Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 1:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 አካ​ዝ​ያ​ስም በሰ​ማ​ርያ በሰ​ገ​ነቱ ላይ ሳለ በዐ​ይነ ርግቡ ወድቆ ታመመ፤ እር​ሱም፥ “ሂዱ፥ ከዚህ ደዌ እድን እንደ ሆነ የአ​ቃ​ሮ​ንን አም​ላክ ብዔ​ል​ዜ​ቡ​ልን ጠይቁ” ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እነ​ር​ሱም ሊጠ​ይ​ቁ​ለት ሄዱ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 በዚህ ጊዜ አካዝያስ በሰማርያ ካለው እልፍኝ ሰገነቱ ላይ ሳለ፣ ከዐይነ ርግቡ ሾልኮ ወድቆ ነበርና ታመመ፤ ስለዚህ፣ “ሄዳችሁ ከዚህ ሕመም እድን እንደ ሆነ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ጠይቁ” ሲል መልእክተኞች ላከ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በዚህም ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ አካዝያስ በሰማርያ ቤተ መንግሥቱ ሳለ ከሰገነቱ ላይ ወድቆ በብርቱ ስለ ቆሰለ ታሞ ነበር፤ እርሱም “እኔ ከዚህ ሕመም እድን ወይም አልድን እንደሆነ በፍልስጥኤም የዔክሮን ከተማ አምላክ የሆነውን ብዔልዜቡልን ጠይቃችሁልኝ ኑ” ብሎ መልእክተኞቹን ላከ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 በዚህም ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ አካዝያስ በሰማርያ ቤተ መንግሥቱ ሳለ ከሰገነቱ ላይ ወድቆ በብርቱ ስለ ቈሰለ ታሞ ነበር፤ እርሱም “እኔ ከዚህ ሕመም እድን ወይም አልድን እንደ ሆነ በፍልስጥኤም የዔክሮን ከተማ አምላክ የሆነውን ብዔልዜቡልን ጠይቃችሁልኝ ኑ” ብሎ መልእክተኞቹን ላከ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 አካዝያስም በሰማርያ በሰገነቱ ላይ ሳለ ከዐይነ ርግቡ ወድቆ ታመመ፤ እርሱም “ሂዱ፤ ከዚህም ደዌ እድን እንደ ሆነ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ጠይቁ፤” ብሎ መልእክተኞችን ላከ።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 1:2
25 Cross References  

ኤል​ያ​ስም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የአ​ቃ​ሮ​ንን አም​ላክ ብዔ​ል​ዜ​ቡ​ልን ትጠ​ይቅ ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ለምን ላክህ? በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አም​ላክ ስለ​ሌለ ነውን? እን​ደ​ዚህ አይ​ደ​ለም፤ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ ከወ​ጣ​ህ​በት አልጋ አት​ወ​ር​ድም” አለው።


ከኢየሩሳሌም የወረዱ ጻፎችም “ብዔል ዜቡል አለበት፤” ደግሞ “በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል፤” ብለው ተናገሩ።


ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው!


አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት አቃ​ጥ​ለ​ዋል፤ የእ​ን​ጨ​ትና የድ​ን​ጋይ የሰው እጅ ሥራም ነበሩ እንጂ አማ​ል​ክት አል​ነ​በ​ሩ​ምና ስለ​ዚህ አጥ​ፍ​ተ​ዋ​ቸ​ዋል።


ነገር ግን ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው፥ “በአ​ጋ​ን​ንት አለቃ በብ​ዔል ዜቡል አጋ​ን​ን​ትን ያወ​ጣ​ቸ​ዋል” ያሉ ነበሩ፤ እር​ሱም መልሶ፥ “ሰይ​ጣን ሰይ​ጣ​ንን ማው​ጣት እን​ደ​ምን ይቻ​ለ​ዋል?” አላ​ቸው።


አባ​ቶች ያጠ​ፉ​አ​ቸ​ውን በቴ​ማን ያሉ​ትን ጎዛ​ን​ንና ካራ​ንን፥ ራፌ​ስ​ንም የአ​ሕ​ዛብ አማ​ል​ክት አዳ​ኑ​አ​ቸ​ውን?


እነ​ር​ሱም፥ “አንድ ሰው ሊገ​ና​ኘን መጣና፦ ሂዱ፤ ወደ ላካ​ችሁ ንጉሥ ተመ​ል​ሳ​ችሁ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የአ​ቃ​ሮ​ንን አም​ላክ ብዔ​ል​ዜ​ቡ​ልን ትጠ​ይቅ ዘንድ የላ​ክህ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አም​ላክ ስለ​ሌለ ነውን? ስለ​ዚህ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ ከወ​ጣ​ህ​በት አልጋ አት​ወ​ር​ድም በሉት አለን” አሉት።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ቴስ​ብ​ያ​ዊ​ውን ኤል​ያ​ስን ጠርቶ፥ “ተነሣ፤ የሰ​ማ​ር​ያን ንጉሥ መል​እ​ክ​ተ​ኞች ለመ​ገ​ና​ኘት ሂድና፦ የአ​ቃ​ሮ​ንን አም​ላክ ብዔ​ል​ዜ​ቡ​ልን ትጠ​ይቁ ዘንድ የም​ት​ሄ​ዱት በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አም​ላክ ስለ​ሌለ ነውን?


ትቶ​ኛ​ልና፥ ለሲ​ዶ​ና​ው​ያ​ንም ርኵ​ሰት ለአ​ስ​ጠ​ራ​ጢስ፥ ለሞ​አ​ብም አም​ላክ ለኮ​ሞስ፥ ለአ​ሞ​ንም ልጆች አም​ላክ ለሞ​ሎክ ሰግ​ዶ​አ​ልና፥ አባ​ቱም ዳዊት እን​ዳ​ደ​ረገ በፊቴ ቅን ነገ​ርን ያደ​ርግ ዘንድ በመ​ን​ገ​ዶቼ አል​ሄ​ደ​ምና።


ስሙ አው​ጤ​ክስ የሚ​ባል አንድ ጐል​ማሳ ልጅም በመ​ስ​ኮት በኩል ተቀ​ምጦ ሳለ ከባድ እን​ቅ​ልፍ አን​ቀ​ላ​ፍቶ ነበር፤ ጳው​ሎ​ስም ትም​ህ​ር​ቱን ባስ​ረ​ዘመ ጊዜ ያ ጐል​ማሳ ከእ​ን​ቅ​ልፉ ብዛት የተ​ነሣ ከተ​ኛ​በት ከሦ​ስ​ተ​ኛው ፎቅ ወደ ታች ወደቀ፤ ሬሳ​ው​ንም አነ​ሡት።


ልጅ ወን​ድሜ በቤ​ቴል ተራ​ሮች ላይ ሚዳ​ቋን ወይም የዋ​ሊ​ያን እን​ም​ቦሳ ይመ​ስ​ላል፤ እነሆ፥ በመ​ስ​ኮ​ቶች ሲጐ​በኝ፥ በዐ​ይነ ርግ​ብም ሲመ​ለ​ከት፥ እርሱ ከቅ​ጥ​ራ​ችን በኋላ ቆሞ​አል።


ሞት ለዐ​መ​ፀኛ፥ መለ​የ​ትም ኀጢ​አ​ትን ለሚ​ሠሩ ነው።


አንድ ሰውም ቀስ​ቱን ድን​ገት ገትሮ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ በሳ​ን​ባ​ውና በደ​ረቱ መካ​ከል ወጋው፤ ሰረ​ገ​ለ​ኛ​ው​ንም፥ “መል​ሰህ ንዳ፤ ተወ​ግ​ቻ​ለ​ሁና ከሰ​ልፍ ውስጥ አው​ጣኝ” አለው።


በእ​ጅ​ሽም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ዐሥር እን​ጀ​ራና የወ​ይን እሸት አን​ድም ማሠሮ ማር ይዘሽ ወደ እርሱ ሂጂ፤ በል​ጁም የሚ​ሆ​ነ​ውን ይነ​ግ​ር​ሻል” አላት።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት ወደ አስ​ቀ​ሎና ላኩ​አት። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ወደ አስ​ቀ​ሎና በመ​ጣች ጊዜ አስ​ቀ​ሎ​ና​ው​ያን፥ “እኛ​ንና ሕዝ​ባ​ች​ንን ልታ​ስ​ገ​ድ​ሉን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ ታቦት ለምን አመ​ጣ​ች​ሁ​ብን?” ብለው ጮኹ።


አም​ላ​ክህ ኮሞስ የሚ​ሰ​ጥ​ህን የም​ት​ወ​ርስ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን? እኛም አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፊ​ታ​ችን ያስ​ወ​ጣ​ቸ​ውን የእ​ነ​ር​ሱን ምድር የም​ን​ወ​ርስ አይ​ደ​ለ​ን​ምን?


የሲ​ሣራ እናት በመ​ስ​ኮት ሆና ተመ​ለ​ከ​ተች፤ በሰ​ቅ​ሰ​ቅም ዘልቃ፦ ከሲ​ሣራ የተ​መ​ለሰ እን​ዳለ አየች፤ ስለ​ምን ለመ​ም​ጣት ሰረ​ገ​ላው ዘገየ? ስለ​ም​ንስ የሰ​ረ​ገ​ላው መን​ኰ​ራ​ኵር ቈየ? ብላ ጮኸች።


ሕዝ​ቡን የያ​ዕ​ቆ​ብን ቤት ትቶ​አ​ልና፤ ምድ​ራ​ቸው እንደ ቀድ​ሞው እንደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ምድር በሟ​ርት ተሞ​ል​ቶ​አ​ልና፤ እንደ ባዕድ ልጆ​ችም ሆነ​ዋ​ልና፤ ብዙ እን​ግ​ዶች ልጆ​ችም ተወ​ል​ደ​ው​ላ​ቸ​ዋ​ልና።


ድን​በ​ሩም ወደ አቃ​ሮን ደቡብ ይወ​ጣል፤ ወደ ሰሜን ወገን ይመ​ለ​ሳል፤ ድን​በሩ ወደ ሰቆት ይወ​ጣል፤ ወደ ደቡ​ብም ያል​ፋል፤ በሌ​ብና በኩ​ልም ይወ​ጣል፤ የድ​ን​በ​ሩም መውጫ በባ​ሕሩ አጠ​ገብ ነበረ።


አክ​ዓ​ብም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ልጁ አካ​ዝ​ያስ ነገሠ።


የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ሁሉ ተዉ፤ ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ት​ንም የሁ​ለ​ቱን እን​ቦ​ሶች ምስ​ሎች አደ​ረጉ፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ድ​ንም ተከሉ፤ ለሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ ሰገዱ፤ በዓ​ል​ንም አመ​ለኩ።


የግ​ብ​ፅም መን​ፈስ በው​ስ​ጣ​ቸው ትደ​ነ​ግ​ጣ​ለች፤ ምክ​ራ​ቸ​ውን አጠ​ፋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንና ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ ድም​ፃ​ቸ​ውን ዝቅ አድ​ር​ገው የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይጠ​ይ​ቃሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements