Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 9:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ማል​ደ​ውም ተነሡ፤ በነ​ጋም ጊዜ ሳሙ​ኤል ሳኦ​ልን፥ “ከሰ​ገ​ነቱ ላይ ጠርቶ፦ ተነ​ሣና ላሰ​ና​ብ​ትህ” አለው። ሳኦ​ልም ተነሣ፤ እር​ሱና ሳሙ​ኤ​ልም ሁለቱ ወደ ሜዳ ወጡ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 በማለዳ ተነሡ፤ ሳሙኤል ሳኦልን ከሰገነቱ ላይ ጠርቶ፣ “ላሰናብትህ ስለ ሆነ ተዘጋጅ” አለው። ሳኦልም ተዘጋጅቶ እንዳበቃ፣ ከሳሙኤል ጋራ ተያይዘው ወደ ውጭ ወጡ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 በነጋም ጊዜ በማለዳ ሳሙኤል ሳኦልን ከሰገነቱ ላይ ጠርቶ፥ “ላሰናብትህ ስለሆነ ተዘጋጅ” አለው። ሳኦልም ተዘጋጅቶ እንዳበቃ፥ ከሳሙኤል ጋር ተያይዘው ወደ ውጭ ወጡ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 በነጋም ጊዜ ማለዳ ሳሙኤል ከሰገነቱ ላይ ሳኦልን ጠርቶ “እንግዲህ ተነሥ፤ ላሰናብትህና መንገድህን ቀጥል” አለው፤ ሳኦልም ከመኝታው ተነሣ፤ እርሱና ሳሙኤልም አብረው ወደ መንገዱ ሄዱ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ማልዶም ተነሡ፥ በነጋም ጊዜ ሳሙኤል ሳኦልን ከሰገነቱ ላይ ጠርቶ፦ ተነሣና ላስናብትህ አለው። ሳኦልም ተነሣ፥ እርሱና ሳሙኤልም ሁለቱ ወደ ሜዳ ወጡ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 9:26
6 Cross References  

እር​ሱም፥ “ተነሺ እን​ሂድ” አላት፤ እር​ስዋ ግን ሞታ ነበ​ርና አል​መ​ለ​ሰ​ችም፤ በዚያ ጊዜም በአ​ህ​ያው ላይ ጫናት፤ ተነ​ሥ​ቶም ወደ ስፍ​ራው ተመ​ለሰ።


ተነ​ሣና ሕዝ​ቡን ቀድስ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ‘እስ​ራ​ኤል ሆይ! እርም የሆነ ነገር በመ​ካ​ከ​ልህ አለ፤ እር​ምም የሆ​ነ​ውን ነገር ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ እስ​ክ​ታ​ጠፉ ድረስ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ፊት መቆም አት​ች​ሉም’ ብሎ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሮ​አ​ልና እስከ ነገ ራሳ​ች​ሁን አንጹ።


ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ወጥ​ተው ገና ሳይ​ርቁ ዮሴፍ ለቤቱ አዛዥ እን​ዲህ አለ፥ “ተነ​ሥ​ተህ ሰዎ​ቹን ተከ​ት​ለህ ያዛ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ በመ​ል​ካሙ ፈንታ ስለ​ምን ክፉን መለ​ሳ​ችሁ?


ሎጥም ወጣ፤ ልጆ​ቹን ለሚ​ያ​ገ​ቡት ለአ​ማ​ቾ​ቹም አላ​ቸው፥ “ተነሡ፤ ከዚች ስፍራ ውጡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ​ችን ከተማ ያጠ​ፋ​ታ​ልና።” ለአ​ማ​ቾቹ ግን የሚ​ያ​ፌ​ዝ​ባ​ቸው መሰ​ላ​ቸው።


ከባማ ኮረ​ብ​ታም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ወረዱ፤ ሳሙ​ኤ​ልም ለሳ​ኦል በሰ​ገ​ነቱ ላይ መኝታ አዘ​ጋ​ጀ​ለት፤ እር​ሱም ተኛ።


እነ​ር​ሱም በከ​ተ​ማ​ዪቱ ዳር ሲወ​ርዱ ሳሙ​ኤል ሳኦ​ልን፥ “ብላ​ቴ​ናው ወደ ፊታ​ችን እን​ዲ​ያ​ልፍ እዘ​ዘው፤ አንተ ግን ከእኔ ጋር ከዚህ ቁምና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ” አለው። ብላ​ቴ​ና​ውም አለፈ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements