Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 11:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ዮዳ​ሄም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የነ​በ​ረ​ውን የን​ጉ​ሡን የዳ​ዊ​ትን ሰይ​ፍና ጦር ሁሉ ለመቶ አለ​ቆች ሰጣ​ቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ካህኑም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የነበሩትን የንጉሥ ዳዊትን ጦሮችና ጋሻዎች ለመቶ አለቆቹ ሰጣቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ዮዳሄም በቤተ መቅደስ ተቀምጠው ይጠበቁ የነበሩትን የንጉሥ ዳዊትን ጦሮችና ጋሻዎች አውጥቶ ለጦር አለቆቹ ሰጣቸው፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ዮዳሄም በቤተ መቅደስ ተቀምጠው ይጠበቁ የነበሩትን የንጉሥ ዳዊትን ጦሮችና ጋሻዎች አውጥቶ ለጦር አለቆቹ ሰጣቸው፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ካህኑም በእግዚአብሔር ቤት የነበረውን የንጉሡን የዳዊትን ጋሻና ጦር ሁሉ ለመቶ አለቆች ሰጣቸው።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 11:10
7 Cross References  

ዳዊ​ትም ለሱ​ባን ንጉሥ ለአ​ድ​ር​አ​ዛር አገ​ል​ጋ​ዮች የነ​በ​ሩ​ትን ጋሻ አግ​ሬ​ዎች ወሰደ፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አመ​ጣ​ቸው። እነ​ዚ​ህ​ንም የግ​ብፅ ንጉሥ ሱስ​ቀም በሰ​ሎ​ሞን ልጅ በሮ​ብ​ዓም ዘመን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በወጣ ጊዜ ወሰ​ዳ​ቸው።


ዳዊ​ትም ለአ​ድ​ር​አ​ዛር አገ​ል​ጋ​ዮች የነ​በ​ሩ​ትን የወ​ርቅ ማር​ዳ​ዎች ወሰደ፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ይዞ​አ​ቸው መጣ።


ሰሎ​ሞ​ንም አባቱ ዳዊት የቀ​ደ​ሰ​ውን ብሩ​ንና ወር​ቁን፥ የመ​ገ​ል​ገያ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ አም​ጥቶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ በነ​በ​ረው ግምጃ ቤት አገባ።


ካህ​ኑም፥ “በኤላ ሸለቆ የገ​ደ​ል​ኸው የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊው የጎ​ል​ያድ ሰይፍ እነሆ፥ በመ​ጐ​ና​ጸ​ፊያ ተጠ​ቅ​ልላ አለች፤ የም​ት​ወ​ስ​ዳት ከሆነ ውሰ​ዳት፤ ከእ​ር​ስዋ በቀር ሌላ ከዚህ የለ​ምና” አለው። ዳዊ​ትም፥ “ከእ​ር​ስዋ በቀር ሌላ ከሌለ እር​ስ​ዋን ስጠኝ” አለው። እር​ሱም ሰጠው።


ዘበ​ኞ​ቹም ሁሉ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው የጦር ዕቃ​ቸ​ውን በእ​ጃ​ቸው ይዘው በን​ጉሡ ዙሪያ ከቤቱ ቀኝ እስከ ቤቱ ግራ ድረስ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውና በቤቱ አጠ​ገብ ቆሙ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements