Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ቆሮንቶስ 7:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 አሁ​ንም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ታገ​ሡን፥ የበ​ደ​ል​ነው የለም፤ የገ​ፋ​ነ​ውም የለም፤ ያጠ​ፋ​ነ​ውም የለም፤ የቀ​ማ​ነ​ውም የለም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ልባችሁን አስፉልን፤ እኛ ማንንም አልበደልንም፤ ማንንም ወደ ብልሹነት አልመራንም፤ ማንንም አላታለልንም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በልባችሁ ስፍራ አኑሩን፤ ማንንም አልበደልንም፤ ማንንም አላጭበረበርንም፤ ማንንም መጠቀሚያ አላደረግንም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ከልባችሁ ተቀበሉን፤ እኛ ማንንም አልበደልንም፤ ማንንም አልጐዳንም፤ ማንንም መጠቀሚያ አላደረግንም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በልባችሁ ስፍራ አስፉልን፤ ማንንም አልበደልንም፥ ማንንም አላጠፋንም፥ ማንንም አላታለልንም።

See the chapter Copy




2 ቆሮንቶስ 7:2
23 Cross References  

ከእ​ና​ንተ ዘንድ በነ​በ​ር​ሁ​በት ጊዜም፥ ስቸ​ገር ገን​ዘ​ባ​ች​ሁን አል​ተ​መ​ኘ​ሁም። ባል​በ​ቃ​ኝም ጊዜ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ከመ​ቄ​ዶ​ንያ መጥ​ተው አሙ​አ​ሉ​ልኝ፤ በእ​ና​ን​ተም ላይ እን​ዳ​ል​ከ​ብ​ድ​ባ​ችሁ በሁሉ ተጠ​ነ​ቀ​ቅሁ፤ ወደ ፊትም እጠ​ነ​ቀ​ቃ​ለሁ።


ወር​ቅም ቢሆን፥ ብርም ቢሆን፥ ልብ​ስም ቢሆን ከእ​ና​ንተ ከአ​ንዱ ስንኳ አል​ተ​መ​ኘ​ሁም።


ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ ይህንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት፤ ሰላምም አትበሉት፤


እነ​ርሱ ለጌ​ታ​ችን ለኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ያይ​ደለ ለሆ​ዳ​ቸው ይገ​ዛ​ሉና፤ በነ​ገር ማታ​ለ​ልና በማ​ለ​ዛ​ዘ​ብም የብ​ዙ​ዎች የዋ​ሃ​ንን ልብ ያስ​ታሉ፤


“እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።


ከማይቀበላችሁም ቃላችሁንም ከማይሰሙ ሁሉ፥ ከዚያ ቤት ወይም ከዚያች ከተማ ስትወጡ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉ።


ሙሴም እጅግ አዘነ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አለው፥ “ወደ መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸው አት​መ​ል​ከት፤ እኔ ከእ​ነ​ርሱ አን​ዳ​ችም ተመ​ኝቼ አል​ወ​ሰ​ድ​ሁም፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ ሰው አል​በ​ደ​ል​ሁም።”


እንግዲህ እንደ ባልንጀራ ብትቈጥረኝ፥ እንደ እኔ አድርገህ ተቀበለው።


እርሱን እልከዋለሁ፤ አንተም ልቤ እንደሚሆን ተቀበለው።


በእናንተ በምታምኑ ዘንድ እንዴት ባለ ቅድስናና ጽድቅ ነቀፋም በሌለበት ኑሮ እንደ ሄድን፥ እናንተና እግዚአብሔር ምስክሮች ናችሁ፤


ከእኔ ጋር የተ​ማ​ረ​ከው አር​ስ​ጥ​ሮ​ኮስ፥ ወደ እና​ንተ በሚ​መጣ ጊዜ ትቀ​በ​ሉት ዘንድ ስለ እርሱ ያዘ​ዝ​ኋ​ችሁ የበ​ር​ና​ባስ የአ​ባቱ ወን​ድም ልጅ ማር​ቆ​ስም፥


እን​ግ​ዲህ በጌ​ታ​ችን በፍ​ጹም ደስታ ተቀ​በ​ሉት፤ እን​ደ​ዚህ ያሉ​ት​ንም ሁሉ አክ​ብ​ሩ​አ​ቸው።


ደግ​ሞም እን​ዲህ እላ​ለሁ፦ ሰነፍ የሚ​ያ​ደ​ር​ገኝ አይ​ኑር፤ ያውም ብሆን እኔ ጥቂት እመካ ዘንድ እንደ ሰነፍ እንኳ ብሆን ተቀ​በ​ሉኝ።


ነገር ግን በስ​ውር የሚ​ሠ​ራ​ውን አሳ​ፋሪ ሥራ እን​ተ​ወው፤ በተ​ን​ኰ​ልም አን​መ​ላ​ለስ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል በው​ሸት አን​ቀ​ላ​ቅል፤ ለሰ​ውም ሁሉ አር​አያ ስለ መሆን እው​ነ​ትን ገል​ጠን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ራሳ​ች​ንን እና​ጽና።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር​ነ​ትና ይቅ​ርታ መመ​ኪ​ያ​ች​ንና የነ​ፃ​ነ​ታ​ችን ምስ​ክር ይህቺ ናትና፥ በሥ​ጋዊ ጥበብ ሳይ​ሆን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ በዚህ ዓለም፥ ይል​ቁ​ንም በእ​ና​ንተ ዘንድ ተመ​ላ​ለ​ስን።


ወደ ማና​ቸ​ውም ከተማ ብት​ገቡ፥ የዚያ ከተማ ሰዎ​ችም ቢቀ​በ​ሉ​አ​ችሁ ያቀ​ረ​ቡ​ላ​ች​ሁን ብሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements