Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 9:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ል​ንና ብላ​ቴ​ና​ውን ወስዶ ወደ አዳ​ራሽ አገ​ባ​ቸው፥ ሰባ ሰዎ​ችም ምሳ በሚ​በ​ሉ​በት በም​ር​ፋቁ ራስ አስ​ቀ​መ​ጣ​ቸው፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ከዚያም ሳሙኤል ሳኦልንና አገልጋዩን ወደ አዳራሹ አመጣ፤ ከተጋበዙትም ሠላሳ ያህል ሰዎች ሁሉ በላይ አስቀመጣቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ከዚያም ሳሙኤል ሳኦልንና አገልጋዩን ወደ አዳራሹ አመጣ፤ ከተጋበዙትም ሠላሳ ያህል ሰዎች ሁሉ በላይ አስቀመጣቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ከዚህ በኋላ ሳኦልንና አገልጋዩን እየመራ ወደ ታላቁ አዳራሽ አስገብቶ ብዛታቸው ሠላሳ የሚሆኑ እንግዶች በተቀመጡበት ገበታ ከሁሉ በላይ የሆነውን የክብር ቦታ ሰጣቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ሳሙኤልም ሳኦልንና ብላቴናውን ወስዶ ወደ አዳራሽ አገባቸው፥ በመርፈቂያውም ራስ አስቀመጣቸው፥ የተጠሩትም ሠላሳ ሰዎች ያህል ነበሩ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 9:22
4 Cross References  

የጠ​ራህ ሰው ቢኖ​ርና ብት​ሄድ ግን የጠ​ራህ በመጣ ጊዜ ወዳጄ ወደ ላይ​ኛው መቀ​መጫ ውጣ ይልህ ዘንድ በታ​ች​ኛው መቀ​መጫ ተቀ​መጥ፤ ያን​ጊ​ዜም ከአ​ንተ ጋር ለማ​ዕድ በተ​ቀ​መ​ጡት ሰዎች ፊት ክብር ይሆ​ን​ል​ሃል።


ለእ​ር​ሱም ለብ​ቻው አቀ​ረቡ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም ለብ​ቻ​ቸው፤ ከእ​ርሱ ጋር ለሚ​በ​ሉት ለግ​ብፅ ሰዎ​ችም ለብ​ቻ​ቸው፤ የግ​ብፅ ሰዎች ከዕ​ብ​ራ​ው​ያን ጋር መብ​ላት አይ​ች​ሉ​ምና፥ ይህ ለግ​ብፅ ሰዎች እንደ መር​ከስ ነውና።


ሳኦ​ልም መልሶ፥ “እኔ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ከሚ​ያ​ንስ ወገን የሆ​ንሁ ብን​ያ​ማዊ ሰው አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? ወገ​ኔስ ከብ​ን​ያም ነገድ ወገ​ኖች ሁሉ የሚ​ያ​ንስ አይ​ደ​ለ​ምን? እን​ዲ​ህስ ያለ​ውን ነገር ለምን ነገ​ር​ኸኝ?” አለ።


ሳሙ​ኤ​ልም ወጥ ቤቱን፥ “በአ​ንተ ዘንድ አኑ​ረው ብዬ የሰ​ጠ​ሁ​ህን እድል ፋንታ አምጣ” አለው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements