Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 9:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ሳኦ​ልም መልሶ፥ “እኔ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ከሚ​ያ​ንስ ወገን የሆ​ንሁ ብን​ያ​ማዊ ሰው አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? ወገ​ኔስ ከብ​ን​ያም ነገድ ወገ​ኖች ሁሉ የሚ​ያ​ንስ አይ​ደ​ለ​ምን? እን​ዲ​ህስ ያለ​ውን ነገር ለምን ነገ​ር​ኸኝ?” አለ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ሳኦልም፣ “እኔ ከእስራኤል ነገዶች ውስጥ በጣም አነስተኛ ከሆነው ከብንያም ወገን አይደለሁምን? ጐሣዬስ ከብንያም ነገድ ጐሣዎች ሁሉ የሚያንስ አይደለምን? ታዲያ እንዲህ ያለውን ነገር ስለ ምን ትነግረኛለህ?” ብሎ መለሰለት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ሳኦልም፥ “እኔ ከእስራኤል ነገዶች ውስጥ በጣም አነስተኛ ከሆነው ከብንያም ወገን አይደለሁምን? ወገኔስ ከብንያም ነገድ ወገኖች ሁሉ የሚያንስ አይደለምን? ታዲያ እንዲህ ያለውን ነገር ስለምን ትነግረኛለህ?” ብሎ መለሰለት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ሳኦልም “እኔ ከእስራኤል ነገዶች መካከል በተለይ ታናሽ የሆነው የብንያም ነገድ ተወላጅ ነኝ፤ በዚሁም ነገድ ውስጥ እንኳ የእኔ ቤተሰብ በጣም አነስተኛ ነው፤ ታዲያ እንዲህ ያለውን ጉዳይ ለእኔ ስለምን ትነግረኛለህ?” ሲል መለሰለት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ሳኦልም መልሶ፦ እኔ ከእስራኤል ነገዶች ከሚያንስ ወገን የሆንሁ ብንያማዊ አይደለሁምን? ወገኔስ ከብንያም ነገድ ወገኖች ሁሉ የሚያንስ አይደለምን? እንዲህስ ያለውን ነገር ለምን ነገርኸኝ? አለ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 9:21
13 Cross References  

ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን አለው፥ “በፊቱ ምንም ታናሽ ብት​ሆን ለእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች አለቃ አል​ሆ​ን​ህ​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባህ።


ከቅ​ዱ​ሳን ሁሉ ለማ​ንስ ለእኔ የማ​ይ​መ​ረ​መ​ረ​ውን የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ባለ​ጸ​ግ​ነት ለአ​ሕ​ዛብ አስ​ተ​ምር ዘንድ ይህን ጸጋ ሰጠኝ።


ራሱን ከፍ የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ ይዋ​ረ​ዳ​ልና፤ ራሱ​ንም ያሚ​ያ​ዋ​ርድ ከፍ ይላ​ልና።”


በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ላይ ኃጢ​አ​ትን ጨም​ር​ባ​ቸው፥ በጽ​ድ​ቅ​ህም አይ​ግቡ።


ኤፍ​ሬም እንደ ተና​ገረ በእ​ስ​ራ​ኤል ሥር​ዐ​ቱን ወሰደ፤ ለበ​ዓ​ልም አደ​ረ​ገው፤ ሞተም።


የሳ​ኦ​ልም ብላ​ቴ​ኖች ይህን ቃል በዳ​ዊት ጆሮ ተና​ገሩ፤ ዳዊ​ትም፥ “እኔ የተ​ዋ​ረ​ድ​ሁና ክብር የሌ​ለኝ ሰው ስሆን ለን​ጉሥ አማች እሆን ዘንድ ለእ​ና​ንተ ትንሽ ነገር ይመ​ስ​ላ​ች​ኋ​ልን?” አለ።


ዳዊ​ትም ሳኦ​ልን፥ “ለን​ጉሥ አማች እሆን ዘንድ እኔ ማን ነኝ? ሰው​ነ​ቴስ ምን​ድን ናት? የአ​ባ​ቴስ ወገን በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ምን​ድን ነው?” አለው።


ክፉ​ዎች ሰዎች ግን፥ “ያድ​ነን ዘንድ ይህ ሰው ማን ነው?” ብለው ናቁት፤ እጅ መን​ሻም አላ​መ​ጡ​ለ​ትም።


ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ል​ንና ብላ​ቴ​ና​ውን ወስዶ ወደ አዳ​ራሽ አገ​ባ​ቸው፥ ሰባ ሰዎ​ችም ምሳ በሚ​በ​ሉ​በት በም​ር​ፋቁ ራስ አስ​ቀ​መ​ጣ​ቸው፤


የሳ​ኦ​ልም አባት ቂስ ነበረ፤ የአ​ቤ​ኔ​ርም አባት የአ​ብ​ኤል ልጅ የያ​ሚን ልጅ ኔር ነበረ።


ከሕ​ያ​ዋን መጽ​ሐፍ ይደ​ም​ሰሱ፥ ከጻ​ድ​ቃ​ንም ጋር አይ​ጻፉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements