Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 1:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ኤል​ያ​ስን፥ “ከእ​ርሱ ጋር ውረድ፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ አት​ፍራ” ብሎ ነገ​ረው። ኤል​ያ​ስም ተነ​ሥቶ ከእ​ርሱ ጋር ወደ ንጉሡ ወረደ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 የእግዚአብሔርም መልአክ ኤልያስን፣ “ዐብረኸው ውረድ፤ ደግሞም አትፍራው” አለው። ስለዚህ ኤልያስ ተነሣ፤ ዐብሮትም ወደ ንጉሡ ወረደ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በዚህም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ኤልያስን “ከእርሱ ጋር አብረህ ውረድ፤ ከቶም አትፍራ” አለው። ስለዚህም ኤልያስ ከመኰንኑ ጋር ወደ ንጉሡ ወረደ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 በዚህም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ኤልያስን “ከእርሱ ጋር አብረህ ውረድ፤ ከቶም አትፍራ” አለው። ስለዚህም ኤልያስ ከመኰንኑ ጋር ወደ ንጉሡ ወረደ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የእግዚአብሔርም መልአክ ኤልያስን “ከእርሱ ጋር ውረድ፤ አትፍራውም፤” አለው። ተነሥቶም ከእርሱ ጋር ወደ ንጉሡ ወረደ።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 1:15
11 Cross References  

እኔ ነኝ፤ የማ​ጽ​ና​ናሽ እኔ ነኝ፤ አንቺ እን​ግ​ዲህ ዕወቂ፤ ማንን ፈራሽ? የሚ​ሞ​ተ​ውን ሰው እንደ ሣርም የሚ​ጠ​ወ​ል​ገ​ውን የሰው ልጅ ነውን?


አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ኩር​ን​ች​ትና እሾህ ከአ​ንተ ጋር ቢኖ​ሩም፥ አን​ተም በጊ​ን​ጦች መካ​ከል ብት​ቀ​መጥ፥ አት​ፍ​ራ​ቸው፤ ቃላ​ቸ​ው​ንም አት​ፍራ፤ አንተ ቃላ​ቸ​ውን አት​ፍራ፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ አት​ደ​ን​ግጥ፤ እነ​ርሱ ዐመ​ፀኛ ቤት ናቸ​ውና።


አንተ ግን ወገ​ብ​ህን ታጠቅ፤ ተነ​ሥም፤ ያዘ​ዝ​ሁ​ህ​ንም ሁሉ ንገ​ራ​ቸው፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ አት​ፍራ። በፊ​ታ​ቸ​ውም አት​ደ​ን​ግጥ አድ​ንህ ዘንድ እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።


ለዚ​ህም ሕዝብ የተ​መ​ሸገ የናስ ቅጥር አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፤ ይዋ​ጉ​ሃል፤ እኔ ግን ለማ​ዳን ከአ​ንተ ጋር ነኝና አያ​ሸ​ን​ፉ​ህም።


አቤቱ፥ አም​ላኬ ሆይ፥ ወደ አንተ እጮ​ኻ​ለሁ፤ ቸልም አት​በ​ለኝ። ቸል ብት​ለኝ ግን ወደ ጕድ​ጓድ እን​ደ​ሚ​ወ​ር​ዱት እሆ​ና​ለሁ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ቴስ​ብ​ያ​ዊ​ውን ኤል​ያ​ስን ጠርቶ፥ “ተነሣ፤ የሰ​ማ​ር​ያን ንጉሥ መል​እ​ክ​ተ​ኞች ለመ​ገ​ና​ኘት ሂድና፦ የአ​ቃ​ሮ​ንን አም​ላክ ብዔ​ል​ዜ​ቡ​ልን ትጠ​ይቁ ዘንድ የም​ት​ሄ​ዱት በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አም​ላክ ስለ​ሌለ ነውን?


ኤል​ያ​ስም፥ “በፊቱ የቆ​ም​ሁት የሠ​ራ​ዊት ጌታ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! እኔ ዛሬ ለእ​ርሱ እገ​ለ​ጣ​ለሁ” አለው።


ከዚ​ህም ነገር በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በራ​እይ ወደ አብ​ራም መጣ፤ እን​ዲህ ሲል፥ “አብ​ራም ሆይ፥ አት​ፍራ፤ እኔ ጋሻ እሆ​ን​ሃ​ለሁ፤ ዋጋ​ህም በእኔ ዘንድ እጅግ ብዙ ነው።”


የን​ጉ​ሡ​ንም ቍጣ ሳይ​ፈራ፥ የግ​ብ​ፅን ሀገር በእ​ም​ነት ተወ፤ ከሚ​ያ​የው ይልቅ የማ​ይ​ታ​የ​ውን ሊፈራ ወዶ​አ​ልና።


እነሆ፥ እሳት ከሰ​ማይ ወርዳ የፊ​ተ​ኞ​ቹን ሁለ​ቱን የአ​ምሳ አለ​ቆ​ችና አምሳ አም​ሳ​ውን ሰዎ​ቻ​ቸ​ውን በላች፤ አሁን ግን ነፍሴ በፊ​ትህ የከ​በ​ረች ትሁን።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements