Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 11:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ካህ​ኑም ዮዳሄ በጭ​ፍ​ራው ላይ የተ​ሾ​ሙ​ትን የመቶ አለ​ቆች፥ “ወደ ሰልፉ መካ​ከል አው​ጡ​አት፤ የሚ​ከ​ተ​ላ​ት​ንም በሰ​ይፍ ግደ​ሉት” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፤ ካህኑ፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አት​ገ​ደል” ብሎ​አ​ልና።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ካህኑ ዮዳሄም የወታደሮች አዛዥ ወደሆኑት የመቶ አለቆች፣ “በረድፍ በተሰለፉት ጭፍሮች መካከል አውጧት፤ የሚከተላትንም ሁሉ በሰይፍ ግደሉት” ሲል አዘዘ፤ ይህ የሆነውም ካህኑ አስቀድሞ፣ “በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መገደል የለባትም” በማለቱ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ዮዳሄ በበኩሉ ዐታልያ በቤተ መቅደሱ ክልል ውስጥ እንድትገደል አልፈለገም፤ ስለዚህም የጦር አለቆቹን “ግራና ቀኝ በተሰለፉት ዘቦች መካከል አውጥታችሁ ውሰዱአት፤ እርሷን ለመከተል የሚሞክር ቢኖር ይገደል” ሲል አዘዛቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ዮዳሄ በበኩሉ ዐታልያ በቤተ መቅደሱ ክልል ውስጥ እንድትገደል አልፈለገም፤ ስለዚህም የጦር አለቆቹን “ግራና ቀኝ በተሰለፉት ዘቦች መካከል አውጥታችሁ ውሰዱአት፤ እርስዋን ለመከተል የሚሞክር ቢኖር ይገደል” ሲል አዘዛቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ካህኑም ዮዳሄ በጭፍራው ላይ የተሾሙትን የመቶ አለቆች “ወደ ሰልፉ መካከል አውጡአት፤ የሚከተላትንም በሰይፍ ግደሉት፤” ብሎ አዘዛቸው፤ ካህኑ “በእግዚአብሔር ቤት አትገደል፤” ብሎአልና።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 11:15
10 Cross References  

ስለ​ዚህ አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ትን​ቢት ተና​ገር፤ እጅ​ህን በእ​ጅህ ላይ አጨ​ብ​ጭብ፤ የተ​ገ​ደሉ ሰዎች ሰይፍ ሦስት ጊዜ ይደ​ጋ​ግም፤ ይኸ​ውም የታ​ላቅ ግድያ ሰይፍ ነው፤ ያስ​ደ​ነ​ግ​ጣ​ቸ​ዋ​ልም።


እር​ሱም፥ “ቤቱን አር​ክሱ፤ ወጥ​ታ​ችሁ ግደሉ፤ በሙ​ታ​ንም መን​ገ​ዶ​ችን ሙሉ” አላ​ቸው።


ካህ​ኑም ኢዮ​አዳ ወጥቶ በጭ​ፍ​ራው ላይ የተ​ሾ​ሙ​ትን አለ​ቆ​ችና የመቶ አለ​ቆች፥ “ከቤተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ውጭ አው​ጡ​አት፤ የሚ​ከ​ተ​ላ​ትም በሰ​ይፍ ይገ​ደል” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው። ካህኑ፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ አት​ገ​ደል” ብሎ​አ​ልና።


ካህ​ኑም ኢዮ​አዳ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የነ​በ​ረ​ውን የን​ጉ​ሡን የዳ​ዊ​ትን ሰይ​ፍና ጦር፥ አላ​ባሽ አግ​ሬ​ው​ንም ጋሻ ለመቶ አለ​ቆች ሰጣ​ቸው።


በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ዮዳሄ ልኮ፥ በኮ​ራ​ው​ያ​ንና በዘ​በ​ኞች ላይ ያሉ​ትን የመቶ አለ​ቆች ወሰደ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አገ​ባ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አማ​ላ​ቸው፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ልጅ አሳ​ያ​ቸው።


ከተ​ማ​ውም ሁሉ ታወከ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ እየ​ሮጡ ሄደው ጳው​ሎ​ስን ጐት​ተው ከቤተ መቅ​ደስ አወ​ጡት፤ በሩ​ንም ሁሉ ዘጉ።


እነ​ሆም፥ ንጉ​ሡን እንደ ተለ​መ​ደው በዓ​ምዱ አጠ​ገብ ቆሞ፥ ከን​ጉ​ሡም ጋር መዘ​ም​ራ​ንና መለ​ከ​ተ​ኞች ቆመው አየች፤ የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ ሁሉ ደስ ብሎ​አ​ቸው መለ​ከት ይነፉ ነበር። ጎቶ​ል​ያም ልብ​ስ​ዋን ቀድዳ፥ “ዐመፅ ነው፥ ዐመፅ ነው፥” ብላ ጮኸች።


እር​ስ​ዋ​ንም ይዘው በን​ጉሡ ቤት አጠ​ገብ ወደ አለ ወደ ፈረ​ሶች መግ​ቢያ መን​ገድ ወሰ​ዱ​አት፤ በዚ​ያም ገደ​ሉ​አት።


ሰው ግን ቢሸ​ምቅ ጠላ​ቱ​ንም በተ​ን​ኰል ቢገ​ድ​ለ​ውና ቢማ​ፀን፥ እን​ዲ​ገ​ደል ከመ​ሠ​ዊ​ያዬ አው​ጥ​ተህ ውሰ​ደው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements