Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 15:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 ኢዮ​አ​ታ​ምም እንደ አባ​ቶቹ አን​ቀ​ላፋ፥ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ተቀ​በረ፤ ልጁም አካዝ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 ኢዮአታምም ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ አባቶቹ በተቀበሩበትም በአባቱ በዳዊት ከተማ ተቀበረ። ልጁ አካዝም በምትኩ ነገሠ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 ኢዮአታም ሞተ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘው የነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ አካዝ ነገሠ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 ኢዮአታም ሞተ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘው የነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ አካዝ ነገሠ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 ኢዮአታም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በአባቱም በዳዊት ከተማ ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ፤ ልጁም አካዝ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 15:38
12 Cross References  

ዖዝያንም ኢዮአታምን ወለደ፤ ኢዮአታምም አካዝን ወለደ፤


አካ​ዝም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሃያ ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ ስድ​ስት ዓመት ነገሠ፤ እንደ አባ​ቱም እንደ ዳዊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገር አላ​ደ​ረ​ገም።


ልጁ አካዝ፥ ልጁ ሕዝ​ቅ​ያስ፥ ልጁ ምናሴ፥


በሮ​ሜ​ልዩ ልጅ በፋ​ቁሔ በዐ​ሥራ ሰባ​ተ​ኛው ዓመት የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​አ​ታም ልጅ አካዝ ነገሠ።


ሮብ​ዓ​ምም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ተቀ​በረ። ልጁም አብያ በፋ​ን​ታው ነገሠ።


ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም የነ​ገ​ሠ​በት ዘመን ሃያ አራት ዓመት ነበረ፥ ከአ​ባ​ቶ​ቹም ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ ልጁም ናባጥ በፋ​ን​ታው ነገሠ።


የዳ​ዊት አሽ​ከ​ሮ​ችም፥ “ለጌ​ታ​ችን ለን​ጉሡ ድን​ግል ልጅ ትፈ​ለ​ግ​ለት፤ በን​ጉ​ሡም ፊት ቆማ ታገ​ል​ግ​ለው፥ በጌ​ታ​ች​ንም በን​ጉሡ ብብት ተኝታ ትቀ​ፈው፤ ታሙ​ቀ​ውም” አሉ።


ዕድ​ሜ​ህም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፤ ከአ​ባ​ቶ​ች​ህም ጋር ባን​ቀ​ላ​ፋህ ጊዜ፥ ከወ​ገ​ብህ የሚ​ወ​ጣ​ውን ዘር​ህን ከአ​ንተ በኋላ አስ​ነ​ሣ​ለሁ፤ መን​ግ​ሥ​ቱ​ንም አዘ​ጋ​ጃ​ለሁ ።


በዚ​ያም ወራት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሶ​ር​ያን ንጉሥ ረአ​ሶ​ን​ንና የሮ​ሜ​ል​ዩን ልጅ ፋቁ​ሔን በይ​ሁዳ ላይ መላክ ጀመረ።


ዳዊ​ትም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ተቀ​በረ።


ኢዮ​ራ​ምም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ተቀ​በረ፤ በፋ​ን​ታ​ውም ልጁ አካ​ዝ​ያስ ነገሠ።


ኢዮ​አ​ታ​ምም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ቀበ​ሩት፤ ልጁም አካዝ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements