Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 17:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ እን​ዲ​ህም ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው፤ አት​ስ​ገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፤ አታ​ም​ል​ኩ​አ​ቸ​ውም፤ አት​ሠ​ዉ​ላ​ቸ​ውም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 እግዚአብሔር ከእስራኤላውያን ጋራ ኪዳን ሲገባ እንዲህ ሲል አዝዟቸው ነበር፤ “ሌሎችን አማልክት አትፍሯቸው፤ አትስገዱላቸው፤ አታገልግሏቸው፤ አትሠዉላቸውም፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን በመግባት እስራኤላውያንን እንዲህ ሲል አዞአቸው ነበር፤ “ባዕዳን አማልክትን አታምልኩ፤ ለእነርሱም አገልጋዮች በመሆን አትስገዱላቸው፤ መሥዋዕትንም አታቅርቡላቸው፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን በመግባት እስራኤላውያንን እንዲህ ሲል አዞአቸው ነበር፤ “ባዕዳን አማልክትን አታምልኩ፤ ለእነርሱም አገልጋዮች በመሆን አትስገዱላቸው፤ መሥዋዕትንም አታቅርቡላቸው፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፤ እንዲህም ብሎ አዘዛቸው “ሌሎች አማልክትን አትፍሩ፤ አትስገዱላቸው፤ አታምልኩአቸው፤ አትሠዉላቸው፤

See the chapter Copy




2 ነገሥት 17:35
19 Cross References  

እና​ን​ተ​ንም፦ እኔ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ በም​ድ​ራ​ቸው የተ​ቀ​መ​ጣ​ች​ሁ​ባ​ቸ​ውን የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አማ​ል​ክት አት​ፍሩ አል​ኋ​ችሁ። እና​ንተ ግን ቃሌን አል​ሰ​ማ​ች​ሁም።”


አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዛ​ች​ሁን ቃል ኪዳን ብታ​ፈ​ርሱ፥ ሄዳ​ች​ሁም ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ብታ​መ​ልኩ፥ ብት​ሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፥ በዚያ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ ይነ​ድ​ድ​ባ​ች​ኋል፥ ከሰ​ጣ​ች​ሁም ከመ​ል​ካ​ሚቱ ምድር ፈጥ​ና​ችሁ ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ።”


በእ​ና​ን​ተም መካ​ከል ወደ ቀሩት ወደ እነ​ዚህ አሕ​ዛብ አት​ግቡ፤ የአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ስሞች በእ​ና​ንተ መካ​ከል አይ​ጠሩ፤ አት​ማ​ሉ​ባ​ቸ​ውም፤ አታ​ም​ል​ኳ​ቸ​ውም፤ አት​ስ​ገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፤


እንደ ተቀ​ረጸ ብር ናቸው፤ እነ​ር​ሱም አይ​ና​ገ​ሩም፤ መራ​መ​ድም አይ​ቻ​ላ​ቸ​ው​ምና ይሸ​ከ​ሙ​አ​ቸ​ዋል። ክፉ መሥ​ራ​ትም አይ​ቻ​ላ​ቸ​ው​ምና፥ ደግ​ሞም መል​ካም ይሠሩ ዘንድ አይ​ች​ሉ​ምና አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው።”


የገ​ባ​ላ​ቸ​ው​ንም ቃል ኪዳን ሁሉ አል​ጠ​በ​ቁም። ከንቱ ነገ​ር​ንም ተከ​ተሉ፤ ከን​ቱም ሆኑ፤ እንደ እነ​ር​ሱም እን​ዳ​ይ​ሠሩ ያዘ​ዛ​ቸ​ውን በዙ​ሪ​ያ​ቸው ያሉ​ትን አሕ​ዛብ ተከ​ተሉ።


“ከእኔ በቀር ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት አታ​ም​ልክ።


አት​ስ​ገ​ድ​ላ​ቸው፤ አታ​ም​ል​ካ​ቸ​ውም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ቀና​ተኛ አም​ላክ ነኝና፤ በሚ​ጠ​ሉኝ እስከ ሦስ​ተ​ኛና እስከ አራ​ተኛ ትው​ልድ ድረስ የአ​ባ​ቶ​ችን ኀጢ​አት በል​ጆች ላይ የማ​መጣ፤


ትገ​ዙ​ላ​ቸ​ውና ትሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸ​ውም ዘንድ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት አት​ከ​ተሉ፤ ክፉም እን​ዳ​ላ​ደ​ር​ግ​ባ​ችሁ በእ​ጃ​ችሁ ሥራ አታ​ስ​ቈ​ጡኝ።


አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኮ​ሬብ ከእ​ና​ንተ ጋር ቃል ኪዳ​ኑን አጸና።


በዙ​ሪ​ያ​ችሁ ያሉት አሕ​ዛብ የሚ​ያ​መ​ል​ኩ​አ​ቸ​ውን ሌሎች አማ​ል​ክት አት​ከ​ተሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements