Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 14:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ወር​ቁ​ንና ብሩን ሁሉ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤትና በን​ጉሥ ቤተ መዛ​ግ​ብት የነ​በ​ሩ​ትን ዕቃ​ዎች ሁሉ፤ በመ​ያ​ዣም የተ​ያ​ዙ​ትን ልጆች ወስዶ ወደ ሰማ​ርያ ተመ​ለሰ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥቱ ግምጃ ቤቶች ያለውን ወርቅ ብርና ዕቃ በሙሉ፣ በዚያም የተገኘውን ዕቃ ሁሉ በመውሰድ ምርኮኞችንም ይዞ ወደ ሰማርያ ተመለሰ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በዚያም ያገኘውን ወርቅና ብር ሁሉ፥ የቤተ መቅደሱን ንዋያተ ቅድሳትና የቤተ መንግሥቱን ሀብት ሁሉ ጭኖ ወደ ሰማርያ ተመለሰ፤ በመያዣ ስም የተማረኩ ሰዎችንም ይዞ ሄደ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በዚያም ያገኘውን ወርቅና ብር ሁሉ፥ የቤተ መቅደሱን ንዋያተ ቅድሳትና የቤተ መንግሥቱን ሀብት ሁሉ ጭኖ ወደ ሰማርያ ተመለሰ፤ በመያዣ ስም የተማረኩ ሰዎችንም ይዞ ሄደ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ወርቁንና ብሩን ሁሉ፥ በእግዚአብሔርም ቤትና በንጉሡ ቤት መዛግብት የነበሩትን ዕቃዎች ሁሉ፥ በመያዣም የተያዙትን ወስዶ ወደ ሰማርያ ተመለሰ።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 14:14
7 Cross References  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ መዛ​ግ​ብ​ትና የን​ጉ​ሡን ቤተ መዛ​ግ​ብት ሁሉ ወሰደ፤ ዳዊ​ትም ከሱባ ንጉሥ ከአ​ድ​ር​ዓ​ዛር ልጆች እጅ ወስዶ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ያመ​ጣ​ቸ​ውን የወ​ርቅ ጦሮ​ችና ሰሎ​ሞን የሠ​ራ​ቸ​ውን የወ​ር​ቁን ጋሻና ጦር ሁሉ ወደ ግብፅ ወሰደ።


እን​ዲ​ሁም ንጉሡ ሰሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የአ​ሠ​ራው ሥራ ሁሉ ተፈ​ጸመ። አባ​ቱም ዳዊት የቀ​ደ​ሰ​ውን፥ ራሱም የቀ​ደ​ሰ​ውን፥ የብ​ርና የወ​ርቅ ዕቃ ሰሎ​ሞን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ በነ​በሩ ግምጃ ቤቶች አገባ።


የአ​በ​ዛ​ዎች አለ​ቃም ጥና​ዎ​ቹን ከወ​ር​ቅና ከብር የተ​ሠሩ መኰ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ንም ወሰደ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ መዛ​ግ​ብት ሁሉ የን​ጉ​ሡ​ንም ቤተ መዛ​ግ​ብት ከዚያ አወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገ​ረው የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ሰሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ የሠ​ራ​ውን የወ​ር​ቁን ዕቃ ሁሉ ሰባ​በረ።


አሁ​ንም እን​ግ​ዲህ ከጌ​ታዬ ከአ​ሦር ንጉሥ ጋር ተወ​ራ​ረድ፤ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ው​ንም ሰዎች ማግ​ኘት ቢቻ​ልህ እኔ ሁለት ሺህ ፈረ​ሶች እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።


የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ኢዮ​አስ አባ​ቶቹ የይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥና ኢዮ​ራም፥ አካ​ዝ​ያ​ስም የቀ​ደ​ሱ​ትን ቅዱስ ነገር፥ እር​ሱም የቀ​ደ​ሰ​ውን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤትና በን​ጉ​ሡም ቤተ መዛ​ግ​ብት የተ​ገ​ኘ​ውን ወርቅ ሁሉ ወሰደ፤ ወደ ሶር​ያም ንጉሥ ወደ አዛ​ሄል ላከው። እር​ሱም ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሰ።


አሳም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትና በን​ጉሥ ቤተ መዛ​ግ​ብት የተ​ገ​ኘ​ውን ብርና ወርቅ ሁሉ ወስዶ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ ሰጣ​ቸው፤ ንጉ​ሡም አሳ በደ​ማ​ስቆ ለተ​ቀ​መ​ጠው ለአ​ዚን ልጅ ለጤ​ቤ​ር​ማን ልጅ ለሶ​ርያ ንጉሥ ለወ​ልደ አዴር፥


Follow us:

Advertisements


Advertisements