Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ጢሞቴዎስ 5:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ባል የሞተባቸውን ቆነጃጅት ግን አትቀበል፤ በክርስቶስ ላይ ተነሥተው ሲቀማጠሉ ሊያገቡ ይወዳሉና፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ወጣት መበለቶችን ግን እንዲህ ባለው መዝገብ አትጻፋቸው፤ ምክንያቱም ሥጋዊ ፍላጎታቸው ለክርስቶስ በገቡት ቃል ላይ በሚያይልበት ጊዜ ለማግባት ይሻሉና።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ወጣት መበለታትን ግን በመዝገብ ላይ አታካትት፤ ሥጋዊ ምኞታቸው ከክርስቶስ ስለሚለያቸው መጋባትን ይፈልጋሉና፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ባሎቻቸው የሞቱባቸው በዕድሜ ያልገፉ ሴቶች ሥጋዊ ምኞታቸው አሸንፎአቸው ለክርስቶስ ያላቸው ፍቅር ሲቀነስ ባል ማግባት ስለሚፈልጉ እነርሱን በመበለቶች መዝገብ አትጻፋቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ባል የሞተባቸውን ቆነጃጅት ግን አትቀበል፤ በክርስቶስ ላይ ተነሥተው ሲቀማጠሉ ሊያገቡ ይወዳሉና፤

See the chapter Copy




1 ጢሞቴዎስ 5:11
13 Cross References  

እንግዲህ ቆነጃጅት ሊያገቡ፥ ልጆችንም ሊወልዱ፥ ቤቶቻቸውንም ሊያስተዳድሩ፥ ተቃዋሚውም የሚሳደብበትን አንድን ምክንያት ስንኳ እንዳይሰጡ እፈቅዳለሁ፤


ከተ​ሰ​ማ​ራ​ችሁ በኋላ ጠገ​ባ​ችሁ፤ በጠ​ገ​ባ​ች​ሁም ጊዜ ልባ​ችሁ ታበየ፤ ስለ​ዚ​ህም ረሳ​ች​ሁኝ።


በምድር ላይ ተቀማጥላችኋል፤ በሴሰኝነትም ኖራችኋል፤ ለእርድ ቀን እንደሚያወፍር ልባችሁን አወፍራችኋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ አለ፥ “የጽ​ዮን ቆነ​ጃ​ጅት ኰር​ተ​ዋ​ልና፥ አን​ገ​ታ​ቸ​ውን እያ​ሰ​ገጉ በዐ​ይ​ና​ቸ​ውም እያ​ጣ​ቀሱ፥ በእ​ግ​ራ​ቸ​ውም እያ​ረ​ገዱ፥ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም እየ​ጐ​ተቱ፥ በእ​ግ​ራ​ቸ​ውም እያ​ማቱ ይሄ​ዳ​ሉና፤


ራስዋን እንደ አከበረችና እንደ ተቀማጠለች ልክ ሥቃይና ሐዘን ስጡአት። በልብዋ ‘ንግሥት ሆኜ እቀመጣለሁ፤ ባልቴትም አልሆንም፤ ሐዘንም ከቶ አላይም፤’ ስላለች፥


ከንቱና ከመጠን ይልቅ ታላቅ የሆነውን ቃል ይናገራሉና፤ በስሕተትም ከሚኖሩት አሁን የሚያመልጡትን በሥጋ ሴሰኛ ምኞት ያታልላሉ።


ባልቴት በመዝገብ ብትጻፍ ዕድሜዋ ከስድሳ ዓመት እንዳያንስ፤ የአንድም ባል ሚስት የነበረች እንድትሆን ያስፈልጋል፤


እነዚህ ውሸተኞች መጋባትን ይከለክላሉ፤ አምነውም እውነትን የሚያውቁ ከምስጋና ጋር ይቀበሉ ዘንድ እግዚአብሔር ከፈጠረው መብል እንዲርቁ ያዝዛሉ።


ያዕ​ቆብ በላ፤ ጠገ​በም፤ የተ​ወ​ደ​ደ​ውን ጥጋብ አቀ​ና​ጣው፤ ሰባ፥ ወፈረ፥ ሰፋ፤ የፈ​ጠ​ረ​ው​ንም እግ​ዚ​አ​ሔ​ርን ተወ፤ ከሕ​ይ​ወቱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ራቀ።


የፊተኛውንም እምነታቸውን ስለ ናቁ ይፈረድባቸዋል፤


አሕዛብ ሁሉ ከዝሙትዋ ቍጣ ወይን ጠጅ የተነሣ ወድቀዋልና፤ የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ፤ የምድርም ነጋዴዎች ከቅምጥልነትዋ ኀይል የተነሣ ባለጠጋዎች ሆኑ፤” ብሎ ጮኸ።


ከእርስዋም ጋር የሴሰኑና የተቀማጠሉ የምድር ነገሥታት የመቃጠልዋን ጢስ ሲያዩ ስለ እርስዋ እየጮሁ እያሉ ያለቅሳሉ፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements