ነው እንጂ በአ​ንተ ላይ ዛሬ አል​መ​ጣ​ሁም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ድ​ቸ​ኩል አዝ​ዞ​ኛል፤ ከእኔ ጋር ያለው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋህ ተጠ​ን​ቀቅ” ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ​በት።


እር​ሱም፥ “እኔ ደግሞ እን​ዳ​ንተ ነቢይ ነኝ፤ መል​አ​ክም፦ እን​ጀራ ይበላ ዘንድ ውኃም ይጠጣ ዘንድ ከአ​ንተ ጋር ወደ ቤትህ መል​ሰው ብሎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ተና​ገ​ረኝ” አለው። ዋሽ​ቶም ተና​ገ​ረው።


ስለ ሰረ​ገ​ሎ​ችና ስለ ፈረ​ሶች በግ​ብፅ ስት​ታ​መን፥ ከጌ​ታዬ አገ​ል​ጋ​ዮች የሚ​ያ​ን​ሰ​ውን የአ​ን​ዱን አለቃ ፊት ትመ​ልስ ዘንድ እን​ዴት ይቻ​ል​ሃል?


የኬ​ል​ቅ​ዩም ልጅ ኤል​ያ​ቄም ሳም​ና​ስም ዮአ​ስም ራፋ​ስ​ቂ​ስን፥ “እኛ እን​ሰ​ማ​ለ​ንና በሱ​ር​ስት ቋንቋ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ተና​ገር፤ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስ​ጥም ቋንቋ አት​ና​ገ​ረን፤ በቅ​ጥ​ርም ላይ ያለው ሕዝብ በሚ​ሰ​ማው ቋንቋ ለምን ትና​ገ​ራ​ለህ?” አሉት።


ምና​ሴም ስላ​ደ​ረ​ገው ኀጢ​አት ሁሉ ከፊቱ ያር​ቀው ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በይ​ሁዳ ላይ ሆነ፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements