Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ቆሮንቶስ 11:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ወደ እና​ንተ የመ​ጣና እኛ ወደ አላ​ስ​ተ​ማ​ር​ና​ችሁ ወደ ሌላ ኢየ​ሱስ የጠ​ራ​ችሁ ቢኖር፥ ወይም ያል​ተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁት ሌላ መን​ፈስ ቢኖር፥ ወይም ያል​ተ​ማ​ራ​ች​ሁት ሌላ ወን​ጌል ቢኖር ልት​ጠ​ብ​ቁን ይገ​ባል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ምክንያቱም አንድ ሰው ወደ እናንተ መጥቶ እኛ ከሰበክንላችሁ ኢየሱስ ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክላችሁ፣ ወይም ከተቀበላችሁት መንፈስ የተለየ መንፈስ ብትቀበሉ፣ ወይም ከተቀበላችሁት ወንጌል የተለየ ወንጌል ብትቀበሉ፣ ነገሩን በዝምታ ታልፉታላችሁ ማለት ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ምክንያቱም አንዱ መጥቶ እኛ ያልሰበክነውን ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክ፥ ወይም ያላገኛችሁትን ልዩ መንፈስ ወይም ያልተቀበላችሁትን ልዩ ወንጌል ሆኖ ብታገኙት፥ በመልካምነታችሁ ትታገሡታላችሁ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 አንድ ሰው ወደ እናንተ መጥቶ እኛ የሰበክነውን ሳይሆን ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክላችሁ ወይም እናንተ የተቀበላችሁትን መንፈስ ሳይሆን ሌላ መንፈስ ብትቀበሉ፥ ወይም የተቀበላችሁትን ወንጌል ሳይሆን ሌላ ወንጌል ብትቀበሉ፥ ዝም ብላችሁ ተሸነፋችሁ ማለት ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የሚመጣውም ያልሰበክነውን ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክ፥ ወይም ያላገኛችሁትን ልዩ መንፈስ ወይም ያልተቀበላችሁትን ልዩ ወንጌል ብታገኙ፥ በመልካም ትታገሡታላችሁ።

See the chapter Copy




2 ቆሮንቶስ 11:4
12 Cross References  

ነገር ግን ከተ​መ​ሠ​ረ​ተው በቀር ሌላ መሠ​ረት ሊመ​ሠ​ርት የሚ​ችል የለም፤ መሠ​ረ​ቱም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ነው።


አንድ እግዚአብሔር አለና፤ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፤ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤


በእ​ና​ንተ ዘንድ ይህን ብቻ ላውቅ እወ​ድ​ዳ​ለሁ፤ መን​ፈስ ቅዱ​ስን የተ​ቀ​በ​ላ​ችሁ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት ነውን? ወይስ ሃይ​ማ​ኖ​ትን በመ​ስ​ማት?


ዳግ​መ​ናም አባ አባት ብለን የም​ን​ጮ​ህ​በ​ትን የል​ጅ​ነት መን​ፈስ ተቀ​በ​ላ​ችሁ እንጂ እንደ ገና ለፍ​ር​ሀት የባ​ር​ነት መን​ፈ​ስን አል​ተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁ​ምና።


መዳ​ንም በሌላ በማ​ንም የለም፤ ከሰ​ማይ በታች እን​ድ​ን​በት ዘንድ የሚ​ገ​ባን ለሰው የተ​ሰጠ ሌላ ስም ከቶ የለ​ምና።”


እንዲህም አላቸው “ወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እጅግ ንቃችኋል።


ለክ​ር​ስ​ቶ​ስም ወን​ጌል ጢሮ​አዳ በደ​ረ​ስሁ ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሩ ተከ​ፈ​ተ​ልኝ።


በስ​ን​ፍ​ናዬ እና​ገር ዘንድ ጥቂት ልት​ታ​ገ​ሡኝ ይገባ ነበር፤ ቢሆ​ንም በር​ግጥ ታገ​ሡኝ፤


ወደ መቄዶንያ በሄድሁ ጊዜ፥ አንዳንዶች ልዩ ትምህርትን እንዳያስተምሩና ወደ ተረት መጨረሻም ወደሌለው ወደ ትውልዶች ታሪክ እንዳያደምጡ ልታዛቸው በኤፌሶን ትቀመጥ ዘንድ ለመንሁህ፤ እንደ እነዚህ ያሉ ነገሮች ክርክርን ያመጣሉና፤ በእምነት ግን ላለ ለእግዚአብሔር መጋቢነት አይጠቅሙም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements