2 ነገሥት 14:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 በሙሴ ሕግ መጽሐፍም እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔርም፥ “ሁሉ በኀጢአቱ ይሙት እንጂ አባቶች ስለ ልጆች አይሙቱ፤ ልጆችም ስለ አባቶች አይሙቱ” ብሎ እንዳዘዘ የነፍሰ ገዳዮቹን ልጆች አልገደላቸውም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ይሁን እንጂ በሙሴ የሕግ መጽሐፍ እግዚአብሔር፣ “ሰው ሁሉ በገዛ ኀጢአቱ ይሙት እንጂ ወላጆች በልጆቻቸው አይገደሉ፣ ልጆችም በወላጆቻቸው ኀጢአት አይገደሉ” ሲል ያዘዘ በመሆኑ፣ የነፍሰ ገዳዩን ልጆች አልገደላቸውም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ይሁን እንጂ ልጆቻቸውን አልገደለም፤ ይልቁንም በኦሪት ሕግ እግዚአብሔር “ልጆቻቸው በፈጸሙት ኃጢአት ወላጆች በሞት አይቀጡበትም፤ ወላጆችም በፈጸሙት ኃጢአት ልጆች በሞት አይቀጡበትም፤ እያንዳንዱ ሰው ራሱ በፈጸመው ወንጀል ብቻ በሞት ይቀጣ” ሲል የሰጠውን ትእዛዝ ፈጽሞአል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ይሁን እንጂ ልጆቻቸውን አልገደለም፤ ይልቁንም በኦሪት ሕግ እግዚአብሔር “ልጆቻቸው በፈጸሙት ኃጢአት ወላጆች በሞት አይቀጡበትም፤ ወላጆችም በፈጸሙት ኃጢአት ልጆች በሞት አይቀጡበትም፤ እያንዳንዱ ሰው ራሱ በፈጸመው ወንጀል ብቻ በሞት ይቀጣ” ሲል የሰጠውን ትእዛዝ ፈጽሞአል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 በሙሴ ሕግ መጽሐፍም እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔርም “ሁሉ በኀጢአቱ ይሙት እንጂ አባቶች በልጆች አይሙቱ፤ ልጆችም በአባቶች አይሙቱ፤” ብሎ እንዳዘዘ የነፍሰ ገዳዮቹን ልጆች አልገደለም። See the chapter |