Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 10:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ኢዩ ከይ​ሁዳ ንጉሥ ከአ​ካ​ዝ​ያስ ወን​ድ​ሞች ጋር ተገ​ና​ኝቶ፥ “እና​ንተ እነ​ማን ናችሁ?” አለ፤ እነ​ር​ሱም፥ “እኛ የይ​ሁዳ ንጉሥ የአ​ካ​ዝ​ያስ ወን​ድ​ሞች ነን፤ የን​ጉ​ሡ​ንና የእ​ቴ​ጌ​ዪ​ቱን ልጆች ደኅ​ን​ነት እን​ነ​ግ​ረው ዘንድ ወረ​ድን” አሉት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ኢዩ ከይሁዳ ንጉሥ ከአካዝያስ ሥጋ ዘመዶች ጥቂቶቹን አግኝቶ፣ “እናንተ እነማን ናችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “እኛ የአካዝያስ ሥጋ ዘመዶች ነን፤ ንጉሣዊውን ቤተ ሰብና የእቴጌዪቱን ልጆች ለመጠየቅ ወደዚህ ወርደን መጥተናል” አሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ከሟቹ የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ ዘመዶች መካከል ጥቂቶቹን አግኝቶ “እናንተ እነማን ናችሁ?” ሲል ጠየቀ። እነርሱም “እኛ የአካዝያስ ዘመዶች ነን፤ አሁንም የንግሥት ኤልዛቤልን ልጆችና የቀሩትንም ንጉሣውያን ቤተሰብ እጅ ለመንሣት ወደ ኢይዝራኤል መሄዳችን ነው” ሲሉ መለሱለት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ከሟቹ የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ ዘመዶች መካከል ጥቂቶቹን አግኝቶ “እናንተ እነማን ናችሁ?” ሲል ጠየቀ። እነርሱም “እኛ የአካዝያስ ዘመዶች ነን፤ አሁንም የንግሥት ኤልዛቤልን ልጆችና የቀሩትንም ንጉሣውያን ቤተሰብ እጅ ለመንሣት ወደ ኢይዝራኤል መሄዳችን ነው” ሲሉ መለሱለት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ኢዩ ከይሁዳ ንጉሥ ከአካዝያስ ወንድሞች ጋር ተገናኝቶ “እናንተ እነማን ናችሁ?” አለ። እነርሱም “እኛ የአካዝያስ ወንድሞች ነን፤ የንጉሡንና የእቴጌይቱን ልጆች ደኅንነት ለመጠየቅ እንወርዳለን፤” አሉት።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 10:13
8 Cross References  

ንጉ​ሡም ኢዮ​ራም ከሶ​ርያ ንጉሥ ከአ​ዛ​ሄል ጋር በተ​ዋጋ ጊዜ ሶር​ያ​ው​ያን በሬ​ማት ያቈ​ሰ​ሉ​ትን ቍስል ይታ​ከም ዘንድ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ተመ​ለሰ። የአ​ክ​ዓ​ብም ልጅ ኢዮ​ራም ታምሞ ነበ​ርና የኢ​ዮ​ራም ልጅ አካ​ዝ​ያስ ሊያ​የው ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ወረደ።


ኢዮ​ራ​ምም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ተቀ​በረ፤ በፋ​ን​ታ​ውም ልጁ አካ​ዝ​ያስ ነገሠ።


ወደ ይሁ​ዳም ወጡ፤ በረ​ቱ​ባ​ቸ​ውም፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ወን​ዶች ልጆ​ቹ​ንም፥ ሴቶች ልጆ​ቹ​ንም ወሰዱ፤ ከታ​ና​ሹም ልጅ ከአ​ካ​ዝ​ያስ በቀር ልጅ አል​ቀ​ረ​ለ​ትም።


ተነ​ሥ​ቶም ወደ ሰማ​ርያ ሄደ፤ በመ​ን​ገ​ድም ወዳ​ለው ወደ በግ ጠባ​ቂ​ዎች ቤት በደ​ረሰ ጊዜ፥


እር​ሱም፥ “በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው ያዙ​አ​ቸው” ብሎ አዘዘ። በበግ ጠባ​ቂ​ዎች ቤትም አጠ​ገብ አርባ ሁለ​ቱን ሰዎች ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ ሰው እንኳ አላ​ስ​ቀ​ረም።


ጢማ​ቸ​ውን ላጭ​ተው፥ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም ቀድ​ደው እያ​ለ​ቀሱ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ያቀ​ርቡ ዘንድ የእ​ህል ቍር​ባ​ንና ዕጣን በእ​ጃ​ቸው የያዙ፥ ሰማ​ንያ ሰዎች ከሴ​ኬ​ምና ከሴሎ፥ ከሰ​ማ​ር​ያም መጡ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements