Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 14:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 አሜ​ስ​ያስ ግን አል​ሰ​ማም፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ዮአስ ዘመተ፤ እር​ሱና የይ​ሁዳ ንጉሥ አሜ​ስ​ያ​ስም በይ​ሁዳ ባለች በቤ​ት​ሳ​ሚስ ፊት ለፊት ተያዩ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 አሜስያስ ግን አልሰማም፤ ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ ዮአስ ወጣ፤ እርሱና የይሁዳ ንጉሥ አሜስያስም በይሁዳ ምድር በቤትሳሚስ ፊት ለፊት ተጋጠሙ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 አሜስያስ ግን የዮአስን መልስ ከምንም አልቆጠረውም፤ ስለዚህም ንጉሥ ዮአስ ሠራዊቱን አስከትሎ በአሜስያስ ላይ በመዝመት በይሁዳ ምድር በምትገኘው በቤትሼሜሽ ጦርነት ገጠመው፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 አሜስያስ ግን የዮአስን መልስ ከምንም አልቈጠረውም፤ ስለዚህም ንጉሥ ዮአስ ሠራዊቱን አስከትሎ በአሜስያስ ላይ በመዝመት በይሁዳ ምድር በምትገኘው በቤትሼሜሽ ጦርነት ገጠመው፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 አሜስያስ ግን አልሰማም፤ የእስራኤልም ንጉሥ ዮአስ ወጣ፤ እርሱና የይሁዳ ንጉሥ አሜስያስም በይሁዳ ባለች በቤት ሳሚስ እርስ በርሳቸው ተያዩ።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 14:11
8 Cross References  

ቄሮህ፥ ሚጋ​ላ​ህ​ሪም፥ ቤታ​ሚና፥ ቴስ​ሚስ፤ ዐሥራ ዘጠኝ መን​ደ​ሮ​ችና ከተ​ሞ​ቻ​ቸው።


የኤ​ዶ​ም​ያ​ስ​ንም አማ​ል​ክት ስለ ፈለጉ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ይህ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነበ​ረና አሜ​ስ​ያስ አል​ሰ​ማም።


እር​ሱም ይህን ሲና​ገር ንጉሡ አሜ​ስ​ያስ፥ “በውኑ የን​ጉሡ አማ​ካሪ ልት​ሆን ሹሜ​ሃ​ለ​ሁን? ቅጣት እን​ዳ​ያ​ገ​ኝህ ተጠ​ን​ቀቅ” አለው። ነቢ​ዩም፥ “ይህን አድ​ር​ገ​ሃ​ልና፥ ምክ​ሬ​ንም አል​ሰ​ማ​ህ​ምና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ጠ​ፋህ እን​ዳ​ሰበ አወ​ቅሁ” ብሎ ዝም አለ።


አሳ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ዮጣ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቤት​ሳ​ሚ​ስ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ከእ​ነ​ዚህ ከሁ​ለቱ ነገ​ዶች ዘጠኝ ከተ​ሞ​ችን ሰጡ።


ድን​በ​ሩም ከበ​ኣላ በባ​ሕር በኩል ያል​ፋል፤ ከዚ​ያም በኢ​ያ​ሪም ከተማ ደቡብ በኩ​ልና በኪ​ስ​ሎን ሰሜን በኩል ወደ አሥ​ራ​ቱስ ድን​በር ያል​ፋል፤ በፀ​ሐይ ከተ​ማም ላይ ይወ​ር​ዳል፤ በሊ​ባም በኩል ያል​ፋል።


ነገር ግን ዮፍ​ታሔ የላ​ከ​በ​ትን ቃል የአ​ሞን ልጆች ንጉሥ አል​ሰ​ማም፤ እን​ቢም አላ​ቸው።


የቀ​ረ​ውም የዮ​አስ ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ ከይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ከአ​ሜ​ስ​ያስ ጋር የተ​ዋ​ጋ​በት ኀይሉ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


Follow us:

Advertisements


Advertisements