Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ቆሮንቶስ 8:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ለቅ​ዱ​ሳን ስለ​ሚ​ሆ​ነው አገ​ል​ግ​ሎት እን​ዲ​ተ​ባ​በሩ ይህን ቸር​ነት መላ​ል​ሰው ማለ​ዱን።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እነርሱም ቅዱሳንን ለመርዳት በሚደረገው አገልግሎት ለመሳተፍ ዕድል ያገኙ ዘንድ አጥብቀው ይለምኑን ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ለቅዱሳን በሚደረገው አገልግሎት እነርሱም ተሳታፊ የመሆንን ጸጋ እንዲያገኙ እኛን አጥብቀው ይለምኑ ነበር፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በይሁዳ ያሉትን ክርስቲያኖች የመርዳት ዕድል እንዳይነፈጋቸውም አጥብቀው ለመኑን፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ለቅዱሳን በሆነው አገልግሎት እንዲተባበሩ ይህን ቸርነት በብዙ ልመና ከእኛ ይለምኑ ነበር፥

See the chapter Copy




2 ቆሮንቶስ 8:4
27 Cross References  

ከብዙ ዓመ​ታ​ትም በኋላ ለወ​ገ​ኖች ምጽ​ዋ​ት​ንና መሥ​ዋ​ዕ​ትን ላደ​ርግ መጣሁ።


እን​ግ​ዲህ ጊዜ ሳለን ለሁሉ መል​ካም ሥራ እና​ድ​ርግ፤ ይል​ቁ​ንም ለሃ​ይ​ማ​ኖት ሰዎች።


ለቅ​ዱ​ሳን ስለ​ሚ​ደ​ረ​ገው አገ​ል​ግ​ሎት የም​ጽ​ፍ​ላ​ችሁ ብዙ አለኝ


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱ​ሳ​ንን ስለ አገ​ለ​ገ​ላ​ችሁ፥ እስከ አሁ​ንም ስለ​ም​ታ​ገ​ለ​ግ​ሉ​አ​ቸው ያደ​ረ​ጋ​ች​ት​ሁን ሥራ፥ በስ​ሙም ያሳ​ያ​ች​ሁ​ትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዐመ​ፀኛ አይ​ደ​ለ​ምና።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ የእ​ስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስና የፈ​ር​ዶ​ና​ጥስ፥ የአ​ካ​ይ​ቆ​ስም ቤተ​ሰ​ቦች፥ የአ​ካ​ይያ መጀ​መ​ሪ​ያ​ዎች እንደ ሆኑ፥ ቅዱ​ሳ​ን​ንም ለማ​ገ​ል​ገል ራሳ​ቸ​ውን እንደ ሰጡ ታውቁ ዘንድ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።


ይል​ቁ​ንም ነዳ​ያ​ንን እን​ድ​ና​ስ​ባ​ቸው ነው፤ ስለ​ዚ​ህም ይህን ነገር ልፈ​ጽ​መው ተጋሁ።


ልጆችን በማሳደግ፥ እንግዶችንም በመቀበል፥ የቅዱሳንንም እግሮች በማጠብ፥ የተጨነቁትንም በመርዳት፥ በጎንም ሥራ ሁሉ በመከተል፥ ይህን መልካም ሥራ በማድረግ የተመሰከረላት ልትሆን ይገባል።


ለቅ​ዱ​ሳን ስለ​ሚ​ደ​ረ​ገው አስ​ተ​ዋ​ፅኦ በገ​ላ​ትያ ላሉት ምእ​መ​ናን እንደ ደነ​ገ​ግ​ሁት እና​ን​ተም እን​ዲሁ አድ​ርጉ።


ይኸ​ውም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያሉ ቅዱ​ሳ​ንን በአ​ገ​ል​ግ​ሎቴ ደስ አሰ​ና​ቸው ዘንድ በይ​ሁዳ ሀገር ካሉ ዐላ​ው​ያን እን​ዲ​ያ​ድ​ነኝ ነው።


እር​ስ​ዋም ከቤተ ሰቦ​ችዋ ጋር ተጠ​መ​ቀች፤ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አማኝ ካደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ኝስ ወደ ቤቴ ገብ​ታ​ችሁ እደሩ” ብላ ማለ​ደ​ችን፤ የግ​ድም አለ​ችን።


ከዚ​ህም በኋላ ደቀ መዛ​ሙ​ርት እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው የሚ​ች​ሉ​ትን ያህል አወ​ጣ​ጥ​ተው በይ​ሁዳ ሀገር ለሚ​ኖ​ሩት ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ርዳ​ታን ይልኩ ዘንድ ወሰኑ።


ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉና፤ በማናቸውም በወደዳችሁት ጊዜ መልካም ልታደርጉላቸው ትችላላችሁ፤ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም።


ንጉሡም መልሶ ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት፤’ ይላቸዋል።


በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ እኅቴም እናቴም ነውና፤” አለ።


ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements