Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ቆሮንቶስ 4:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በጨ​ለማ ውስጥ “ብር​ሃን ይብራ” ያለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ፊት የክ​ብ​ሩን ዕው​ቀት ብር​ሃን በል​ባ​ችን አብ​ር​ቶ​ል​ና​ልና።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት እግዚአብሔር የክብሩን ዕውቀት ብርሃን ይሰጠን ዘንድ፣ “በጨለማ ብርሃን ይብራ” ያለው እግዚአብሔር ብርሃኑን በልባችን አብርቷልና።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት እንዲሰጥ ብርሃን በልባችን ውስጥ ያበራ፥ “በጨለማ ብርሃን ይብራ፤” ያለው እግዚአብሔር ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 “ብርሃን በጨለማ ውስጥ ይብራ!” ብሎ የተናገረ እግዚአብሔር በክርስቶስ መልክ የሚያበራውን የእግዚአብሔርን ክብር የማወቅ ብርሃን እንዲሰጠን ብርሃኑን በልባችን ውስጥ እንዲበራ አደረገ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት ብርሃን እንዲሰጥ በልባችን ውስጥ የበራ፦ በጨለማ ብርሃን ይብራ ያለ እግዚአብሔር ነውና።

See the chapter Copy




2 ቆሮንቶስ 4:6
35 Cross References  

እነሆ፥ ጨለማ ምድ​ርን፥ ድቅ​ድቅ ጨለ​ማም አሕ​ዛ​ብን ይሸ​ፍ​ናል፤ ነገር ግን በአ​ንቺ ላይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይገ​ለ​ጣል፤ ክብ​ሩም በአ​ንቺ ላይ ይታ​ያል፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ብር​ሃን ይሁን” አለ፤ ብር​ሃ​ንም ሆነ።


እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤


ከእርሱም ይልቅ እጅግ የጸና የትንቢት ቃል አለን፤ ምድርም እስኪጠባ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪወጣ ድረስ፥ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብራት እንደሚጠነቀቅ ይህን ቃል እየጠነቀቃችሁ መልካም ታደርጋላችሁ።


ቀድሞ ጨለማ ነበ​ራ​ች​ሁና፥ ዛሬ ግን በጌ​ታ​ችን ብር​ሃን ሆና​ች​ኋል። እን​ግ​ዲ​ህስ እንደ ብር​ሃን ልጆች ተመ​ላ​ለሱ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​መ​ስ​ለው የክ​ር​ስ​ቶስ የክ​ብሩ ወን​ጌል ብር​ሃን እን​ዳ​ያ​በ​ራ​ላ​ቸው የዚህ ዓለም አም​ላክ ልባ​ቸ​ውን አሳ​ው​ሮ​አ​ልና።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ይገ​ለጥ፤ ሥጋ ለባ​ሹም ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትድ​ግና ይይ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።”


እር​ሱም የክ​ብሩ መን​ጸ​ባ​ረ​ቅና የመ​ልኩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በሥ​ል​ጣኑ ቃል እየ​ደ​ገፈ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንን በራሱ ካነጻ በኋላ፥ በሰ​ማ​ያት በግ​ር​ማው ቀኝ ተቀ​መጠ።


እኛስ ሁላ​ችን ፊታ​ች​ንን ገል​ጠን በመ​ስ​ተ​ዋት እን​ደ​ሚ​ያይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር እና​ያ​ለን፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ እንደ ተሰ​ጠን መጠን የእ​ር​ሱን አር​አያ እን​መ​ስል ዘንድ ከክ​ብር ወደ ክብር እን​ገ​ባ​ለን።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ብታ​ም​ናስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር ታያ​ለሽ አላ​ል​ሁ​ሽም ነበ​ርን?” አላት።


ብር​ሃ​ንን ፈጠ​ርሁ፤ ጨለ​ማ​ው​ንም ፈጠ​ርሁ፤ ሰላ​ም​ንም አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ክፋ​ት​ንም አመ​ጣ​ለሁ፤ እነ​ዚ​ህን ሁሉ ያደ​ረ​ግሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ።


ይኸ​ውም የማ​ይ​ታይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​መ​ስ​ለው፥ ከፍ​ጥ​ረቱ ሁሉ በላይ የሆነ በኵር ነው።


ይኸ​ውም የክ​ብር ባለ​ቤት የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አባቱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጥ​በ​ብን መን​ፈስ ይሰ​ጣ​ችሁ ዘንድ፥ ዕው​ቀ​ቱ​ንም ይገ​ል​ጽ​ላ​ችሁ ዘንድ፥


ያም ቃል ሥጋ ሆነ፤ በእ​ኛም አደረ፤ ለአ​ባቱ አንድ እንደ ሆነ ልጅ ክብር ያለ ክብ​ሩን አየን፤ ጸጋ​ንና እው​ነ​ትን የተ​መላ ነው።


ረዥም ዕድ​ሜን አጠ​ግ​በ​ዋ​ለሁ፥ ማዳ​ኔ​ንም አሳ​የ​ዋ​ለሁ።


ከክ​ፉ​ዎች ሴራ ከብ​ዙ​ዎች ዐመፅ አድ​ራ​ጊ​ዎች ሰው​ረኝ።


ለእነርሱም ከሰማይ በተላከ በመንፈስ ቅዱስ ወንጌልን የሰበኩላችሁ ሰዎች አሁን ባወሩላችሁ ነገር እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው፤ ይህንም ነገር መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ።


ይኸ​ውም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መልኩ ነው፤ ቀምቶ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሆነ አይ​ደ​ለም።


ኢሳ​ይ​ያስ ጌት​ነ​ቱን አይ​ቶ​አ​ልና፥ ይህን ተና​ገረ፤ ስለ እር​ሱም መሰ​ከረ።


ሁሉ ከአ​ባቴ ዘንድ ተሰ​ጠኝ፤ ወልድ ማን እንደ ሆነ ከአብ በቀር የሚ​ያ​ውቅ የለም፤ አብም ማን እንደ ሆነ ከወ​ልድ በቀር የሚ​ያ​ውቅ የለም። ወልድ ግን ለወ​ደ​ደው ይገ​ል​ጥ​ለ​ታል።”


የዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ምድረ በዳ ያብ​ባል፤ ሐሤ​ት​ንም ያደ​ር​ጋል፤ የሊ​ባ​ኖስ ክብ​ርና የቀ​ር​ሜ​ሎስ ክብር ይሰ​ጠ​ዋል፤ ሕዝ​ቤም የጌ​ታን ክብር፥ የአ​ም​ላ​ክ​ንም ግርማ ያያሉ።


ይኸ​ውም ዐይ​ና​ቸ​ውን ትከ​ፍ​ት​ላ​ቸው ዘንድ፥ ከጨ​ለ​ማም ወደ ብር​ሃን፥ ሰይ​ጣ​ንን ከማ​ም​ለ​ክም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትመ​ል​ሳ​ቸው ዘንድ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸው ዘንድ፥ በስ​ሜም በማ​መን ከቅ​ዱ​ሳን ጋር አን​ድ​ነ​ትን ያገኙ ዘንድ ነው።’


በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የጥ​በብ ቃል የሚ​ሰ​ጠው አለ፤ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም የዕ​ው​ቀት ቃል የሚ​ሰ​ጠው አለ።


ይቅር የም​ት​ሉት ቢኖር፥ እኔም ከእ​ና​ንተ ጋር ይቅር እለ​ዋ​ለሁ፤ እኔም ይቅር ያል​ሁ​ትን በክ​ር​ስ​ቶስ ፊት ስለ እና​ንተ ይቅር ብያ​ለሁ።


ዐይነ ልቡ​ና​ች​ሁ​ንም ያበ​ራ​ላ​ችሁ ዘንድ፥ የተ​ጠ​ራ​ች​ሁ​በት ተስ​ፋም ምን እንደ ሆነ፥ በቅ​ዱ​ሳ​ንም የር​ስቱ ክብር ባለ​ጸ​ግ​ነት ምን እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ፥


ነገር ግን አንድ ጊዜ ብር​ሃን የበ​ራ​ላ​ቸ​ውን፥ ሰማ​ያ​ዊ​ው​ንም ስጦታ የቀ​መ​ሱ​ትን፥ ከመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም ተካ​ፋ​ዮች ሆነው የነ​በ​ሩ​ትን፥


Follow us:

Advertisements


Advertisements