Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 9:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ለእ​ር​ሱም ሳኦል የሚ​ባል የተ​መ​ረጠ መል​ካም ልጅ ነበ​ረው፤ በም​ድር ሁሉ ላይ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከእ​ርሱ ይልቅ መል​ካም የሆነ ሰው አል​ነ​በ​ረም፤ ከሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ይልቅ ከት​ከ​ሻ​ውና ከዚ​ያም በላይ ቁመቱ ዘለግ ያለ ነበረ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ቂስም ከእስራኤል ልጆች መካከል በመልከ ቀናነቱ ተወዳዳሪ የማይገኝለት፣ ቁመቱም ከሌሎቹ ሁሉ ይልቅ ከትከሻው በላይ ዘለግ ያለ፣ ሳኦል የተባለ ወጣት ልጅ ነበረው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ቂስም ከእስራኤል ልጆች መካከል በመልከ ቀናነት ተወዳዳሪ የማይገኝለት፥ ቁመቱም ከሌሎቹ ሁሉ ይልቅ ከትከሻው በላይ ዘለግ ያለ፥ ሳኦል የተባለ ወጣት ልጅ ነበረው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ቂስም በመልከ ቀናነቱ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ሳኦል ተብሎ የሚጠራ ልጅ ነበረው፤ ሳኦልም ከትከሻው ዘለል፥ በቁመት ከሕዝቡ ሁሉ ይልቅ መለል ያለ ነበር፤ በመልከቀናነቱም ከሁሉ ይበልጥ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ለእርሱም ሳኦል የሚባል የተመረጠ መልካም ልጅ ነበረው፥ ከእስራኤልም ልጆች ከእርሱ ይልቅ መልካም የሆነ ሰው አልነበረም፥ ከሕዝቡም ሁሉ ይልቅ ከትከሻውና ከዚያም በላይ ቁመቱ ዘለግ ያለ ነበረ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 9:2
10 Cross References  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ፊቱን፥ የቁ​መ​ቱ​ንም ዘለ​ግታ አትይ፤ ሰው እን​ደ​ሚ​ያይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አያ​ይ​ምና ናቅ​ሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ልብን ያያል” አለው።


በዚ​ያም ግዙ​ፋን የሆ​ኑ​ትን አየን፤ እኛም በእ​ነ​ርሱ ፊት እንደ አን​በ​ጣ​ዎች ሆን፤ እን​ዲ​ሁም በፊ​ታ​ቸው ነበ​ርን፤” እያሉ የሰ​ለ​ሉ​አ​ትን ምድር ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አስ​ፈሪ አደ​ረ​ጓት።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆ​ችም የሰ​ውን ሴቶች ልጆች መል​ካ​ሞች እን​ደ​ሆኑ አዩ፤ ከመ​ረ​ጡ​አ​ቸ​ውም ሁሉ ሚስ​ቶ​ችን ለራ​ሳ​ቸው ወሰዱ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ጠቢብ በጥ​በቡ አይ​መካ፤ ኀያ​ልም በኀ​ይሉ አይ​መካ፤ ባለ​ጠ​ጋም በብ​ል​ጥ​ግ​ናው አይ​መካ፤


ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሰፈር የጌት ሰው ጎል​ያድ፥ ቁመ​ቱም ስድ​ስት ክንድ ከስ​ን​ዝር የሆነ፥ ኀይ​ለኛ ሰው መጣ።


የሳ​ኦ​ልም አባት የቂስ አህ​ዮች ጠፍ​ተው ነበር፤ ቂስም ልጁን ሳኦ​ልን፥ “ከብ​ላ​ቴ​ኖቹ አን​ዱን ወስ​ደህ ተነ​ሡና ሄዳ​ችሁ አህ​ዮ​ችን ፈልጉ” አለው።


የብ​ን​ያ​ም​ንም ነገድ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው አቀ​ረበ፤ ዕጣ​ውም በማ​ጥር ወገን ላይ ወደቀ፤ የማ​ጥ​ር​ንም ወገን በየ​ሰዉ አቀ​ረበ፤ ዕጣ​ውም በቂስ ልጅ በሳ​ኦል ላይ ወደቀ፤ ፈለ​ገ​ውም፤ አላ​ገ​ኘ​ው​ምም።


ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦ​ልን ወለደ፤ ሳኦ​ልም ዮና​ታ​ንን፥ ሜል​ኪ​ሳን፥ አሚ​ና​ዳ​ብን፥ አስ​በ​ኣ​ልን ወለደ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements