Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ቆሮንቶስ 9:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ስለ​ዚ​ህም አስ​ቀ​ድ​መው ወደ እና​ንተ መጥ​ተው በቅ​ድ​ሚያ የተ​ና​ገ​ራ​ች​ኋ​ትን በረ​ከ​ታ​ች​ሁን እን​ዲ​ያ​ዘ​ጋጁ ወን​ድ​ሞ​ችን ማለ​ድሁ፤ እን​ደ​ዚ​ህም የተ​ዘ​ጋጀ ይሁን፤ በረ​ከ​ትን እን​ደ​ም​ታ​ገ​ኙ​በት እንጂ በን​ጥ​ቂያ እንደ ተወ​ሰ​ደ​ባ​ችሁ አይ​ሁን።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ስለዚህ ወንድሞች አስቀድመው ወደ እናንተ እንዲመጡና ከዚህ በፊት ለመስጠት ቃል የገባችሁትን ስጦታ አጠናቅቃችሁ እንድትጠብቋቸው፣ እነርሱን መለመን አስፈላጊ ሆኖ አግኝቻለሁ፤ እንግዲህ በልግስና ለመስጠት ያሰባችሁት ነገር በግዴታ ሳይሆን በፈቃደኝነት የተዘጋጀ ይሆናል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እንግዲህ ዝግጁ እንድትሆኑ ወንድሞች አስቀድመው ወደ እናንተ መጥተው፥ አስቀድማችሁ ተስፋ የሰጣችሁትን የልግስና ስጦታ እንደ ግዴታ ሳይሆን በበጎ ፈቃደኝነት ቀደም ብለው እንዲያዘጋጁ፥ እነርሱን መለመን አስፈላጊ መሆኑን አስቤበታለሁ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ስለዚህ ልትሰጡ ቃል የገባችሁበትን የልግሥና ስጦታችሁ በቅድሚያ እንድታዘጋጁ እንዲያስታውሱአችሁ በማለት እነዚህ ወንድሞች ከእኔ ቀድመው ወደ እናንተ እንዲመጡ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፤ በዚህ ዐይነት እኔ በምመጣበት ጊዜ የልግሥና ስጦታችሁ ዝግጁ ይሆናል፤ እናንተም የምትሰጡት በግድ ሳይሆን በፈቃደኛነት መሆኑን ያሳያል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እንግዲህ እንደ በረከት ሆኖ ከስስት የማይሆን ይህ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ አስቀድመው ወደ እናንተ መጥተው፥ አስቀድማችሁ ተስፋ የሰጣችሁትን በረከት አስቀድመው እንዲፈጽሙ ወንድሞችን እለምን ዘንድ እንዲያስፈልገኝ አሰብሁ።

See the chapter Copy




2 ቆሮንቶስ 9:5
11 Cross References  

አሁ​ንም ባሪ​ያህ ወደ ጌታዬ ያመ​ጣ​ች​ውን ይህን መተ​ያያ ተቀ​በል፤ በጌ​ታ​ዬም ዘንድ ለሚ​ቆሙ ሰዎች ስጣ​ቸው።


ከወ​ደ​ድ​ኸ​ኝስ ይህ​ችን ያመ​ጣ​ሁ​ል​ህን በረ​ከ​ቴን ተቀ​በል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራር​ቶ​ል​ኛ​ልና፥ ለእ​ኔም ብዙ አለ​ኝና።” እስ​ኪ​ቀ​በ​ለ​ውም ድረስ ግድ አለው፤ ተቀ​በ​ለ​ውም።


ይህ​ንም የማ​ነ​ሣ​ሣው ስጦ​ታ​ች​ሁን ፈልጌ አይ​ደ​ለም፤ በእ​ና​ንተ ላይ የጽ​ድቅ ፍሬ ይበዛ ዘንድ ፈልጌ ነው እንጂ።


ይህ​ንም የቸ​ር​ነት ሥራ እንደ ጀመረ ይፈ​ጽ​ም​ላ​ችሁ ዘንድ ቲቶን ማለ​ድ​ነው።


እኔ ስመጣ ይህ የገ​ን​ዘብ ማዋ​ጣት ያን​ጊዜ እን​ዳ​ይ​ሆን፥ ከእ​ና​ንተ ሰው ሁሉ በየ​ሳ​ም​ንቱ እሑድ የተ​ቻ​ለ​ውን ያወ​ጣጣ፤ ያገ​ኘ​ው​ንም በቤቱ ይጠ​ብቅ።


እር​ሱም ከጭ​ፍ​ራው ሁሉ ጋር ወደ ኤል​ሳዕ ተመ​ለሰ፤ ወደ እር​ሱም ደርሶ በፊቱ ቆመና፥ “እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነው እንጂ በም​ድር ሁሉ አም​ላክ እን​ደ​ሌለ ዐወ​ቅሁ፤ አሁ​ንም ከአ​ገ​ል​ጋ​ይህ በረ​ከት ተቀ​በል” አለው።


ዳዊ​ትም ወደ ሴቄ​ላቅ በመጣ ጊዜ ለይ​ሁዳ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ለወ​ዳ​ጆቹ፥ “እነሆ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶች ምርኮ በረ​ከ​ትን ተቀ​በሉ” ብሎ ከም​ር​ኮው ላከ​ላ​ቸው።


ዓስ​ካም፥ “በረ​ከ​ትን ስጠኝ፤ ወደ ደቡብ በረሃ ሰድ​ደ​ኸ​ኛ​ልና ውኃ የማ​ጣ​ቴን ዋጋ ደግሞ ስጠኝ” አለ​ችው። ካሌ​ብም በል​ብዋ እንደ ተመ​ኘ​ችው የመ​ከ​ራ​ዋ​ንና የኀ​ዘ​ኗን ዋጋ ሰጣት።


በዚ​ህም ያመ​ሰ​ገ​ን​ና​ችሁ ምስ​ጋና በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ሐሰት እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ብን፥ እንደ ነገ​ር​ና​ቸ​ውም ተዘ​ጋ​ጅ​ታ​ችሁ እን​ዲ​ያ​ገ​ኙ​አ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ችን ወደ እና​ንተ ላክ​ና​ቸው።


አሳ​ንሶ የሚ​ዘራ ለእ​ርሱ እን​ዲሁ መከሩ ያን​ስ​በ​ታል፤ በብዙ የሚ​ዘራ ግን በብዙ ያመ​ር​ታል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements