Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ቆሮንቶስ 12:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ወደ ገነ​ትም ነጥ​ቀው ወሰ​ዱት፤ በዚ​ያም ሰው ሊና​ገ​ረው የማ​ይ​ች​ለ​ውን የማ​ይ​ተ​ረ​ጐም ነገር ሰማ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እርሱም ወደ ገነት እንደ ተነጠቀ፣ በዚያም በሰው አንደበት ሊገለጥ የማይችል፣ ሰውም እንዲናገረው ያልተፈቀደለት ነገር ሰማ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ወደ ገነት ተነጠቀ፤ በሰው አንደበት ሊገለጥ የማይችለውን፥ ሰውም ሊናገር ያልተፈቀደለትን ነገር ሰማ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እርሱ ወደ ገነት ተነጥቆ በሰው ቃል ሊገለጥና ሰውም ሊናገረው የማይችለውን ነገር ሰማ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ወደ ገነት ተነጠቀ፥ ሰውም ሊናገር የማይገባውን የማይነገረውን ቃል ሰማ።

See the chapter Copy




2 ቆሮንቶስ 12:4
9 Cross References  

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “እው​ነት እል​ሃ​ለሁ፥ ዛሬ በገ​ነት ከእኔ ጋር ትሆ​ና​ለህ።”


መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ እሰጠዋለሁ።


በጫ​ፎቹ ብዛት ውብ አደ​ረ​ግ​ሁት፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ገነት በዔ​ድን የነ​በሩ ዛፎች ሁሉ ቀኑ​በት።


እጅ መሳ​ይ​ንም ዘረጋ፤ በራስ ጠጕ​ሬም ያዘኝ፤ መን​ፈ​ስም በም​ድ​ርና በሰ​ማይ መካ​ከል አነ​ሣኝ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ራእይ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ሰሜን ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ በር መግ​ቢያ ቅን​አት የተ​ባ​ለው ምስል ወደ አለ​በት አመ​ጣኝ፤


ከው​ኃ​ዉም ከወጡ በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ፊል​ጶ​ስን ነጥቆ ወሰ​ደው፤ ጃን​ደ​ረ​ባ​ዉም ከዚያ ወዲያ አላ​የ​ውም፤ ደስ እያ​ለ​ውም መን​ገ​ዱን ሄደ።


የሰ​ውን ሁሉ ቋንቋ ባውቅ፥ የመ​ላ​እ​ክ​ት​ንም ሁሉ ቋንቋ ባውቅ፥ ነገር ግን ፍቅር ከሌ​ለኝ እን​ደ​ሚ​ጮህ ነሐስ፥ ወይም እን​ደ​ሚ​መታ ከበሮ መሆኔ ነው።


በክ​ር​ስ​ቶስ ያመነ አንድ ሰው አው​ቃ​ለሁ፤ ዘመኑ ከዐ​ሥራ አራት ዓመት በፊት ነው፤ ነገር ግን በሥ​ጋው ይሁን በነ​ፍሱ እንጃ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያው​ቃል፤ ያን ሰው እስከ ሦስ​ተ​ኛው ሰማይ ድረስ ነጥ​ቀው ወሰ​ዱት።


ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው ታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።


አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጅዋም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements