Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ቆሮንቶስ 4:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ስለ​ዚህ አን​ሰ​ልች፤ በውጭ ያለው ሰው​ነ​ታ​ችን ያረ​ጃ​ልና፤ በው​ስጥ ያለው ሰው​ነ​ታ​ችን ግን ዘወ​ትር ይታ​ደ​ሳል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ስለዚህ ተስፋ አንቈርጥም፤ ውጫዊው ሰውነታችን እየጠፋ ቢሄድም እንኳ፣ ውስጣዊው ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ስለዚህ አንታክትም፤ ውጫዊው ሰውነታችን እየመነመነ ቢሄድ እንኳን፥ ውስጣዊው ሰውነታችን በየዕለቱ ይታደሳል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ስለዚህ ተስፋ አንቈርጥም፤ ምንም እንኳ የውጪው ሰውነታችን ቢጠፋ የውስጡ ሰውነታችን በየቀኑ ይታደሳል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ስለዚህም አንታክትም፥ ነገር ግን የውጭው ሰውነታችን ቢጠፋ እንኳ የውስጡ ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል።

See the chapter Copy




2 ቆሮንቶስ 4:16
22 Cross References  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተስፋ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉና የሚ​ታ​ገሡ ግን ኀይ​ላ​ቸ​ውን ያድ​ሳሉ፤ እንደ ንስር ክንፍ ያወ​ጣሉ፤ ይሮ​ጣሉ፤ አይ​ታ​ክ​ቱ​ምም፤ ይሄ​ዳሉ፤ አይ​ራ​ቡ​ምም።


ፈጣ​ሪ​ውን ለመ​ም​ሰል በዕ​ው​ቀት የሚ​ታ​ደ​ሰ​ውን አዲ​ሱን ሰው ልበ​ሱት።


ለደ​ካ​ሞች ኀይ​ልን ይሰ​ጣል፤ መከራ የሚ​ቀ​በ​ሉ​ት​ንም አያ​ሳ​ዝ​ና​ቸ​ውም።


ይህን ዓለም አት​ም​ሰሉ፤ ልባ​ች​ሁ​ንም አድሱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ወ​ደ​ውን መል​ካ​ሙ​ንና እው​ነ​ቱን፥ ፍጹ​ሙ​ንም መር​ምሩ።


ስለ​ዚህ እንደ ቸር​ነቱ የሰ​ጠን ይህ መል​እ​ክት አለ​ንና አን​ሰ​ለ​ችም።


እንደ ጌት​ነቱ ምላት ይሰ​ጣ​ችሁ ዘንድ፥ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም ኀይል ያጸ​ና​ችሁ ዘንድ።


በል​ቡ​ናዬ ውስጥ ያለ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ መል​ካም ነው።


እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤


ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ።


የል​ቡ​ና​ች​ሁን ዕው​ቀት አድሱ።


አሁ​ንም የተ​ወ​ደ​ዳ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ የጸ​ና​ች​ሁና የማ​ት​ና​ወጡ ሁኑ፤ ዘወ​ትር በጎ ምግ​ባ​ርን አብ​ዝ​ታ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አበ​ር​ክቱ፤ ስለ ጌታ​ችን መድ​ከ​ማ​ችሁ ለከ​ንቱ እን​ዳ​ይ​ደለ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።


እኔ ግን እጥፍ ድርብ አወ​ጣ​ለሁ፤ ስለ ሕይ​ወ​ታ​ች​ሁም ሰው​ነ​ቴን አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ እና​ን​ተ​ንም እጅግ ብወ​ዳ​ችሁ ራሴን ወደ​ድሁ።


የዕ​ለት ምግ​ባ​ች​ንን በየ​ዕ​ለቱ ስጠን።


አንተ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ማሜ ላይ ኀዘ​ንን ጨም​ሮ​ብ​ኛ​ልና ወዮ​ልኝ! በል​ቅ​ሶዬ ጩኸት ደክ​ሜ​አ​ለሁ፤ ዕረ​ፍ​ት​ንም አላ​ገ​ኘ​ሁም ብለ​ሃል።


ስለ ክርስቶስ ስም ብትነቀፉ የክብር መንፈስ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ላይ ያርፋልና ብፁዓን ናችሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements