Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ቆሮንቶስ 5:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ታም​ነ​ናል፤ ይል​ቁ​ንም ከሥ​ጋ​ችን ተለ​ይ​ተን ወደ ጌታ​ችን እን​ሄ​ዳ​ለ​ንና ደስ ይለ​ናል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ከሥጋ ተለይተን ከጌታ ጋራ መኖርን እንደምንመርጥ ርግጠኛ ሆኜ እናገራለሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 አዎ፥ ታምነናል፤ ይልቁንም ከሥጋ ተለይተን በጌታ ዘንድ መኖር እንመርጣለን።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ከዚህ እንደ መኖሪያችን ከሆነው ሥጋችን ተለይተን ከጌታ ጋር ለመሆን እንመኛለን፤ ስለዚህ በመተማመን እንኖራለን።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ታምነናል ይልቁንም ከሥጋ ተለይተን በስደት መኖር በጌታም ዘንድ ማደር ደስ ይለናል።

See the chapter Copy




2 ቆሮንቶስ 5:8
22 Cross References  

እን​ግ​ዲህ ሁል​ጊዜ እመኑ፥ ጨክ​ኑም፤ በዚህ ሥጋ ሳላ​ች​ሁም እና​ንተ እን​ግ​ዶች እንደ ሆና​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ከሥ​ጋ​ች​ሁም ተለ​ይ​ታ​ችሁ ወደ ጌታ​ችን ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ።


ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን።


ከሄ​ድ​ሁና ቦታ ካዘ​ጋ​ጀ​ሁ​ላ​ች​ሁም ዳግ​መኛ እመ​ጣ​ለሁ፤ እና​ን​ተም እኔ በአ​ለ​ሁ​በት ትኖሩ ዘንድ ወደ እኔ እወ​ስ​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።


አሁ​ንም ብን​ኖ​ርም፥ ብን​ሞ​ትም እር​ሱን ደስ ለማ​ሰ​ኘት እን​ጥ​ራ​ለን።


አቤቱ፥ ከተ​ግ​ሣ​ጽህ፥ ከመ​ዓ​ት​ህም መን​ፈስ እስ​ት​ን​ፋስ የተ​ነሣ፥ የው​ኆች ምን​ጮች ታዩ፥ የዓ​ለም መሠ​ረ​ቶ​ችም ተገ​ለጡ።


አሁ​ንም አባ​ረ​ሩኝ፤ ከበ​ቡ​ኝም፤ ዐይ​ና​ቸ​ው​ንም ወደ ምድር ዝቅ ዝቅ አደ​ረጉ።


ከእንግዲህም ወዲህ መርገም ከቶ አይሆንም። የእግዚአብሔርና የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ ይሆናል፤ ባሪያዎቹም ያመልኩታል፤ ፊቱንም ያያሉ፤


ጳው​ሎስ ግን መልሶ፥ “ለምን እን​ዲህ ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ? እያ​ለ​ቀ​ሳ​ችሁ ልቤን ትሰ​ብ​ሩ​ታ​ላ​ችሁ፤ እኔ እኮ ተስፋ የማ​ደ​ር​ገው መከ​ራ​ንና እግር ብረ​ትን ብቻ አይ​ደ​ለም፤ እኔ ግን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለመ​ሞ​ትም ቢሆን የቈ​ረ​ጥሁ ነኝ” አለ።


አባት ሆይ፥ የሰ​ጠ​ኸኝ እነ​ዚህ እኔ ባለ​ሁ​በት አብ​ረ​ውኝ ይኖሩ ዘን​ድና የሰ​ጠ​ኸ​ኝን ክብ​ሬን ያዩ ዘንድ እወ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ዓለም ሳይ​ፈ​ጠር ወድ​ደ​ኸ​ኛ​ልና።


እን​ዲ​ህም አለ፤ “አቤቱ፥ እንደ አዘ​ዝህ ዛሬ ባር​ያ​ህን በሰ​ላም ታሰ​ና​ብ​ተ​ዋ​ለህ።


ጌታውም ‘መልካም፥ አንተ በጎ፥ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፤ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ፤’ አለው።


ጌታውም ‘መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፥ በጥቂቱ ታምነሃል፤ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ፤’ አለው።


ኃጥእ በክፋቱ ይወገዳል፤ በቸርነቱ የሚታመን ግን ጻድቅ ነው።


እኔን የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ለኝ ካለ ይከ​ተ​ለኝ፤ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ለኝ እኔ ባለ​ሁ​በት በዚያ ይኖ​ራ​ልና፤ እኔን የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ለ​ኝ​ንም አብ ያከ​ብ​ረ​ዋል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements