Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ቆሮንቶስ 5:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እኛ ሰነ​ፎች ብን​ሆ​ንም፥ ስን​ፍ​ና​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ዐዋ​ቂ​ዎች ብን​ሆ​ንም ዐዋ​ቂ​ነ​ታ​ችን ለእ​ና​ንተ ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ከአእምሮ ውጭ ብንሆን ለእግዚአብሔር ብለን ነው፤ ባለአእምሮም ብንሆን ለእናንተ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 አእምሮችንን የሳትን ብንሆን፥ የሳትነው ለእግዚአብሔር ነው፤ ጤነኞችም ብንሆን ለእናንተ ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እብዶች ብንሆን ለእግዚአብሔር ስንል ነው፤ ባለ አእምሮዎች ብንሆንም ለእናንተ ስንል ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እብዶች ብንሆን፥ ለእግዚአብሔር ነው፤ ባለ አእምሮዎች ብንሆን፥ ለእናንተ ነው።

See the chapter Copy




2 ቆሮንቶስ 5:13
15 Cross References  

እነሆ እና​ንተ ስላ​ገ​በ​ራ​ች​ሁኝ በመ​መ​ካቴ ሰነፍ ሆንሁ፤ ለእ​ኔማ በእ​ና​ንተ ዘንድ ልከ​ብ​ርና እና​ን​ተም ምስ​ክ​ሮች ልት​ሆ​ኑኝ ይገ​ባኝ ነበር፤ እኔ እንደ ኢም​ንት ብሆ​ንም ዋና​ዎቹ ሐዋ​ር​ያት ሁሉ ከሠ​ሩት ሥራ ያጐ​ደ​ል​ሁ​ባ​ችሁ የለ​ምና።


ልመካ ብሻም አላ​ዋቂ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ እው​ነ​ቱን እና​ገ​ራ​ለ​ሁና፤ ነገር ግን ስላ​ዩ​ኝና ስለ ሰሙኝ እን​ደ​ም​በ​ልጥ አድ​ር​ገው እን​ዳ​ይ​ጠ​ራ​ጠ​ሩኝ ትቸ​ዋ​ለሁ።


በስ​ን​ፍ​ናዬ እና​ገር ዘንድ ጥቂት ልት​ታ​ገ​ሡኝ ይገባ ነበር፤ ቢሆ​ንም በር​ግጥ ታገ​ሡኝ፤


በተ​ሰ​ጠኝ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ሁላ​ች​ሁም እን​ዳ​ት​ታ​በዩ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ ራሳ​ች​ሁን ከዝ​ሙት የም​ታ​ነ​ጹ​በ​ትን ዐስቡ እንጂ ትዕ​ቢ​ትን አታ​ስቡ፤ ሁሉም እንደ እም​ነቱ መጠን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አደ​ለው ይኑር።


ስለዚህ እነርሱ ደግሞ በክርስቶስ ኢየሱስ ያለውን መዳን ከዘላለም ክብር ጋር እንዲያገኙ ስለ ተመረጡት በነገር ሁሉ እጸናለሁ።


ወንጌላችን በኀይልና በመንፈስ ቅዱስ በብዙ መረዳትም እንጂ በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና፤ በእናንተ ዘንድ ስለ እናንተ እንዴት እንደ ነበርን ታውቃላችሁ።


አሁ​ንም በመ​ከ​ራዬ ደስ ይለ​ኛል፤ አካሉ ስለ ሆነች ስለ ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን፥ ከክ​ር​ስ​ቶስ መከራ ጥቂ​ቱን በሥ​ጋዬ እፈ​ጽ​ማ​ለሁ።


ይህን የጻ​ፍ​ሁ​ላ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ስለ እኛ እንደ ተጋ​ችሁ ይታ​ወቅ ዘንድ ነው እንጂ ስለ በደ​ለና ስለ ተበ​ደለ ሰው አይ​ደ​ለም።


ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ረ​ውን ሰው ሁሉ፥ የሚ​ለ​ፈ​ል​ፈ​ው​ንም ሰው ሁሉ በግ​ዞት ታኖ​ረ​ውና በፈ​ሳ​ሽም ታሰ​ጥ​መው ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አለቃ እን​ድ​ት​ሆን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በካ​ህኑ በዮ​ዳሄ ፋንታ ካህን አድ​ር​ጎ​ሃል።


ዘመዶቹም ሰምተው “አበደ” ብለዋልና ሊይዙት ወጡ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements