Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 17:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ስለ​ዚ​ህም ለአ​ሦር ንጉሥ፥ “ያፈ​ለ​ስ​ኻ​ቸው፥ በሰ​ማ​ር​ያም ከተ​ሞች ያኖ​ር​ኻ​ቸው ሕዝ​ቦች የሀ​ገ​ሩን አም​ላክ ሕግ አላ​ወ​ቁም፤ የሀ​ገ​ሩን አም​ላክ ሕግ አላ​ወ​ቁ​ምና አን​በ​ሶ​ችን ሰድ​ዶ​ባ​ቸ​ዋል፤ እነ​ሆም፥ እየ​ገ​ደ​ሉ​አ​ቸው ነው” ብለው ተና​ገ​ሩት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ለአሦርም ንጉሥ፣ “ወደ ሰማርያ ከተሞች ወስደህ ያሰፈርኸው ሕዝብ የዚያ አገር አምላክ የሚፈልገውን አላወቀም፤ ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ሰብሮ የሚገድል አንበሳ ላከበት” የሚል ወሬ ደረሰው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ለአሦርም ንጉሠ ነገሥት “በሰማርያ ከተሞች ሰፍረው እንዲኖሩ ያደረግሃቸው ሕዝቦች የዚያችን አገር አምላክ ሕግ የሚያውቁ ሆነው አልተገኙም፤ ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ሰባብሮ የሚገድሉ አንበሶችን ላከባቸው” የሚል ወሬ ደረሰው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ለአሦርም ንጉሠ ነገሥት “በሰማርያ ከተሞች ሰፍረው እንዲኖሩ ያደረግሃቸው ሕዝቦች የዚያችን አገር አምላክ ሕግ የሚያውቁ ሆነው አልተገኙም፤ ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ሰባብሮ የሚገድሉ አንበሶችን ላከባቸው” የሚል ወሬ ደረሰው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ስለዚህም ለአሦር ንጉሥ “ያፈለስኻቸው፥ በሰማርያም ከተሞች ያኖርኻቸው የአገሩን አምላክ ወግ አላወቁም፤ የአገሩን አምላክ ወግ አላወቁምና አንበሶችን ሰድዶባቸዋል፤ እነሆም፥ ገደሉአቸው፤” ብለው ተናገሩት።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 17:26
5 Cross References  

ዳን ሆይ፥ ሕያው አም​ላ​ክ​ህን! ደግ​ሞም፦ ሕያው የቤ​ር​ሳ​ቤ​ህን አም​ላክ ብለው በሰ​ማ​ርያ መማ​ፀኛ የሚ​ምሉ፥ እነ​ርሱ ይወ​ድ​ቃሉ፥ ደግ​ሞም አይ​ነ​ሡም።”


የአ​ሦ​ርም ንጉሥ፥ “ከዚያ ካመ​ጣ​ኋ​ቸው ካህ​ናት አን​ዱን ውሰዱ፤ ሄዶም በዚያ ይቀ​መጥ፤ የሀ​ገ​ሩ​ንም አም​ላክ ሕግ ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው” ብሎ አዘዘ።


ሳሙ​ኤ​ልም የን​ጉ​ሡን ሥር​ዐት ነገ​ራ​ቸው፤ በመ​ጽ​ሐ​ፍም ጻፈው፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት አኖ​ረው። ሳሙ​ኤ​ልም ሕዝ​ቡን ሁሉ ወደ እየ​ቤ​ታ​ቸው አሰ​ና​በ​ታ​ቸው። ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ እየ​ቤ​ታ​ቸው ሄዱ።


አሁ​ንም ቃላ​ቸ​ውን ስማ፤ ነገር ግን ጽኑ ምስ​ክር መስ​ክ​ር​ባ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ የሚ​ነ​ግ​ሠ​ውን የን​ጉ​ሡን ሥር​ዐት ንገ​ራ​ቸው።”


በዚ​ያም መቀ​መጥ በጀ​መሩ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አይ​ፈ​ሩ​ትም ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አን​በ​ሶ​ችን ሰደ​ደ​ባ​ቸው፤ ይገ​ድ​ሉ​አ​ቸ​ውም ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements