Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 13:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 አዛ​ሄ​ልም ከአ​ባቱ ከኢ​ዮ​አ​ካዝ እጅ በሰ​ልፍ የወ​ሰ​ዳ​ቸ​ውን ከተ​ሞች የኢ​ዮ​አ​ካዝ ልጅ ዮአስ መልሶ ከአ​ዛ​ሄል ልጅ ከወ​ልደ አዴር እጅ ወሰደ። ዮአ​ስም ሦስት ጊዜ መታው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ከተ​ሞች መለሰ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ከዚያም የኢዮአካዝ ልጅ ዮአስ፣ አዛሄል ከአባቱ ከኢዮአካዝ እጅ በጦርነት የወሰዳቸውን ከተሞች ከአዛሄል ልጅ ከቤን ሃዳድ አስመልሶ ያዘ። ዮአስ ሦስት ጊዜ ድል አደረገው፤ የእስራኤልንም ከተሞች በዚህ ሁኔታ መልሶ ያዘ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ከዚህም በኋላ የእስራኤል ንጉሥ ዮአስ ቤንሀዳድን ሦስት ጊዜ ድል ነሥቶ በአባቱ በኢዮአካዝ ዘመነ መንግሥት ቤንሀዳድ ይዞአቸው የነበሩትን ከተሞች አስመለሰ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ከዚህም በኋላ የእስራኤል ንጉሥ ዮአስ ቤንሀዳድን ሦስት ጊዜ ድል ነሥቶ በአባቱ በኢዮአካዝ ዘመነ መንግሥት ቤንሀዳድ ይዞአቸው የነበሩትን ከተሞች አስመለሰ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 አዛሄልም ከአባቱ ከኢዮአካዝ እጅ በሰልፍ የወሰዳቸውን ከተሞች የኢዮአካዝ ልጅ ዮአስ ከአዛሄል ልጅ ከቤንሀዳድ እጅ ወሰደ። ዮአስም ሦስት ጊዜ መታው፤ የእስራኤልንም ከተሞች መለሰ።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 13:25
8 Cross References  

በዚ​ያም ወራት እዚ​አ​ብ​ሔር እስ​ራ​ኤ​ልን ያጠፋ ጀመረ፤ አዛ​ሄ​ልም በእ​ስ​ራ​ኤል ዳርቻ ሁሉ መታ​ቸው።


በጋ​ት​ሔ​ፌር በነ​በ​ረው በአ​ማቴ ልጅ በባ​ሪ​ያው በነ​ቢዩ በዮ​ናስ አፍ እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እስ​ራ​ኤል አም​ላክ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ድን​በር ከሔ​ማት መግ​ቢያ ጀምሮ እስከ ዓረባ ባሕር ድረስ መለሰ።


በዮ​ር​ዳ​ኖስ ምሥ​ራቅ ያለ​ውን የገ​ለ​ዓ​ድን ሀገር ሁሉ፥ በአ​ር​ኖን ወንዝ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር ጀምሮ የጋ​ድ​ንና የሮ​ቤ​ልን የም​ና​ሴ​ንም ሀገር፥ ገለ​ዓ​ድ​ንና ባሳ​ንን መታ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በጣም ተቈጣ፤ በዘ​መ​ኑም ሁሉ በሶ​ር​ያው ንጉሥ በአ​ዛ​ሄል እጅ፥ በአ​ዛ​ሄ​ልም ልጅ በወ​ልደ አዴር እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለእ​ስ​ራ​ኤል ታዳ​ጊን ሰጠ፤ ከሶ​ር​ያ​ው​ያ​ንም እጅ ዳኑ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እንደ ቀድ​ሞው ጊዜ በድ​ን​ኳ​ና​ቸው ተቀ​መጡ።


የሶ​ር​ያም ንጉሥ አዛ​ሄል ሞተ፤ ልጁም ወልደ አዴር በፋ​ን​ታው ነገሠ።


“አክ​ዓብ በፊቴ እንደ ደነ​ገጠ አየ​ህን? በፊቴ በልጁ ዘመን በቤቱ ላይ ክፉ ነገር አመ​ጣ​ለሁ እንጂ በእ​ርሱ ዘመን ክፉ ነገር አላ​መ​ጣም።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements