Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 16:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ካህ​ኑም ኦርያ ንጉሡ አካዝ ከደ​ማ​ስቆ እንደ ላከ​ለት መሠ​ዊ​ያ​ውን ሁሉ ሠራ፤ እን​ዲ​ሁም ካህኑ ኦርያ ንጉሡ አካዝ ከደ​ማ​ስቆ እስ​ኪ​መጣ ድረስ ሠራው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ካህኑ ኦርያም ንጉሥ አካዝ ከደማስቆ በላከለት ዝርዝር ጥናት መሠረት መሠዊያ ሠራ፤ ንጉሡ አካዝ ከመመለሱም በፊት አጠናቀቀው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ስለዚህም ኡሪያ ንጉሥ አካዝ ተመልሶ ከመምጣቱ በፊት ልክ ያንኑ የሚመስል መሠዊያ ሠራ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ስለዚህም ኡሪያ ንጉሥ አካዝ ተመልሶ ከመምጣቱ በፊት ልክ ያንኑ የሚመስል መሠዊያ ሠራ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ካህኑም ኦርያ መሠዊያ ሠራ፤ ንጉሡ አካዝ ከደማስቆ ልኮ እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ ካህኑ ኦርያ ንጉሡ አካዝ ከደማስቆ እስኪመጣ ድረስ ሠራው።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 16:11
17 Cross References  

አሁ​ንስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያይ​ደለ ለሰው ብዬ አስ​ተ​ም​ራ​ለ​ሁን? ወይስ ሰውን ደስ አሰ​ኛ​ለ​ሁን? ሰውን ደስ ላሰኝ ብወ​ድስ የክ​ር​ስ​ቶስ ባሪያ አይ​ደ​ለ​ሁም።


ኤፍ​ሬም የተ​ገፋ ሆነ፤ በፍ​ር​ድም ተረ​ገጠ፤ ከን​ቱን ይከ​ተል ዘንድ ጀም​ሮ​አ​ልና።


ሕዝቤ አእ​ምሮ እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው ይመ​ስ​ላሉ፤ አን​ተም አእ​ም​ሮህ ተለ​ይ​ቶ​ሃ​ልና እኔ ካህን እን​ዳ​ት​ሆ​ነኝ እተ​ው​ሃ​ለሁ፤ የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም ሕግ ረስ​ተ​ሃ​ልና እኔ ደግሞ ልጆ​ች​ህን እረ​ሳ​ለሁ።


ካህ​ና​ቷም ሕጌን ጣሱ፤ በመ​ቅ​ደ​ሴም መካ​ከል ቅድ​ሳ​ቴን አረ​ከሱ፤ ከር​ኵ​ሰ​ትም አል​ራ​ቁም፤ በን​ጹ​ሕና በር​ኩስ መካ​ከል ያለ​ው​ንም ልዩ​ነት አላ​ወ​ቁም፤ ዐይ​ና​ቸ​ው​ንም ከሰ​ን​በ​ታቴ ሸፈኑ፤ እኔም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ረከ​ስሁ።


“ነቢ​ዩና ካህ​ኑም ረክ​ሰ​ዋ​ልና፥ በቤ​ቴም ውስጥ ክፋ​ታ​ቸ​ውን አግ​ኝ​ቻ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


የታ​መ​ኑ​ትን ሰዎች ካህ​ኑን ኦር​ያ​ንና የበ​ራ​ክ​ዩን ልጅ ዘካ​ር​ያ​ስን ምስ​ክ​ሮች አድ​ር​ግ​ልኝ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ አድ​ሮ​ባ​ቸ​ዋ​ልና፤”


የይ​ሁዳ ንጉሥ አካ​ዝም የአ​ሦ​ርን ንጉሥ ቴል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶ​ርን ሊገ​ና​ኘው ወደ ደማ​ስቆ ሄደ፤ በደ​ማ​ስቆ የነ​በ​ረ​ው​ንም መሠ​ዊያ አየ፤ ንጉ​ሡም አካዝ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ምሳ​ሌና የአ​ሠ​ራ​ሩን መልክ ወደ ካህኑ ወደ ኦርያ ላከው።


ንጉ​ሡም ከደ​ማ​ስቆ በመጣ ጊዜ መሠ​ዊ​ያ​ውን አየ፤ ንጉ​ሡም ወደ መሠ​ዊ​ያው ወጣ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት የነ​በ​ረ​ውን የና​ሱን መሠ​ዊያ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ፊት ከመ​ሠ​ዊ​ያ​ውና ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መካ​ከል ፈቀቅ አድ​ርጎ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ በሰ​ሜን በኩል አኖ​ረው።


ካህኑ ኦር​ያም ንጉሡ አካዝ እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ እን​ዲሁ አደ​ረገ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ስሜን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አኖ​ራ​ለሁ” ባለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መሠ​ዊ​ያን ሠራ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለዳ​ዊ​ትና ለልጁ ለሰ​ሎ​ሞን፥ “በዚህ ቤት ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገድ ሁሉ በመ​ረ​ጥ​ኋት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ስሜን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አኖ​ራ​ለሁ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ስሜ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል” ባለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የጣ​ዖት መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ችን ሠራ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements