Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 12:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​አስ ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ታሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ኢዮአስ በዘመነ መንግሥቱ ያከናወነው ሌላው ተግባርና የፈጸመው ሥራ ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ንጉሥ ኢዮአስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ንጉሥ ኢዮአስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 የይሁዳም ንጉሥ ኢዮአስ አባቶቹ የይሁዳ ነገሥታት ኢዮሣፍጥና ኢዮራም አካዝያስም የቀደሱትን ቅዱስ ነገር፥ እርሱም የቀደሰውን፥ በእግዚአብሔርም ቤትና በንጉሡ ቤተ መዛግብት የተገኘውን ወርቅ ሁሉ ወሰደ፤ ወደ ሶርያም ንጉሥ ወደ አዛሄል ላከው። እርሱም ከኢየሩሳሌም ተመለሰ።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 12:19
10 Cross References  

የተ​ረ​ፈ​ውም የኢ​ዮ​ራም ነገር ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


የቀ​ረ​ውም የሮ​ብ​ዓም ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ታሪክ መጽ​ሐፍ እነሆ፥ ተጽ​ፎ​አል።


የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ነገር፥ እን​ዴት እንደ ተዋጋ፥ እን​ዴ​ትም እንደ ነገሠ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል።


የቀ​ረ​ውም የሰ​ሎ​ሞን ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ ጥበ​ቡም ሁሉ፥ እነሆ፥ በሰ​ሎ​ሞን የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል።


የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ኢዮ​አስ አባ​ቶቹ የይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥና ኢዮ​ራም፥ አካ​ዝ​ያ​ስም የቀ​ደ​ሱ​ትን ቅዱስ ነገር፥ እር​ሱም የቀ​ደ​ሰ​ውን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤትና በን​ጉ​ሡም ቤተ መዛ​ግ​ብት የተ​ገ​ኘ​ውን ወርቅ ሁሉ ወሰደ፤ ወደ ሶር​ያም ንጉሥ ወደ አዛ​ሄል ላከው። እር​ሱም ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሰ።


አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ተነ​ሥ​ተው ዐመ​ፁ​በት፥ ወደ ሲላ በሚ​ወ​ር​ደ​ውም መን​ገድ በመ​ሀሎ ቤት ኢዮ​አ​ስን ገደ​ሉት።


አሳም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትና በን​ጉሥ ቤተ መዛ​ግ​ብት የተ​ገ​ኘ​ውን ብርና ወርቅ ሁሉ ወስዶ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ ሰጣ​ቸው፤ ንጉ​ሡም አሳ በደ​ማ​ስቆ ለተ​ቀ​መ​ጠው ለአ​ዚን ልጅ ለጤ​ቤ​ር​ማን ልጅ ለሶ​ርያ ንጉሥ ለወ​ልደ አዴር፥


አካ​ዝም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትና በን​ጉሡ ቤተ መዛ​ግ​ብት የተ​ገ​ኘ​ውን ብርና ወርቅ ወስዶ ወደ አሦር ንጉሥ ገጸ በረ​ከት አድ​ርጎ ሰደ​ደው።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትና በን​ጉሡ ቤተ መዛ​ግ​ብት የተ​ገ​ኘ​ውን ብር ሁሉ ሰጠው።


በዚ​ያን ጊዜም ሕዝ​ቅ​ያስ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ ደጆ​ችና የይ​ሁዳ ንጉሥ ሕዝ​ቅ​ያስ ከለ​በ​ጣ​ቸው መቃ​ኖች ወር​ቁን ቈረጠ፤ ለአ​ሦ​ርም ንጉሥ ሰጠው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements