Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 16:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት የነ​በ​ረ​ውን የና​ሱን መሠ​ዊያ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ፊት ከመ​ሠ​ዊ​ያ​ውና ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መካ​ከል ፈቀቅ አድ​ርጎ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ በሰ​ሜን በኩል አኖ​ረው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በአዲሱ መሠዊያና በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መካከል፣ በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ የነበረውን የናስ መሠዊያ፣ ከቦታው አስነሥቶ ከአዲሱ መሠዊያ በስተሰሜን በኩል አኖረው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ከነሐስ ተሠርቶ ለእግዚአብሔር የተለየውም መሠዊያ በዚያ አዲስ መሠዊያና በቤተ መቅደሱ መካከል ነበር፤ አካዝም ያንን መሠዊያ አስነሥቶ እርሱ ባሠራው በአዲሱ መሠዊያ በስተ ሰሜን በኩል አኖረው፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከነሐስ ተሠርቶ ለእግዚአብሔር የተለየውም መሠዊያ በዚያ አዲስ መሠዊያና በቤተ መቅደሱ መካከል ነበር፤ አካዝም ያንን መሠዊያ አስነሥቶ እርሱ ባሠራው በአዲሱ መሠዊያ በስተ ሰሜን በኩል አኖረው፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በእግዚአብሔርም ፊት የነበረውን የናሱን መሠዊያ ከመቅደሱ ፊት ከመሠዊያውና ከእግዚአብሔር ቤት መካከል ፈቀቅ አድርጎ በመሠውያው አጠገብ በሰሜን በኩል አኖረው።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 16:14
12 Cross References  

ርዝ​መ​ቱም ሃያ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ ክንድ፥ ቁመ​ቱም ዐሥር ክንድ የነ​በ​ረ​ውን የና​ሱን መሠ​ዊያ ሠራ።


ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን መሠ​ዊ​ያም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጅ አኖረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው በላዩ መሥ​ዋ​ዕ​ቱ​ንና ቍር​ባ​ኑን አቀ​ረበ።


ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ው​ንም መሠ​ዊያ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጅ ፊት ታኖ​ረ​ዋ​ለህ።


ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቅ ደም ሁሉ ይደርስባችኋል።


የሆ​ርም ልጅ የኡሪ ልጅ ባስ​ል​ኤል የሠ​ራው የናስ መሠ​ዊያ በዚያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪያ ፊት ነበረ፤ ሰሎ​ሞ​ንና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጉባኤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ይፈ​ል​ጓት ነበር።


ካህ​ኑም ኦርያ ንጉሡ አካዝ ከደ​ማ​ስቆ እንደ ላከ​ለት መሠ​ዊ​ያ​ውን ሁሉ ሠራ፤ እን​ዲ​ሁም ካህኑ ኦርያ ንጉሡ አካዝ ከደ​ማ​ስቆ እስ​ኪ​መጣ ድረስ ሠራው።


“ርዝ​መቱ አም​ስት ክንድ፥ ወር​ዱም አም​ስት ክንድ መሠ​ዊ​ያን ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት አድ​ርግ፤ አራት ማዕ​ዘ​ንም ይሁን፤ ከፍ​ታ​ውም ሦስት ክንድ ይሁን።


በአ​ራ​ቱም ማዕ​ዘን ቀን​ዶ​ችን ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ ቀን​ዶቹ ሥረ-ወጥ ይሁኑ፤ በና​ስም ለብ​ጣ​ቸው።


የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን አሳ​ረገ፤ የመ​ጠ​ጡ​ንም ቍር​ባን አፈ​ሰሰ፤ የደ​ኅ​ን​ነ​ቱ​ንም መሥ​ዋ​ዕት ደም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ረጨ።


ንጉ​ሡም አካዝ፥ “የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን የጥ​ዋት መሥ​ዋ​ዕት፥ የማ​ታ​ው​ንም የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን፥ የን​ጉ​ሡ​ንም መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን፥ የሕ​ዝ​ቡ​ንም ሁሉ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን፥ የመ​ጠ​ጡ​ንም ቍር​ባን በታ​ላቁ መሠ​ዊያ ላይ አቅ​ርብ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት ደም ሁሉ፥ የሌ​ላ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን ደም ሁሉ በእ​ርሱ ላይ ርጭ​በት፤ የናሱ መሠ​ዊያ ግን በየ​ጥ​ዋቱ ለእኔ ይሁን” ብሎ ካህ​ኑን ኦር​ያን አዘ​ዘው።


ንጉ​ሡም አካዝ ነግሦ ሳለ በመ​ተ​ላ​ለፉ ያረ​ከ​ሰ​ውን ዕቃ ሁሉ አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ናል፤ ቀድ​ሰ​ና​ልም፤ እነ​ሆም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ፊት ሆነ​ዋል” አሉት።


መድ​ረ​ካ​ቸ​ውን በመ​ድ​ረኬ አጠ​ገብ፥ መቃ​ና​ቸ​ው​ንም በመ​ቃኔ አጠ​ገብ አድ​ር​ገ​ዋ​ልና። በእ​ኔና በእ​ነ​ርሱ መካ​ከል ግንብ ብቻ ነበረ፤ በሠ​ሩ​ትም ርኵ​ሰት ቅዱስ ስሜን አረ​ከሱ፤ ስለ​ዚህ በቍ​ጣዬ አጠ​ፋ​ኋ​ቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements